መለስ (ለገሰ) ጀግና?! – ወገኖች ጀግንነት መቀለጃ ሆነ እንዴ? ተስፋዬ ገብረአብ
መለስ ፈሪው 1. በ 1980 ዓ.ም አጋማሽ በእንጥጮ በምትገኝ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች በሚስጥር በተሰበሰቡበት ቆርቆሮ ቤት አካባቢ ከሚጠብቁ ጓዶች አንዱ እንቅልፍ ይዞት ባርቆበት ጥይት ያጮሃል፥ ከዛም መለስየ ጀግናዋ የምትመራዉን ስብሰባ ዘንግታ ከባለሶስት ወንበር ላይ ወደኋላ ተንከባለለች ብሎ ኢያሱ በርሄ እየሳቀ አጫውቶኛል። ተሰብሳቢው ሳቁ አላበቃ በማለቱ መለስ ከወደቀበት ወንበሩ ላይ ለተወሰኑ ሰከንዶች ሳይነሳ ደርቆ ቆይቶ ነበር።
መለስ ፈሪ 2. አጠገቡ ያለ ስው ሁሉ ሲያስነጥስ በፍርሃት የሚነስረው መለስ: ማንበብ አለብኝ እያለ መሰሪያ ከሚጮህበት አካባቢዎች ሁሉ በዘዴ ይርቅ ነበር። ከፍተኛ ሰራዊት ተገድሎባቸው እንኳን በቃ እኛም እንታኮስ ሲሉት እንዴ ማን ሊመራው ነው ሰራዊቱን እያለ በማፈግፈግ ይታወቃል። ታዲያ በአንዱ የጦፈ ውጊያ ዕለት በተወጠረ ስብሰባ ተይዘው ቆይተው ወደ ማረፊያቸው ሲያመሩ የደርግ ሚግ 23 ድብለቅለቅ አርጋው ወደታች ብላ ወደላይ ስትመለስ የነበራት ድምጽ ሁሉንም መሬት ላይ አንከባሏቸው ነበር። መልስ እንደልማዱ በዛው ተኝቶ ቀረ ከዛም፥ ስዩም መስፍን” እረ ተነስ እንጅ ምንድነው ተጎዳህ እንዴ ሲለው” አጅሬው መለስም በማቃሰት ” ጭንቅላቴ ደህና ነው” ዳበስ ዳበስ እያደረገ ከዛም ቀጠል አድርጎ” አግሬ ተርፏል እንዴ?” ብሎ ሲጠይቅ በቃ ዙሪያውን ከበው ከት ከት ብለው ሲስቁ ምንም እንዳልሆነ አውቆ ብድግ አለ ” እንዲህ ነኝ እኔ ሰራውላችሁ “እያለ በቀልድ እንዳስመሰለ አርጎ አሳምኗቸው ልብሱን እያራገፈ ተነሳ። እንግዲህ የመለስ መሰሪ ባህሪ የሚባለው እንደዚህ እየሸወዳቸው ነው። ሚጓ ምንም ቦንብ ሳትጥል አስፈራርታ ብቻ ነበር የተመለሰችው።
መለስ ፈሪ 3. የአበበ ገላውን አልነግራችሁም። በሚቀጥለው ከፍርሃቱ የተነሳ ምን ምን እንዳደረገ በስፋት እመለስበታለሁ።
ተራ ካድሬዎች ግን ሰው እንዳይስቅባችሁ መለስን ጀግና አትበሉ እንኳን እናንተ ይቅርና ነባር ታጋዮች እንኳን ደፋርና ጀግና እንዳልሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ።
መለስ ፈሪ!!! በፍርሃት ኖሮ በፍርሃት የሞተ!!! – ተስፋዬ ገብረአብ