በቻይና ሰሜናዊ ክፍል ቲያንጂን ከተማ በደረሱ ሁለት ተከታታይ ፍንዳታዎች 44 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ።

በፍንዳታው የሟቾች ቁጥር ከዚህም ከፍ እንደሚል የተገመተ ሲሆን 500 ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል። የቻይና ዜና አገልግሎትን ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው፥ ፍንዳታዎቹ የተከሰቱት ሩሃይ ሎጂስቲክስ በተባለ አደገኛ የሆኑ ኬሚካሎችን በያዘ መጋዘን ላይ ነው። ፍንዳታው የፈጠረው የእሳት አደጋ በርካታ ህንጻዎችንና ተሽከርካሪዎችን ከጥቅም ውጪ አድርጓል። ሁለተኛው ፍንዳታ ከመጀመሪያው የበለጠ ከባድ እንደነበር የተነገረ ሲሆን፥ በሬክተር ስኬል 2 ነጥብ 9 የተመዘገበው የመሬት […]