ጐዳና የተገፉ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን

Limenih and Solomonአርአያ ተስፋማሪያም
[ፎቶ: ሰሎሞንና ልመንህ]

የዛሬ አመት አንድ አርቲስት እዚህ ዲሲ መጥቶ ሲያወራ « ከሌሊቱ 10 ሰዓት ቀረፃ አብረውኝ ያመሹትን ለማድረስ በሾላ መንገድ እያሽከረከርኩ ስጓዝ አካባቢው ጭር ብሎ ነበር። ሃይለኛ ዝናብ ይጥላል። በርቀት ዶፍ እየወረደበት በእግሩ የሚጓዝ ሰው ተመለከትኩ። ስንቀርብ ለካስ ልመንህ ታደሰ ነው» ሲል ከመሃከላችን አንዱ «እና ዝም ብለኸው ሄድክ?» አለ። «አዎ መንገዴን ቀጠልኩ» ርህራሄ የነጠፈበት የወዲ ጉግሳ ምላሽ ነበር። ሌላ የተናገረውን ባልደግመው ይሻላል። ኮሜዲያን ልመንህ ይህቺ ወረተኛ አለምና ህይወት ፊቷን ያዞረችበት አሳዛኝ ወገን የሚታደግ፣ ቢያንስ ፀበል እንኳ የሚወስድ ይጥፋ?.. ልመንህ በጤናው ሆኖ አገር ቤት ቢመጣ አጃቢው ይበዛ ነበር። በተመሳሳይ ለነፃው ፕሬስ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያበረከተው፣ በርካታ ድራማዎችን የፃፈው ጋዜጠኛና ደራሲ ሰሎሞን ሙሉ ታፈሰ ጊዮርጊስ ቤ/ር ጀርባ ጐዳና ማደርና መዋል ከጀመረ አመታት ተቆጠሩ። በዛ ላይ በኪንታሮት በሽታ ይሰቃያል። ረሃብ፣ በሽታና ስቃይ እንዲሁም ዝናብና ቁር ይፈራረቁበታል። በእሱ ጀርባ ተረማምደው ሚሊየነር የሆኑትና ለዚህ ያበቃቸው እነሰራዊት ፍቅሬና ሌሎች አይተው እንዳላዩት ያልፋሉ። ሰው ሲሞት አበባ ጉንጉን ለማስቀመጥና ታሪክ ለማነብነብ የሚቀድማቸው የለም። የጋሽ ተስፋዬ ለማ ውሳኔ መነሻው ይኸው መገፋት ነበር።

7 Comments on “ጐዳና የተገፉ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን”

  1. Tebaberene yemedenubetene menegede benefelege yemeshale yemeselegnale yesewe seme eyanesane kemenewekese

  2. አንዲት ኢትዮጵያ እያላችሁ ከሀኋላ እየዘመራችሁ የማገዳችሁት በሺዎች የሚቆጠር የቀድሞ ሠራዊት ጀግና አካሉን ገብሮ እጅ እግሩን አጥቶ ቁራሽ እንጀራ አጉራሽ አጥቶ ለመሥራት አካል አጥቶ መንገድ ላይ አንጥፎ ስለምን 24 አመት አለፈው ማንም ሳያየዉ። ለእናንተ ኢትዮጵያዊ አርቲሰት ብቻ ነዉ እንዴ? ስንቱ ኢትዮጵያዊ እምሮዉን ስቶ በየሜዳዉ አላያችሁም እነሱሰ ወገኖቻችን አይደሉምን? ስለሁከት አርቲስት ሰማይ ጥግ ማራገባችሁ ምንነዉ እየተሰተዋለ ቢሆን ደግ ነዉ

  3. How did he know that he is LIMENH. COUSE A PERSON who walk on the rain alwayes their head’s are down he didn’t even load he just pass and look the time and I neva see a creazy person(sory to say that but he is)walking on the rain so its too difficult to recognise some one who complletly changed person. Any way stay blessed

  4. ከዚህ ፅሁፍ የተረዳሁት ነገር ቢኖር፤ ፀሀፊው አጋጣሚውን ተጠቅሞ ምንም አላደረጉላቸውም ብሎ ያሰባቸውን ግለሰቦች መውቀስ ብቻ ነው። እሱንም ቢሆን በችግር ላይ ያሉትን ሰዎች ሳይጠቅስ በሌላ 100 ምክንያቶች ማድረግ ይችል ነበር። የእኔ ጥያቄ ለፀሀፊው የሚሆነው፤ እርስዎስ ምን አደረጉ? መቼም ወሬውን ፈልጎ ማቅረብ እንደሚቀል ተቸግረው ያሉት ሰዎችንም ማግኘት የሚቸግርዎት አይመስለኝም። የፈለገ ዶፍ ዝናብ እየወረደ እንኳን ቢሆን፤ ለመርዳት ከሆነ አይከብድም። እስኪህ መጀመሪያ እንረዳዳና፤ በኋላ እንወቃቀስ። አይመስልዎትም?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*