አቶ አንዳርጋቸው፣ ዩናይትድ ስቴትስና አውሮፓ – ዶይቸ ቬለ
የአሜሪካና የአውሮፓ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ መንግሥት ያሠራቸውን የተቃዋሚው የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ መሪ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን እንዲፈታ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ መላካቸው ተዘግቧል። ደብዳቤው የእንግሊዝ የአሜሪካና የአውሮፓ ፓርላማ እንደራሴዎች የፈረሙበትና አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲፈቱ የሚጠይቅ መሆኑን የአውሮፓ ህብረት ቃል አቀባይ ለዶቼቬለ አስታውቀዋል። አቶ አንዳርጋቸው ከየመን ተወስደው ኢትዮጵያ ውስጥ ከታሰሩ አንድ ዓመት አልፏቸዋል። ገበያው ንጉሴ ከብራስልስ ዘገባ አለው → Listen ↓↓↓