“አላሙዲን ሆይ…?” – ከኤርሚያስ ለገሰ

al amoudi wearing eprdf tshirtበዚህ አመት በሀገረ አሜሪካን በሚገኙ ታላላቅ ሚዲያዎች አነጋጋሪ የሆነውን የፒተር ሽዊዘር ” CLINTON CASH” የሚለውን መጵሀፍ እንደነበረ የሚታወቅ ነው። መጵሀፋን ከወዳጆቼ ተውሼ እያነበብኩ ገጵ 134 ስደርስ ከዛ በላይ መቀጠል አልቻልኩም። እንዲህ በማለት ራሴን ጠየኩ፣

“አላሙዲን ሆይ ከኢትዬጲያውያን የነጳነት ጫንቃ መቼ ነው የምትወርደው?”
“አላሙዲን ሆይ እንደ ሰው ተቆጥረን የመኖር መብታችን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀህ የምትኖረው እስከመቼ ነው?”

እነዚህን ጥያቄዎች ለማንሳት ያስገደደኝ በፒተር መጵሀፍ ከገጵ 128 -134 የሰፈረውን ቁምነገር በማንበቤ ነው። ርግጥ አላሙዲን እና ከስሩ የኮለኮላቸው ኮልኮሌዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የፈጰሟቸውን ወንጀሎች ጠንቅቄ ስለማውቅ ፒተር በምርመራ አግኝቶ ከጳፈው በላይ መናገር እንደሚቻል አውቃለሁ። ጊዜውና ሰአቱ ሲደርስ። በነገራችን ላይ ከእኔ በላይ ስለ አላሙዲን እና ግብረአበሮቹ ብዙ የሚያውቁ ኢትዬጲያውያን በየቦታው አጋጥመውኛል። አንዳንዶቹም ለሼሁ እንደነገሩት እና ” ጆሮ ዳባ ልበስ!” እንዳለ አጫውተውኛል። እሁድ እለት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ላሊበላ ሆቴል ያገኘሁት የሆቴሉ ቋሚ ደንበኛ የሼሁ የቅርብ ጓደኛ እንደነበረ ብዙዎች ስለመሰከሩ፣ ጆሮዬን ከፍቼ አዳምጠው ነበር። ባለፋት 24 አመታት ሼህ መሀመድ አላሙዲን በኢትዬጲያውያን የእለት ተእለት ህይወት ውስጥ ተጵእኖ የሚያሳድር ሰው እንደሆነ ማንም አይክደውም። በዚህ ምክንያት የሼሁ ሁኔታ በኢትዬጲያውያን ዘንድ በበርካታ ወለፈንዲዎች የተሞላ ነው። ከኮልኮሌዎቹ አንጳር ሰውየው በተቃርኖ ውስጥ ባለ ቀጭን ገመድ ላይ ተዝናንቶ የቆመ ነው። በዝህች በተወጠረች ገመድ ስር በርካታ ሹል ምስማሮች ተሰክተው ይጠብቁታል። ቀን ሲጥለው እነዛን ሹል ምስማሮች ከማንም ቀድመው እየተስፈነጠሩ ይሰኩበታል። ምስማሮቹ ኮልኮሌዎቹ ናቸው። ከሌላው ኢትዬጲያዊ አንጳር የተቃርኖው ምንጭ ከሰው ሰው ይለያያል። በአንድ በኩል ሰውየው በሀገሪቱ ታይተው የማይታወቁ ኢንቨስትመንቶች አሉት፣ እጁን ፈታ አድርጐ ሊረዱ የሚገባቸው ታዋቂ ግለሰቦችን ይረዳል የሚል ነው። በሌላ በኩል የሀብት ምንጩ የሀገራችን ወርቅ፣ የተሰጡት የትየለሌ መሬቶች፣ በሞተ ዋጋ የገዛቸው መንግስታዊ ተቋማት ናቸው። የሚረዳውም በአካፋ ከወሰደው ውስጥ በቡና ማንኪያ ነው። አረዳዱም እንደ አለቆቹ በከፋፍለህ ግዛው መርሆ በመመራት ነው የሚሉ በርካታ ናቸው። እኔም የምስማማው በመጨረሻው ዘርፍ ካሉት ሰዎች ቢሆንም በዝች አጭር ማስታወሻ ከዚህ በላይ መሻገር አልፈልግም።

ለዛሬው “አላሙዲን ሆይ… ?”” የሚለውን ጥያቄ ከፒተር መጵሀፍ አንጳር ላንሳ። ፒተር በምእራፍ ስምንት ” WARLORD ECONOMICS” ብሎ በጠራው ክፍል ውስጥ በሼህ አላሙዲን፣ በመለስ ዜናዊ ( ነብሱን ይማረው!”) እና በክሊንተን መካከል የነበረውን ግንኙነት በዝርዝር ያብራራል። ሼህ መሀመድ እና ክሊንተን በእንግሊዝ ለንደን ተገናኝተው እንደነበረና እንደተወያዩ ይነግረናል። አፍታም ሳይቆይ እ• ኤ•አ ግንቦት 14 ቀን 2007 በተካሄደ አጭር ድግስ ሼሁ ለክሊንተን ፋውንዴሽን ሀያ ሚሊዬን ዶላር ለመስጠት ቃል ይገባል። የዛኑ እለት ሁለት ሚሊዬን ዶላር በቼክ ይከፍላል።

ፒተር ባደረገው ጥናት አላሙዲን የአማላይ ( lobbing firm) እንዳለው ያረጋግጣል። በዚህ አማላይ ተቋም ውስጥ በአባልነት ሶስት ትላልቅ ሰዎች በተከፋይ አማካሪነት እንደሚሰሩም ይናገራል። እንዲህ በማለት፣ “… His lobbying firm in washington included Senators George Mitchell, Lioyd Bentsen( who had been treasury secretary when Bill was president), and Bob Dole as paid advisers.” ፒተር ከዚህ በኃላ የሚያመጣው መረጃ ለኢትዬጲያውያን በጣም አስደንጋጭ ነው። አላሙዲን ይህንን ቃል የገባው ኮንግረስ ማን ዶናልድ ፔይን የኢትዬጲያ ባለስልጣናትን የሚቀጣው H•R• 2003 ተብሎ የሚጠራው ህግ ባስተዋወቁ ወቅት እንደሆነ ይገልጳል። የህጉ ተኮላሽቶ መቅረት በዚህ ምክንያት እንደሆነ ያሳውቃል። በወቅቱ እነ አቶ በረከት ደረታቸውን ነፍተው ህጉ አይፀድቅም ያሉበት ዝርዝር ምክንያት በጣም ግልጵ ሆኖልኛል። ፒተር የጳፈው ከፊሉ እንደሚከተለው ይነበባል፣ ” In may 2007, when he made his commitement to the clinton Foundation, the Ethiopian Democracy and Accountablity Act ( H•R• 2003) had just been introduced by congressman Donald Payen.” ፒተር በዚህ ክፍል ሌላው የገለፀው በአላሙዲን እና በአቶ መለስ መካከል ስላለው ግንኙነት ነበር። አቶ መለስ በሞተ ሰአት አላሙዲን ቀኝ እጄ ተቆረጠ ብሎ እንደተናገረ አስታውሷል ( When Zenawi died with in 2012 of a mysterious stomach ailment, Amoudi would say, ” I lost my right hand”).

እንግዲህ በአጭሩ አላሙዲን የኢትዬጲያ ሰብአዊ መብት ጥሰትን የሚያበረታታው በዚህ መልኩ ነው። በኢትዬጲያ መንግስት ስም ገንዘብ እየለገሰ፣ ሴናተሮችን በአማላይነት እየቀጠረ እና በወሳኝ ወቅቶች ተጵእኖ እየፈጠረ። ያውም በራሳችን ገንዘብ!! … በነገራችን ላይ በህውሀት መራሹ መንግስት ላይ እንደዛ ውርጅብኝ እየወረደ የኦባማ ወደ ኢትዬጲያ መጓዝ ከላይ ከተጠቀሰው የሼሁ ተልእኮ አንጳር አይተነው ይሆን?…ታሪክ ያወጣዋል!… እስከዛው ግን ለራሴ ” ያልጠረጠረ ተመነጠረ!” የሚለውን የሀገሬ ብሂል ብል ምን ይለኛል?

21 Comments on ““አላሙዲን ሆይ…?” – ከኤርሚያስ ለገሰ”

  1. You people in the USA are funny. You are scared to death to say anything against America but you hurry to attack the little criminals like Al Amoudi and TPLF.

    Al Amoudi and TPLF are peanuts compared to the biggest criminal USA.

    You guys have no credibility anymore because of your pro-American views, and are even viewed as American agents.

    You better not try to impose your crooked pro-American views on Ethiopians. Ethiopians have no other choice but to be anti-American, thanks to 24 years TPLF rule and what happened before.

  2. hey ermi
    beka zim bileh tikededaleh!! Eski netsa honeh and wetatun yemiyastemr metsihaf tsaf, yedanial kibretn yegna tiwldn anbibew
    lesheku tena ena erejm edme

  3. ewnet nw yethiopia wanga telat alamude ena berket simon nachewberket ahunm ngrhalew lejoch wesha yweladu degmo tyaw yhonal kalhe abaye thayhem endezaw tekure wesha yeweldu lejoch yethopia telatoch degmo enywalen

  4. Ermias ante ESAT lay kemekeded wichi min serah. Abreh stbela stbela noreh ahun lalalalala tilalih , maferia neh

  5. He is not represent any images in ethiopia he is one of well developed prostitute organization leaders spoil every marriage definitely to say one of ethio porn star buying car house business investment ….so on .
    Wayne needs such kinds of investors try to suck our natural resources like Gold. also one of the supporter weyane during TPLF gurella fighter with a bridge to saudi Arabia weyane financial money flow cable wired like this they can spent any thing like fore example what Bereket Semone
    in hospital at saudi we can proof any thing nothing above will hide from Ethiopians.

    Death to all weyane swarms suckling ethiopia blood

    Pride for G7 movement give your blood and mind to us

  6. A True legendary lobby for weyane finacial network to drain ethiopia resources.

    We have all evidence to face them for a connection of bribe link to weyane regime.

  7. ERMIYAS LEGESSE! NOW HE LERN FROM HIS NEW FRIEND TAMAGNI BEYENE HOW TO COLLECT MONEY FROM THE DIASPORA WITH OUT WORK,GOOD FOR HIM. HIS NEW FRIEND TEACH HIM HOW TO GET EASY MONEY FROM THE DIASPORA AND THEY HAVE GOOD RELATIONSHIP AND COMMON UNDERSTANDING NOW. TAMAGNI HAVE A GOOD EXPIRIANCE ON THIS FOR THE LAST 20 YEARS AND THE NEW RECURIT ERMIYAS STARTED LETLLY 4 YEARS AFTER HIS ARIVAL IN USA.THEY KNOW HOW TO LIE AND WHEN TO LIE AND COLLECT EASY MONEY.ONE DAY THEY WILL STOP LIEING. ERMIYAS TEBASIN YALAYE BE ESAT AYCHAWETIM, BE ELIYAS KIFLIE YEDERESEW KITAT ETIF HONO WEDANTE ENDAYMETA TETENKEN BE ESAT ATICHAWET

  8. አቶ አኤርሚያስ ያገሬ ያዱገነት ልጅ፤ የማትስ አጫዋቹ፤ አድናቂህ ነኝ ፤ አሁን ግን እናቴ ምን እንዳለችህ ልንገርህና ወደ ሀሳቤ ሊግባ፤ ሁሉን ቢያወሩት ሆድ ባዶ ይቀራል ምነዉ ይሄ ሊጅ …..
    እኔ ደሞ
    እኛ ዘጠኝ ድስቶች አሉን አሁን አንተ ከነሱ ጋር ተቀላቅለህ እንድትማሰል ሳይሆን የምንፍልግህ ወይም ምትክሰዉ ወይ ዉረድ ወደ ሜዳዉ ወይ በከባድ ሚዛን ታገል። ትንታኔ ለዶ*ሩ ወይ ለጋዜጠኛዉ ተወዉ።
    2) ከሳጥኑ ዉጪ አስብ፡ ስለ አላሙዲ ወይም ስለ በረከት ብትለዉ ብትለዉ ጠብ ያሚል የለም እኛ ገፈት ቀማሾቹ (የኢትዮጲያ ህዝብና ዲያስፖር) እናዉቀዋለን ፤ ምን መሰለህ ብሮ/ እያካሄድን ያለዉ ፖለቲካ ቀላል አቀራረብ የበዛበት ነዉ ማለት ሰዉን ተነጋግሮ ተወያይቶ ተመካክሮ ሰዎችን ወደ ራስ ማቅረብ ሀሳባቸዉን ማስቀየር ደጋፊ ወዳጅ ማድረግ ትግስት፤ብልሀት እልህ፤ ራስን ዝቅ ማድረግ ገንዘብ ጊዜ …. የጠይቃል ግን ቀላሉ ምናባቱ የው.. ልጅ ወያኔ ባንዳ ነዉ ምንም አታወታበትም፤ ፤ ስለዚህ አላሙዲን የአኢትዮ/አኤርትራን ጦርነት 60% የረዳ ባለሀብት መሆኑን ላንተ ባልነግርም ዝም ብለህ በዚህ ሰአት የሱን አጀንዳ ስታነሳው ጠላት እየጨመርክልን መሆኑን ሳስበዉ ትንሽ ኧለ አደል … ስለዚህ አልሙዲንንም ሆነ ሌሎች ባለሀብቶችን ልክ እንደ 97 ቅንጅት ጊዜ እንዲረዱን ሎቢ ንና ፔኔትሬት ማረግ ና ወዳጅ ደጋፊ ያገር ልጆች ( do not forget at the end Al/mudi is an Ethiopian citizin) እኛ ስንመጣ እንወርሳለን እንቆርጣለን ለነጋዴ ቀርቶ ለካድሬዎችም አይሰራም . ልብ ካልክ ወያኔ ሰራዊቶቹ ፌደራል ፖሊስ ወይም አጋዚ ይልቅ በጥቅም ወንጀል የተበተባቸዉ ካድሬዎችና የሰፈር ደላሎች ናቸዉ.. ስለዚህ ባጭሩ አልሙዲንንም ሆነ ሌሎች ባለህብቶችን ወገንና ረዳት እንዲሆኑ ወጣ ብለህ አስተባብርና ስራ
    ከይቅርታ ጋራ

  9. TENKOLU yetenkol sew malet new. It mean you are on evel sprit. Yenanten hasab yemayaramid sew ,yemayikebel sew weyani mebalun akalehu bihonim gin ewnetun kemenager alakomim. Bergitegninet yihi sewn emitzeretitibet afih kenu soders yizegal. Maninetihin feligeh sitagegnew titewewalehu. Eski gadem sitil asibew, eskemeche new chuh siluh eyechok atinager siluh zim eyalk yemitnorew eski ende habesha kuru defar hun ( vuvu zula) atihun. Ewnetin feligeh agignat. GOD BLESS ETHIOPIA

  10. Bekedem ye unity temariwochun siyasmerk yalewn semachu wow. Hagerachin begnaw belijochuwa new beteley betemarew. Abo sheku genzebh sayhon ante nurlin!!! Ermi ahun ante meret limat bitsera kehager tiweta neber? Ere befitsum!! B/c mar betuto silale. Endenante le telat kemiset lenat hageru biset jegninet new. Lesheku tenawn yisitln.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*