በወያኔ ለዲያስፖራ ሳምንት ከጎረቤት አገር የሄዱ ስደተኞች ለስለላ መመልመላቸውን ተናገሩ::(ምንሊክ ሳልሳዊ)

#Ethiopia ጥብቅ መረጃ :  በወያኔ ለዲያስፖራ ሳምንት ከጎረቤት አገር የሄዱ ስደተኞች ለስለላ መመልመላቸውን ተናገሩ::(ምንሊክ ሳልሳዊ)

የወያኔ ጁንታ የገባበትን አጣብቂኝ በደህንነት ሃይሎች አፈና እና ስለላ ለማስወገድ ጥረት ቢያደርግም እንደማይሳካለት ለዲያስፖራ ሳምንት ከጎረቤት አገሮች ወጪያቸው ተሸፍኖ የሄዱ እና ለስለላ ስራ የተመለመሉ ስደተኞች ጠቁመዋል::ከዚህ ቀደም በጎረቤት አገሮች ውስጥ የሚሰሩ የደህንነት አታቼዎች ለነዚሁ ለተመለመሉ በወያኔ የዲያስፖራ ሳምንት የተሳተፉ ስደተኞች ስልጠና እየሰጡ መሆኑ ታውቋል::ከዚሁ ጋር በተያያዘ በጎረብት አገር ኤምባሲዎች ውስጥ ቻይና ሰራች የስልክ ጠለፋ እና ስለላ መሳሪያዎች በድብቅ እንደሚተከሉ እና የኢትዮጵያውያንን ስልኮች ቁጥሮችን እና አይነቶችን ሰብስበው በምስጢር መረጃ የሚያቀብሉ ሰዎችም መዘጋጀታቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናግረዋል::

መሬት እና ጥቅማ ጥቅም ይሰጣል ሲባሉ እንዲሁም አገር ቤት መመለሻ ገንዘብ ያልነበራቸውን ሰዎች መዝግቦ እና ሰብስቦ ዲያስፖራ ናቸው በሚል ሽፋን አገር ቤት ወስዶ ሙሉ ልብስ በማልበስ ሲያስጨበጭባቸው የከረሙት የጎረቤት አገር ስደተኞች ለስለላ መመልመላቸው በሚኖሩብት ጎርበት አገሮች ውስጥ ለሶስተኛ አገር ጉዞ የጀመሩት የስደተኛ ፕሮሰስ እንዳይበላሽባቸው እና እንዳይጋልጡ ከፍተኛ ስጋት እንዳደረባቸው ታውቋል::

ለስለላ ስራ ከተመለመሉ የፎርጂድ ዲያስፖራ ስደተኞች ከሚያሰለጥኑት ውስጥ አንዱ አቶ መለስ ይባላል በኬንያ የደህንነት አታሼ ሆኖ የሚያገለግል እስከ አሁን ከኬንያ ታፍነው እየታገቱ ይወሰዱ የነበሩ ሰዎች በሱ ባሰማራቸው ሀይሎች ነበር በተጨማሪም በስደተኛው መሀል ያሉትን የያንዳንዱን ስደተኛ እንቅስቃሴ እየሰለሉ መረጃ የሚያቀብሉትን ሰዎች የሚያሰማራውና ቀጥታ ሪፖርታቸውንም የሚቀበል የነበረው እሱ ነው በኬንያ ስደተኞች መሀል መተማመን እንዳይኖር እርስ በእርስ እንዲጠራጠሩ የሚያስፈራራ መረጃ በስደተኛው መሀል ሲያሰራጭ የነበረ ነው በአሁን ሰዓት ይሄን ሲሰራ ቆይቶ ማስተርሱን እንደጨረሰ በሌላ ሰው እንዲተካ ተደርጎዋል ተወልዶ ያደገው አስመራ ውስጥ ሲሆን የትግራይ የአድዋ ሰው እንደሆነ ይነገራል ኬንያ ያለው ስደተኛ በጣም በፍርሃት እንዲኖር ሲያደርግ ነበር።የአይን እማኞች እንደሚሉት ሰዎችን እያስፈራራ ወደ አገርቤት እመልሳችኋለው እያለ ከፍተኛ ገንዘብ ከስደተኛው እየተቀበለ በገንዘቡም ማታ ማታ አበሻ ሬስቶራንት የተባለ ቤት ውስኪ ሲራጭ ያመሽ ነበር::

በጎረቤት አገሮች ያሉ ስደተኞች ከፍተና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የመከሩት በወያኔ የዲያስፖራ ሳምንት ላይ የሚሳተፉት እንዲሁም ለስለላ የተመለመሉ ወገኖች አገር ቤት ደርሰው የመጡ እና ብጥቅማ ጥቅም የተደለሉ ግለሰፖች ጥቃት እንዳያደርሱባቸው እንዲጠነቀቁ ምክራቸውን ልከዋል::ተሳታፊ ሆነው የሚገኙት እነዚሁ ስደተኞች በየቀኑ ከባድ የፖለቲካ ጥላቻ እንደሚሰበክ እና በብሄር በብሄር ቡድን እየተከፋፈሉ ከፍተኛ ዘረኝነት እና ጥላቻ እንደሚሰበኩ ተናግረዋል::እጅግ አስደንጋጭ መመሪያ ነው እየተሰጠው ያለው አገዛዙ ከባድ የሆነ አጣብቂኝ ውስጥ እንደሆነ ተሳታፊዎቹ ቴናግረውል::ይህንን ሰበካ የሚያደርጉት ሙሉ በሙሉ ትግሪኛ ተናጋሪ የሆኑ የሕወሓት አባላት እንደሆኑ ተናግረዋል የወያኔ ዲያስፖራ ሳምንት ተሳታፊዎች:: #ምንሊክሳልሳዊ