በቦረና ክልል በኖኖ-አሎ ቀበሌ በሚኖሩ ዜጎች ላይ ጥቃት ተፈጸመ ሲሉ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድን ሀላፊ ተናገሩ
በቦረና ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በኖኖ-አሎ ቀበሌ በሚኖሩ ዜጎች ላይ ባካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናትና ጥቂት ተባባሪዎቻቸው ብሄር-ተኮር ጥቃት ደርሶባቸዋል ሲል ሰ መ ጉ የተሰኘው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ገለጸ። ጥቃቱ ብሄር-ተኮር ይሁን እንጂ የብሄር ግጭት አይደለም ሲሉ የ ሰመጉ ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር ተናግረዋል። ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ዜጎች ከወከሏቸው መካከል፥ በዛሬው እለት ባካባቢው ፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውም ታውቋል። የአዲስ አበባው ዘጋብያችን መለስካቸው አመሃ ዝርዝር ዘገባውን ይዟል ያድምጡ።