ሕወሓት ለቀድሞ የኢሕዴን ታጋዮች የድረሱልኝ ጥሪ ማድረጉን ቀጥሏል::
ምንሊክ ሳልሳዊ :- ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በተለያዩ የሃገሪት ክፍሎች የተነሱበትን ሕዝባዊ አመጾች ለመቆጣጠር ካለመቻሉም በላይ በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ ያለው እምነት የተሟጠጠ በመሆኑ በሰራዊቱ ውስጥ ያለው አለመተማመን በስፋት በመንገሱ እንዲሁም በተጨማሪ የተሰናበቱ የኢሕዴን ታጋዮች በውስጣቸው ያመቁትን ብሶት እና ቂም ይዘው የትጥቅ ትግሉን በመደገፍ ከተቃዋሚ ሃይሎች ጋር ሊቀላቀሉ ይችላሉ በሚል ጥርጣሬ የተሰናበቱበትን ማስረጃ በመያዝ ቀርበው እንዲመዘገቡ ጥሪ ማቅረቡ ታውቋል::
ሕወሓት ያቀረበው የድረሱልኝ ተሰብሰቡ ተመዝገቡ ጥሪ ስርአቱ ምን ያህል እንደበሰበስ በገሃይ የሚያሳይ መሆኑን እና ለተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬን እንደሚያላብስ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል::ከሃምሌ 2007 መጀመሪያ ጀምሮ የተደረገው ጥሪ በስርአቱ ላይ በለውጥ ሃይሎች እየደረሰ ያለው ጫና እና የትግል ስኬት የሚያሳይ አንድ እርምጃ መሆኑንየተሰበሰቡ አስተያየቶች ጠቁመዋል::ይህ ጥሪ ባለፉት 3 ወራት በትግራይ ለሚኖሩ የሕወሓት የወድሞ ታጋዮች በተደጋጋሚ እየቀረበ እንዳለ ታውቋል::ለቀድሞ የትጥቅ ታጋዮች ከተላለፉ የጥሪ ማስታወቂያዎች አንዱ ይህን ይመስላል::ይመልከቱ
