11 Comments on “የኢትዮጵያ ሕዝብ በጀግና መሪ እንጂ በድርጅት አምኖ አያውቅም!!”

  1. አቶ ይፍሩ ምን ማለትዎ ይህ ጽሁፎ እኮ በእኔ እይታ ባዶ ወረቀት ነው? ብርሃኑ ነጋ ኤርትራ ገባ ስለተባለ ብቻ ጀግና ነው የሚሉት በጣም ከእውነታው ጋር የተጣረሰ ነው። እስቲ ግንቦት ሰባት ከተመሠረት ጊዜ አንስቶ የሰራውን በዝርዝር ይግለጹልን። ወሬ ሌላ ስራ ሌላ። እርስዎ በግልዎ የመደገፍ መብትዎ ቢሆንም የምንቃወም ሰዎችም መብት እንዳለን እንዲያውቁልን ያስፈልጋል።

  2. Ferto yesheshe sew jegna eyalu metrat neshota enji tinegnanet aydelem. Eritriya begeba magist betekmat yemichemalk feri enji jegna aydelem. Minew yejegnochu simina sira tefabih endi? Jegnochun menak new birhanu negan jegna malet. Ahun eko ye Eroup mircha commition metl ende 1997 ayaterfewm nebsun. ETHIOPIA LEZELALEM TEKEBRA TINUR

  3. ሰበር ዜና:-ሸዋንግዛው ላለፉት 24 ዓመታት ሸዋን በማርከሱ(Markeshaw) ሸዋንቆጨው ተነሳ።

  4. .የአፍራሾች ዋይ ዋይታ (ደነባ ጉልላት)
    July 25, 2015

    ደነባ ጉልላት

    ስንሰማ የነበረው ወያኔን በትጥቅ ትግል የሚፋለም ጠፋ ነበር ። ስንሰማ የነበረው የሕዝባዊ ሀይሉ መሪ ዶክተር ብርሃኑ በግንባር አልተገኙም የሚለውን ነበር ። ሁለቱም ቅሬታ ሲወገድ ግን ዋይ ዋይታና ኡ ኡታ የሚያሰሙ ከየስርቻው ብቅ አሉ ።

    ከማንም በፊት ወደ ሻዕቢያ ሂዶ የነበረው ኤልያስ ክፍሌ የዚሁ ፊታውራሪ ሆኖ ብቅ አለ ። ወዳጅ ሲለው የነብረውን ሻዕቢያን ጠላት ብሎ ሰይሞ ተጀመረ የተባለውን የትጥቅ ፍልሚያ ሀሰት ሲል ኮነነ ። ሕዝባዊ ሀይሉን ቁጥር ከ ፲ ወደ መቶ ቢያደርሰውም የትም አልተንቀሳቀስም ብሎ አስተባበለ ።ይኽው ግለሰብ ግን የዴምህት ሀይል በኤርትራ ፵ ሺ ደርሷል ይለናል ። ለዚህ ያህል የማይንቀሳቀስ ጦር ምን ያህል ወጪ ይጠይቃልን አላሰበበትም ።ኢሳያስም የሌላ ህገር ዜጎች ያሉበት ይህን ያህል ጦር ማስተናገድስ ለደህንነቱ ይበጀዋል? ምን ገዶት ለኤልያስ!የኢትዮጵያ ረቪው የኢንተሊጀንስ ክፍል ባገኘው መረጃ መሰረት እያለ ውሸት መጠረቅ ልምዱ ነው ። ኤርትራና ሻዕቢያ ጠላት ከሆኑን ኢሳያስን የዓመቱ የኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ያለ ኤልያስ ሊወገዝ የሚገባው ይሆናል ። ኾለኔል ፍጹም ያን ሁሉ ወጣት ከረሸነ ለምን ይህንን ለማጋለጥ ዓመታት ፈጀበት ብንል መልሱ ራሱ ጠቋሚ ነው ።ኤልያስ ክፍሌ ለመሆኑ አለሁ አለሁ ማለት ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ የማንን አጀንዳ ነው በስራ ላይ እያዋለ ያለው ጥያቄ እንዳለ ሆኖ ዋናው ተል እኮእ ግን አርበኛ ሀይሉን/ታጋዮችን መበጥበጠ መሆኑን ታሪኩ ይመስክራል ።

    ሌላው ዋይ ዋይታ አሰሚ አቶ መልኬ ሲሆኑ ወደ ኤርትራ የዘለቁት በዚያ ዋሾና ተራ ሌባ አብርሃም ያዬህ ተወስደው ነውና ያጋጠማቸው መጥፎ ተመክሮ ካለ ቅሬታቸው ቢገባንም ስለ አርበኞች ግንባር ያላቸው ዕውቀት ግን ጊዜ ያለፈበት መሆኑ የሚታይ ነው ። ደምስ የሚባለው በበኩሉ የመኢሶን ገራፊነት ታሪኩን እያነሱ ቀልቡን የሚገፉት እንዳሉ ሲታወቅ እሱም ቢሆን አርበኞች ግንባርን ደጋፊ መስሎ በተደጋጋሚ ወደ ኤርትራ የዘለቀ ነው ።ለምን መሄድ እንዳቆመ ኮለኔል ፍጹምን መጠይቅ አንገደድም —እናውቀዋለን ምክንያቱንና ነው ። እስካዛሬ ድምጹን አጥፍቶ ተደብቆ ከርሞ አሁን በግንቦት ፯ና አርበኞች ግንባር ላይ ምን አስነሳው ? በሻዕቢያም ሆነ በአርበኞች ግንባር መሪዎች ግፍ ተፈጸመ ካለስ ለምን እስካሁን ዝምታን መረጠ ብለን ስንጠይቅ የምናገኘው መልስ ግልጽ ያደርጋል የእሱን አፍራሽ ተልእኮ ።

    ከድረ ገጾች ደግሞ ያ የለመደበትን ኢትዮፓትርዮት የተባለውን የትምክሀት ገጽ ወደ ጎን ስንተው የኢትዮሚዲያው አብርሃም በላይና የዘሃበሻም አዘጋጅ ና ጋዜጠኛ በሉን ባዩን አበበ በለውን አጅበው በጸረ ሻዕቢያ ሰበብ ሕዝባዊ ሀይሉ ላይ ተነስተዋል ። ወያኔን የሚያስደስት ጸረ ሕዝባዊ ሀይልና ጸረ ዶክተር ብርሃኑ ዘመቻ በግልጽም በረቀቀ መንገድም እያካሄዱ መሆናቸውን ሀገር ወዳዶች ያጋለጡት ጉዳይ ነው ።ከኢትዮፓትርዮት እየለቀሙ ጸረ ሕዝባዊ ሀይል ጽሁፎችን የሚለጥፉት አሲምባ አዘጋጆች ደግም ጸረ ግንቦት 7 አቅዋማቸውን ማሰማት ከጀመሩ ውሎ አድሯል ። የፓል ቶኩ እንደራሴ (ተስፉ ፡ስድስት“) አዲስ አቅዋም አልያዘም—ጸረ ግንቦትነቱ የታወቀ ነውን ። የዚህ አፍራሽ ስብስብ ማዕክል ግልጽ ሆኖ ባይመጣም ወይም አንድ ሆኖ ላይገኝ ቢችልም ስራቸው ግን የተጀመረውን ትግል በርታ በርቱ በማለት ፈንታ ማፋለስ ሆኖ ይገኛል ።ከዚህስ ማን ይጠቀማል ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል ። ተጠቃሚው ወያኔ መሆኑ ግልጽ ነው ። መፍረክረክ ሲጀምር አይዞህ ባዮች ስለሆኑለት ባይወዳቸውም ሊያመስግናቸው ይችላል ። አንዳንዶቹም በቀጥታ ከእሱ ጋር ንክኪ የላቸውም ማለት አንችልም ። እነ አበብ በለው ወያኔ ወያኔ መሽተት ከጀመሩ ዓመታት አልፈዋል ።

    ትጥቅ ትግሉ ተጀምሯል ። ያለውን አደጋ አይተው ሸብረክ ሳይሉ መሪዎቹ ወደ አስመራ አቅንተዋል ። ትግሉን በቦታው ሆነን እንመራለንም ብለዋል ። አንመለስም እስከ ድል ድረስ ብለዋል የሚለውን ግን ካፋቸው ስላልሰማሁ ማረጋጋጥ አልችልም ። ብለዋል ባዮቹ አንዳንዶቹ ምን ሞቲቭ እንዳላቸውም የሚሳት አይደለም ። ሕዝባዊ ሀይል የጀመረውን ትግል በርታ ግፋበት ሊባል ይገባዋል ። ዶክተር ብርሃኑ ውድቀታችንን ትሰማላችሁ፤ ስንነሳም ትሰማላችሁ እንዳሉት ሁሉ በዚህ መንፈስ የትግሉን ሂደት መጠበቅ መልካም ይሆናል ። ድጋፍ እየሰጠናቸው መሆኑ አስፈላጊ ነው ። ከዚህ ቀደም በጄኔራል ሃይሌ መለስ፤ በኢአግ፤ወዘተ የተደረጉ የትጥቅ ትግል ሙከራዎችን በበቂ ባንደግፋቸውም ውድቀታቸውን አልተመኘንም ። የረዱም ጥቂቶች አልነበሩም ። የሕዝባዊ ጥሪ እንደሚወገዘው በነዚህ አፍራሾች ያልተደረገ ከሆነ በአጭር ጊዜ መታወቁ አይቀርም ።እየተካሄደ ካለም (እኔ ነው ብዬ አምናለሁ) ደግሞ አፍራሾቹ ያፍራሉ ። እነ ኤልያስ፤አብርሃም፤ዘ ሀበሻ፤አበበ በለውና መሰሎቻቸው ላይም ማዕቀብ ያስፈልጋል ።

    አፍራሾች ይፈርሳሉ !!

    ድል ለሕዝብ !!

    ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ በኢትዮጵያ ከረንት አፊርስ ተቋም በግንቦት 22 ቀን 2009 በሰጠው ቃለ ምልልስ „ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከዳኛ ብረቱካን ይብልጣሉ! ብርቱካን ምን አላት¡ ቦንብ የላትም፤ ፕሬዚዳንቱ ግን ቦንብ አላቸው“

    ውሻ ጮኸ ተብሎ ድንጋይ አይወረወርም
    July 22, 2015

    ቹቸቤ ነኝ አማን ነው? የሰሞኑን ነገር ለመግለጥ የሚሆን መንደርደርያ ፍለጋ ስባጅ ቆየሁ። ዛሬ ሁሉም ተናጋሪ ቢሆንም የነገር ድግግሞሽ አታክቶናል። ገና የተተነፈሰው እንደሰሚው ተወላግዶ ወይም ጣፍጦ የበሬ ግንባር በምታክለው ፌስ ቡክ ይለጠፋል። ወሬ ብርቅ አይደለም። እንዲያውም በርካታ ተግባር አልባ የወሬ ቤቶች ተከፍተው ወሬ ሲወቁ ነገር ሲሰልቁ ቡና ቤት መለወጥ እንደሚወድ ጠጪ ከአንዱ ፓልቶክ ወደ ሌላው እየዞሩ በጉንጭ አልፋ ፍሬከርስኪ የሚያደነቁሩን አውርቶ አደሮች በዝተውብናል። ከሁሉ የሚያሳዝነው ደግሞ ከፈር ቀዳጅ ታጋዮቹ መንደር ነበርንና አንቱ በሉን የሚሉ እድሜ ጠገቦቹ ከተማሪ ረብሻ ወዲህ አርባ አመት ያስቆጥሩም ቢሆን ዛሬም እንኳ የአስተሳሰብ ጨቅላነታቸውን አለመጨረሳቸውና አሁንም በረብሻ መተዳደርን የመረጡ በሚያስመስል አፍራሽ ተግባር ተጠምደው ማየታችን ነው።

    በእድሜ ዘመናቸው አንድም ሚዛን የሚደፋ ቁምነገር ሰርተው አያውቁም። በተለይ ደግሞ ወያኔ ወደስልጣን ከመጣ በሁዋላ ከኛ በላይ የወያኔ ተቃዋሚ ለአሳር እያሉ ሽንጣቸውን ገትረው የሚውረገረጉም ቢሆን የዚህን አረመኔ ወያኔ እድሜ የሚያረዝም እንጂ የሚያሳጥር ምንም ሰርተው አያውቁም። እንዲያውም ከእድር ለየት ባለ የፖለቲካ ቡድንነት የተሰባሰቡ መሆናችው ትዝ የሚላችውና ነገር ጣል ለማደረግ የሚባንኑት ሌላው ወገን የሰራው ነገር መኖሩን ሲሰሙ ነው። ያኔ አይናቸው ደም ይለብሳል እንደ ወያኔ ተለጣፊ ወይም ተመሳሳይ ነገር ሰርተው የተሰራውን ለማፍረስ ይጣደፋሉ። ገና አልባነነ ይሆናል እንጂ ጋዜጠኛውም ከፍርስራሾቹ አንዱን እየሆነ ነው። እንዲያውም ቆመጥ አድርገውት የራሱን ኢሳትን ይደበድቡበታል። እርሱም ዝናዬን ቀሙኝ ኩርፊያ የያዘ ይመስል አጓጉል መሄዱን መርጧል። ብቻ አጎቶቻችን ለማፍረስ ሲሆን እንደ ተኩላ ናቸው በጩኸት ይጠራራሉ ሳይነጋገሩ ይግባባሉ። ድርጅት በአይነት በአይነት ያቋቁሙና የመጥለፍ ጥማታቸውን ለጊዜውም ቢሆን ያረካሉ። የጀመሩትን ከምን እንዳደረሱት የሚጠይቅ ስለሌለ አዲስ ባቆሙት ላይ ያወራሉ። ትግል የሚለውን ቃል በግርድፉ እንዲያው ቃል በቃል ወስደው ነው መሰል አድማ እየመቱ ከሁሉም ሲታገሉና ሲያፈርሱ እድሜ ራሱ አፈራርሶ ሊጨርሳቸው ነው።

    በመጨረሻ አንደርዳሪ ብልጥ ሃሳብ አገኘሁ እነሆ የብልህ ሰዎች ማህደር ከዊንስተን ቸርችል አባባል ላይ ወስዶ የለጠፈው ቃል ማረከኝ። “ውሻ በጮኸብህ ቁጥር ድንጋይ እያነሳህ የምትወረውር ከሆነ ካሰብክበት አትደርስም” የሚል ነው። አዎ ሩቅ ለመሄድ አልመው ድንጋይ ወርዋሪና ማዶ ለማዶ ቆሞ ተሳዳቢነትን የመረጡ ያሰቡበት አይደርሱም። ሰሞኑን የሚነፍሰው ንፋስ ግምኛ ነው ይሰነፍጣል። በርግጥ እነዚህ ሰዎች ነጻነትን ይፈልጋሉ ወይንስ እኛ ካላረግነው ሁሉም አፈር ይብላው የሚሉ ናቸው? እውን እነዚህ ሰዎች ለአፍራሽ ተልዕኮ የሚሰጣቸው ፍርፋሪ ኖሮ ነው ወይንስ ኑሮአቸው ይኸው ግርግር የመፍጠር ሆኖ ነው? ያስብላል። በተለይ የተማሩትና የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል እያሉ የሚጽፉት ምሁራኖች እነሱ ባሉብት መድረክ ላይ በጠንካራ ታጋዮችና መሪ ድርጅቶች ላይ ተራ ስድብ ሲደረደርና ትግሉን የሚጎዳ ግርድፍ ሀሳብ ሲዥጎዶጎድ በዝምታ ማለፋቸው ምን ይባላል? እኔን አንቱ እስካላችሁኝ ድረስ ሌላውን ድባቅ ብታስገቡትና ትግሉን ብትጎዱት እኔ ምን ገዶኝ ብለዋል ማለት ነው? ይሄ ከሆነ ስሌቱ ፍላጎታቸው መድረክ ላይ መኮፈስ እንጂ ሀገርን ማዳን አይደለም ብለን እኛም ለእንደዚህ አይነቶቹ የሚቸረውን አክብሮት እንሰጣቸዋለን።

    በተግባራዊ ትግል የተጠመደው ወገን ደግሞ እነ ሰው ከንቱን ቁም ነገር አድርጎ አቧራ ማጨሱን ተወት አድርጎ ጊዜውን ተግባራዊው ትግል በሚፈልገው እንቅስቃሴ ላይ ቢያተርኩር ይሻላል። የእነኚህ አፍራሽ ወሬኞች ፋይል መዘጋት አለበት። እነርሱን ሰምቶ ከመንጫጫት ከግንቦት ሰባት አመራር ተምረን ለወሬኞች የምናባክነው ሰአት የለንም ብለን ወደተግባሩ እንመለስ። የግንቦት ሰባት አመራሮች ለርካሽና ተልካሻ ነገር መልስ ለመስጠት ደፋ ቀና ሲሉ አናያቸውም። ስራው ላይ በማተኮራቸው የእምነት ጽናትም በማሳየታቸው መሬት ላይ የሚታይ ስራ እየሰሩ ነው። ‘በርገር’ እየበሉ ግፋ በለው ብቻ እንደማይሉ ደግሞ በተግባርም እያሳዩ ነው። የሚበልጠው ለእናት ሀገር ለመዋደቅ የቆረጡ ወጣቶችንና አርበኞችን መደገፍና ትግሉን ማፋፋም ወይንስ የአሽሙር ጧፍ እያበሩ የእርግማን አዝማች ያለው የስድብ መዝሙር መዘመር?

    ምርጫችንን ልናውቅ ልንበስልና ልንበቃ የሚገባን ጊዜ ላይ ነንና ከአመት አመት ራሳችንን እዚያው የነበርንበት ላይ ማግኘት ደካማ አቅማችንን ፀሀይ ማስሞቅ ይሆናል። ለዚህ ነው እነ ስም አይጠሬን ከቁም ነገር መድረክ ላይ ቆልለን በጮሁ መጠን ቃላት የምንወራወር ከሆነ መቼም ቢሆን ካሰብንበት አንደርስም ለማለት የወደድኩት። እንዲያውም ተጋብቶብን ቀንደኛ ተሳዳቢና አለክላኪ ተጓዥ ሆነን እርስበርስ የመነካከስ ባህርያትንም እየወረስን ነውና እነሱን ከመሆን ያድነን እንበልና ወደፊት እንገስግስ። ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር የሚል መፈክር ትዝ የሚለው ማነው? አዎ ያኔ ያለቀ ቢሆን ዛሬን ባልዘመትን ነበር።
    ድል የማይቀር እውነት ነውና ዱር ቤቴ ላሉት ደጀን መሆን ምርጫችን ይሁን!

  5. The people in main land Ethiopia are with the fight for freedom and I also believe the majority of us in the diaspora are falling in line with that.Quite a few of you are making noises like that. Probably 10 of you max. that is like a drop in a bucket …not something to be worried about.
    If you guys were serious about any the issue at all, you should have come and confront Andargachew and Dr Berhanu on the meeting that was held in DC more than approximately a year ago. That meeting was open for any one including Derg journalists like you.You failed to show up on that meeting and it was good opportunity to voice your concern if you had any in front of the public. You and guys like you blew it. You failed to learn from this free country you lived in for over 20 years. The media or journalists in this country never miss an opportunity like that because they want to get the truth out to the people.
    ፍሬከርስኪ አውርቶ አደሮች (pathological liars) like you missed one and only one opportunity. I am dead sure you guys don’t dare to show up even if you get another chance again. Because you know that you will certainly lose. You and your peers never had any concrete evidence to support your daily non sense on your website , pal talk, radio or what ever….Nothing to expect from some of you who were active during the Derg era or from those who were double agents between Derg-EPRP like Aba Mela. People reached guilty verdict on you guys any way. 1) Guilty for lying 2)for collecting money for at least 18 years and used it for your personal gain.Collected it on behalf of our people back home and here in the diasporay 3) Guilty for trying to weaken our new resolve to fight for freedom.Guilty on all three counts.That is why ESAT and Arbegnoch G7 is getting all the attention it deserves.You and your peers better honestly apologize and move on or you will be persona non grata post woyane.

  6. አቶ ይፍሩ እንደሚያውቁት ምዕራባውያን ሐገር እየኖርን እኔ ያልኩት ብቻ ካልሆነ ማለት ዲሞክራሲ እያሉ ያቀመሱን ነገር አለና ብንተወው ይበጃል። መድህን ውስጥ ወያኔዋች ተሠግስገው ኮሎኔል ጎሹን አላሰራ ስላሉት ፖለቴካውን እርግፍ አርጎ ተወው ያሉት በዚያን ግዜ ወያኔ እንደው ከየት ተገፕ? ትንሽ ስላልገባኝ ኮሎኔሉ እናም ሌሎችም አባሎች በህይወት ስላሉ ታሪካቸው እንዳይበላሽ ከያሉበት ወጥተው እርምት እንዲሰጡ በአክብሮት እንጠይቃለን። አቶ ይፍሩ አፄ ኃይለስላሴን በማይጨው ሰበብ ጥላሸት መቀባት ይቀልዎት ይሆናል ግና ጦር ሜዳ መሄድ ቃላት መደርደርና ግጥም ጣጥፎ የአንባቢ ያለህ ማለትም አይደል። አፄ ኃይለሥላሤ እዩኝ እዩኝ ባይ ያልነበሩ፣ በዘመናቸው ለሐገራቸውና ለሕዝባቸው በአቅማቸውና በዘመኑ ከነበረባቸው ትንንቅ አኳያ አየር መንገድን፤ አየር ኃይልን ፤ባሕር ኃይልን ፤ ዩንቨርስቲ በመክፈት እነ ፀኃፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ኅብተወልድን የመሰሉ ሰዎችን አፍርተው አልፈዋል። ወንድማችን ደሞ ብዙ ከመጫር ይልቅ *ተከተል አለቃህን * ብለዋልና ዶክተር ብርሃኑ ብዙ ርቀው ሳይቀምዎት ወደ አሥመራ መጓዝ ነው ምን ችግር አለ? እውነት ሁሉንም ነፃ ታወጣለች። ሽልም ከሆነ ይወለዳል ፣ እህልም ከሆነ ይወጣል ይባል የለ? እናያለን።

  7. “ተከተል አለቃህን” የሚል አባባል በዚህ ባለንበት ዘመን ሲነገር ስሰማ እጅግ ይሰቀጥጠኛል። ይህን ፅሁፍ ያዘጋጁ ሰው አትጠይቁ ጀሌ ሁኑ ተነዱ የሚል መልእክት አስተላልፈዋል። ምን አይነት መደዴና ገለባ ሰው ናቸው?

  8. What is this article about? At one point the writer talks about how Dr Berihanu is his hero on the other side he is telling us gossip, how Dr Berihanu doesn’t like Amara and how he is a coward. This is unnecessary.

  9. Solomon:
    I commend you for your interest in reading about your country. I thought my piece was written in clear and precise manner.there was nothing that contradicts my position and my opinion on Dr. Berhanu Nega.I put all the facts,reservations and concerns posed by others including myself. Please go back to the article and revisit its contents in its entirety.
    Thank you again.

  10. የኔ መልስ ለአቶ ዳሩ ለጽሑፌ በሰጡት ትችት ፤
    እንደ የግል ግዳጄ አድርጌ የምወስደው ለራሴ የደነገግሁት ሕግ አለኝ፤ ይኸውም “ ትክክል ነው፤ አምንበታለሁ፤ብዬ በወረቀት አስፍሬ ለንባብ በማበቃቸው፡ጽሁፎቼ ላይ በሚሰጡት የድጋፍም ሆነ የነቀፌታ አስተያይቶች ላይ ምንም ዓይነት መልስ ለመስጠትና ከማይረባ “እሰጥ አገባና” ንትርክ ዉስጥ ላለመጋብት የወሰድኩት እርምጃ ነበር። ግን የወገኔ የ አቶ ዳሩ ትችት ባነሷቸው ነጥቦች ላይ ማብራሪያ ለመስጠት ሳልወድ በግ ተገድጃለሁ።
    አንደኛ/ “ የንጉሠ ንገሥቱን ስም ጥላሸት ቀብተሃል፤ ለኢትዮጵያ የዋሉትን ዉለታ ዋጋ ቢስ አድርገኸዋል” በንጉሠነገሥቱ ዘመነ መንግሥት የተወሰዱትን ዕርምጃዎችና ክንውኖች፤ እንደዚሁ በዘማናቸው ለበቀሉት ግሩም ድንቅ ምሑር ኢትዮጵያውያንን ያነሱና በዋና ምሳሌነት ክቡር ጸሓፊ ተእዛዝ አክሊሉ ኃብተወልድን ያስቀምጣሉ። እኔ በዚህ ላይ ምንም ችግር የለኝም። እንዲያው ወገኔ ሳያውቁኝና ሳይረዱኝ ቀርተው እንጂ፤ ከኔም ሌላ ለንጉሠ ነግሥቱ በዚህ ላይ ሽንጡን ገትሮ፤ በስማቸው እየማለ፤ከሚከራክሩላቸው አንዱ መሆኔን ሳይገነዘቡልኝ በመቅረታቸው፤ ከንፍሬን ከመምጠጥና “አዬ ጉድ” ከማለት ሌላ ምንም ልላቸው አልችልም። የጠቅላይ ምኒስትሩን ታላቅ ምሑርነትና አስተዋይነት ከተነሳ ዘንዳ እባክዎ ቢቻለዎት የምባሳደር ዘውዴ ረታን “ የኤርትራ ጉዳይ” የምትባለውን መጽሓፋቸውንና በኢትዮጵያ ወዳጅ የፕሮፌሰር ጆን ኤች ስፐንሰር ን “ኢትዮፕያ አት ቤይ” የተሰኘውን መጽሃፍት ያንቡቡና በኢትዮጵያ ዋና ዋና የመንግሥት ጉዳዮች ላይ ማን መምህር? ማን ደቀ መዝሙር? እንደነበረ ይንገሩኝ። ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ፤ በአቶ መዝገቡ ምትኬና በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም (የፕሬዚደንት መንግሥቱ ኃይለማርያም የስም ሞግሼ) “ጥርስ የገባች አገር” በሚል ረእስ የተተረጎመ ድንቅ መጽሓፍ ስለአለ እሱንም ይቃኙት።
    እኔ ያልኩት የማይጮው ጦርነት ያለቅንበት እንጂ የጨረስንበት(ጠላትን የፈጀንበት)፤ የተሸነፍንበት እንጂ ድል የመታንበት አለመሆኑና ንጉሠ ንገሥቱ ወደ እንግሊዝ አገር ሲሄዱ ከአርበኞቻቸው አንዱን ጠርተው “ጀግኖች አሰባስበህ አግርህን ተከላክል፤ እኛም በዲፕሎማሲው በኩል የምንችለውን እናደርጋለን….” ብለው አደራ የተጣለበት ሰው ነበርወይ? ብዬ ጠየቅሁ እንጂ ሌላ ያልኩት የለም። አርበኞችን “ተከተሉኝ” ብለው ብዙዎችን መጠየቃቸው የማይካድ ሃቅ ነው።
    ሁለተኛ/ “ መድኅን ሲመሠረት ወያኔ አልነበረም” ላሉት እነአቶ ዮሰፍ መርሻ የነበሩበትን (ኢዲሕቅ..?) የተባለ ድርጅትን የአቋቋምነው ወያኔን ለመቋቋምና ብሎም በሱ ምትክ ሌላ መፍትሔ ለፈለግ መሆኑን እንዴት እንደዘንጉት አልግባኝም። “የወያኔ ሠርጎገቦች ያልከው እነማንን ነው?” ለሚለው ጥያቄዎ እባክዎ እነ ዶክተር ፍስሃ ጽዮን መንግሥቱንና መሰሎቻቸውን የማግኘት ዕድል ካለዎት እነርሱን ይጠይቁልኝ። በተረፈ ኮሎኔል ጎሹን ብቃትቸውንና በጊዜው የነበረውን ፈተና ለመቋቋም በብዙዎችና በኔ ግምት የሚያሟሉ ሆነው አግኝተናቸው ነበር። ደካማ ጎን የሌላቸው ፍጹም አድርጌ ያቀረብኳቸው መስሎ ከታየዎት ይቅርታዎን እጠይቃለሁ። ግን እኔ እንደ አንድ ግለሰብ ኮሎኔሉን የመደገፍም ሆነ የመቃወም መብት እንዳለኝ የረዱልኝ።
    ሦስተኛ/ “ ግጥም እየሞነጫጨርክ የአንባቢ ያለህ እያልክ ትጮሃለህ” ላሉት በዕውነት እለዎታለሁ እኔ ጊዜው የጣለብኝን ቁጭት፤ፈተናና ብሶት የምገልጽበት ዘዴ{መንገዴ} ነው እንጂ ሰው ያነብልኛል ብዬ ለንግድ የማቀርበው አይደለም። ይስሙኝ ጌታዬ አንድ ጥልቅ የሆነ የብልሖች አነጋገር አለ እንዲህ የሚል” መከራና ችግር ብልሃትና ድፍረትን ይፈጥራሉ “ ይባላል። በመከራና በችግር ጊዜ ፤ሙዚቀኛው በእንጉርጉሮው፤ ሠአሊው በሠዕሉ፤ ብሶቱን የሚገልጹና የሚያብራሩ መልክቶቹን ያስተላልፋል። አንዳንዱ የአልታደለ ደግሞ ችግሩን ለመወጣት በመጠጣት፤ የተለያዩ እሥዋትን በማጤስ፤ ችግሩን በዚያ ጥላ ስር ሆኖ ለማሳለፍ የሚሞክር አለ። አንዳንዱ ደግሞ የናቱ ልጅ መሣርያውን አንስቶ፤ ጫካ ገብቶ ጥይት እየተኮሰ፤ በባሩዱ ሽታ እየረካ፤ አውሬ እየገደለ፤”እንዲህ ይሠራል እኔ የአባቴ ልጅ!!” ይላል። የኔ ብጤ ደግሞ ባለችኝ አቅሜ፤ በምችለው መንገድ፤ የራሴን ቁጭት የምግልጸው በወረቅት ላይ ጭሮ በማስቀመጥ ነው። የሚገርመዎት እንዲያው እርሰዎን ሳልታደልዎት ቀርቼ እንጂ ብዙዎች ፤ ከተለያየ ቦታ እየጻፉ “የልባችንን ትርታ አሳምረህ ስለጻፍክ እናመሰግናለን “ ብለው አቆላምጠው የሚያሞግሱኝም ሞልተዋል። እንግዲህ ጌታዬ “ሸማ በፈርጁ ይለበሳልና” በሚቀጥለው ጊዜ የኔን ጽሑፍ ሲያዩ ዝም በለው አረም ጭነውበት ይለፉት።
    አራተኛ/ “ እንደ ብርሃኑ ወደ ኤርትራ ገስግስ” ያሉት በጣም ጥሩ ሃሳብ ነበር። አልተገነዘቡልኝም እንጂ ለእኔ እኮ ሻቢያም ወያኔም አንድ ስለሆኑ በማያሻማ ቋንቋ አቋሜን ግልጬ ደጋግሜ ጽፌአለሁ። አሁን በጀብደኝነት ወደ ኤርትራ ብጓዝ አንድ ጥይት ሳልተኩስ በውነት እለዎታለሁ፤ ሻቢያ በጨጓራዬ ይቆርብበታል። እርስዎ የሚያውቁት ሌላ አማራጭ መንገድ ካሳዩኝ ሳልውል ሳላድር፤ የዓመት ስንቄን ሙሉ ትጥቄን ችዬ ነገ እነ ብርሃኑን ለመቀላቀል ዝግጁ ነኝ። በዚህ እንደማላስፍረዎት ቃል እገባለሁ። በነገራችን ላይ ግጥም መሞነጫጨር ብቻ ሳይሆን ብዙ ማድረግ የምችለው ሞልቷል። በዚህሞ የነዋይ ፍቅር የለኝም። ሁሉንም አራግፌው ለመሄድ ዝግጁ ነኝ።
    ጌታዬ አቶ ዳሩ ድርጅት ስናቋቁም ፤ ድርጅት ስናፈርስ፤ “መምራት እችላለሁ፤ ተከተሉኝ፤ ደግፉኝ” የሚለንን ሁሉ ሽንጣችንን ገትረን ያንን ድርጂትና ያንን ግለስብ የመቃወም አባዜ እየተጠናወተን ስለመጣ ይህ መጥፎ ልማድ መቅረትና አንድ ቦታ ላይ መቆም አለበት።ያለበለዚያ “እኔ ካልመራሁት፤ እኔ ሃሳቡን ካለፈለቅሁት ፉርሽ ነው” ማለቱን እናቁም። ወያኔ ያለ ትጥቅ ትግል ይወገዳል ማለት ዘበት ነው። ጊዜም ማጥፋትን የወገንን ስቃይ ማራዘም ነው። እስኪ በሰከነና እረጋ ባለ መንፈስ የነብርሃኑን መጨረሻ፤የምንችለውን እያደረግንላቸው የት እደሚያደርሱን እንመልከት። መርዳት ባንችል ማደናቀፍን እናቁም። እኔ ለኢትጵያ ብሎ የሚታገልን ማንኛውንም ድርጅት አቅሜ በሚፈቅደው ሁሉ ከመርዳት አልቆጠብም። አንድ ከፈረጆች የታዘብኩትን አባባል ላካፍለዎትና ጽሁፌን እደመድማለሁ።
    ፈረንጆች አንድ ለማከናወን በሚሞክሩት ፕሮጀክት ላይ አንድ አፈንጋጭ ይነሳና ያፕሮጀክት እንዴት እንደማሳካ፤ የሚአጋጥመውንም ችግር እየዘረዘረ መቃወም ይጀምራል። አለቆቹም “እኛ ሁሉንም እንቅፋትና ችግር በየአቅጣጫው ተምልክተነዋል፤ ለዚያም መፍተሔውን አዘጋግተናል፤ ስለዚህ በዚህ አትጨነቅ ብቻ አንተ ሙሉ ድጋፍህንና ትብብርህን ስጠን።” ይሉታል። አሁንም ይህ ግትር በአቋሙ ይጸናና “አልተባበርም ፤ እንደሚወድቅ አውቃለሁ!” ይላቸዋል። በዚህን ጊዜ ይህን ሰው ላንድና ለመጨረሻ ጊዜ “ አዳምጥ ምራን፤ተከተል፤ ወይም ከዚህ ጥፋ!!” ብለው ያሰናብቱታል።( Lead, folloe or get the hell out of here”) ጊታዬ መደገፍ ካቻልን ማደናቀፉን እናቁም።” If you are not part of the solution, then you are part of the problem” Eldridge Cleaver on Soul On Ice. የሚለውን የ ኤልድሪጅ ክሊቨርን ጥቅስ ላስታዉእስዎ? ስለ እርሰዎ አላውቅም እኔ በወያኔ መረገጥ፤ መቀጥቀጥ ፤መሰደድ፤መንገላታት መሮኛል።ልክ የዛሬ ዓመት እናቴ ከዚህ ዓለም በሞት ስትለይ አገሬ ገብቼ እናቴን መሰናበት ያልቻልኩ ሰው ነኝ። ዛሬ ደግሞ ልክ በዓመቱ ታላቅ ወንድሜን ተረድቼ በሃዘን ላይ እያለሁ ነው ይህን የምጽፍልዎት። እኔ በመሰለኝ መንገድ ጠላቴን ልፋለመው። በወያኔና በኔ መሃል አይግቡ።
    በአክብሮት፤
    ይፍሩ ኃይሉ፤

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*