አሁንም አልሸባብ! – ጌታቸው ሽፈራው
ምርጫ 97 ላይ ድምፅ ሲሰርቅ እጅ ከፍንጅ የተያዘው፣ ከዛም የሌባ አይነ ደረቅ ሆኖ እኔ ነኝ አሸናፊ ያለው ህወሓት/ኢህአዴግ የተቀየመውን ህዝብን ትኩረት ለማስቀየስ አንዳች ዘመቻ ያስፈልገው ነበር፡፡ የእስልምና ፍርድ ቤቶች ህብረት ሶማሊያ ውስጥ ቡራከረዩ ሲል የነበረበት ወቅት ነው፡፡ ለህወሓት/ኢህአዴግ ጥሩ አጋጣሚ ሆነለት፡፡ ‹‹ድንበርክን ጠብቅ›› ተብሎ ቢመከር አልሰማም፡፡ አሜሪካ፣ የተባበሩት መንግስታትና ሌሎችም ጥለውት የወጡት ሶማሊያ ውስጥ ዘሎ ገባ፡፡ ለጊዜው በምስኪን ኢትዮጵያውያን ደም የእስልምና ፍርድ ቤቶች ህብረት የተበታነ መሰለ፡፡ ግን ደግሞ የውጭ ወረራ ከምንም በላይ የሚያበረታቸው ሶማሊያዎች ‹‹ጠላት ኢትዮጵያ ወረረችን›› ብለው ወጣቱን አነቃነቁ፡፡ አልሸባብ ወይንም ‹‹ወጣቶቹ›› አዲስ ሀይል ሆነው መጡ፡፡ በህወሓት/ኢህአዴግ ዘሎ ገብነት ምክንያት በምስራቅ አፍሪካ አዲስ አሸባሪ ተፈጠረ፡፡
ከብአዴን፣ ኦህዴድ….እስከ ትግስቱ አወሉው አንድነት ኢህአዴግ ቡድኖችን ፈጥሯል፡፡ እነዚህ ሁሉ ታዛዦች ናቸው፡፡ አልሸባብ ግን ህወሓት/ኢህአዴግ ከፈጠራቸው ቡድኖች መካከል አደገኛው ነው፡፡ በእርግጥ ለእሱ የዶላር ምንጭ ነው፡፡ ከእነ ቴሌ ቀጥሎ ሌላ በኢትዮጵያውያን ደም ዶላር የሚታለብ ላም፡፡ ወደ ሶማሊያ ከገባበት 2006 (እ.ኤ.አ) ጀምሮ ዶላር ይዝቅባታል፡፡ በኢትዮጵያውያን ደም!
እ.ኤ.አ ከ2006 ጀምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን አልቀዋል፡፡ ከሁለት አመት በኋላ ደግሞ ‹‹ተው!›› እየተባለ አልሰማ ብሎ የፈጠረውን አልሸባብን አልችል ብሎ በበቃኝ ከሶማሊያ ቅሌቱን ተከናንቦ፣ ኢትዮጵያውያንን አስፈጅቶ ወጣ፡፡ ዶላር ተፈለገና ከወጣ ከሁለት አመት በኋላ እንደገና ገባ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አልሸባብን ጠራርገን አስወጣን ሲሉን ቆይተዋል፡፡ አልሸባብ ግን አሁንም አለ፡፡ አሁን ኦባማ ሲመጣ እንኳን በጦር ጀት እያባረርነው ነው፣ በታንክ መግቢያ መውጪያ እየነሳነው ነው ይሉናል፡፡ ሰሞኑን ወሬያቸው አልሸባብ ላይ እየተወሰደ ያለው ‹‹መጠነ ሰፊ ጥቃት›› ሆኗል፡፡ ለኦባማ ገፀ በረከት መሆኑ ነው፡፡ (ለጠቅላላ እውቀት ያህል ግን ኦባማ ኢቲቪን አያይም)
ሀገር ውስጥም የፈጠሩት አልሸባብ ጥቃት ይፈፅማል ብለው ሰራዊት አፍሰዋል፡፡ አልሸባብ ነህ ብለው ዲያቆን ሳይቀር አስረዋል፡፡ አልሸባብ ግብሩን ከማን ወሰደ ቢባል መልሱ ቀላል ነው፡፡ ከፈጣሪው!

All signs point to Eritrean regime’s plan to march the Tigrean People Democratic Movement (TPDM) into Ethiopia in the near future. So far, there is no action on the ground except hyper propaganda. But by all indications, Shabia is ready for action because it cannot sit idly by while the country withers away as Eritrean youth run for the border and the U.N. sanction takes its toll. The country’s economy and military is depleted by the mass migration of Eritrean youth out of the country. Eritrea is in a death spiral. Molla Asgedom to the rescue…ዛሬ ሁሉም ተናጋሪ ቢሆንም የነገር ድግግሞሽ አታክቶናል። ገና የተተነፈሰው እንደሰሚው ተወላግዶ ወይም ጣፍጦ የበሬ ግንባር በምታክለው ፌስ ቡክ ይለጠፋል። ወሬ ብርቅ አይደለም። እንዲያውም በርካታ ተግባር አልባ የወሬ ቤቶች ተከፍተው ወሬ ሲወቁ ነገር ሲሰልቁ ቡና ቤት መለወጥ እንደሚወድ ጠጪ ከአንዱ ፓልቶክ ወደ ሌላው እየዞሩ በጉንጭ አልፋ ፍሬከርስኪ የሚያደነቁሩን አውርቶ አደሮች በዝተውብናል። ከሁሉ የሚያሳዝነው ደግሞ ከፈር ቀዳጅ ታጋዮቹ መንደር ነበርንና አንቱ በሉን የሚሉ እድሜ ጠገቦቹ ከተማሪ ረብሻ ወዲህ አርባ አመት ያስቆጥሩም ቢሆን ዛሬም እንኳ የአስተሳሰብ ጨቅላነታቸውን አለመጨረሳቸውና አሁንም በረብሻ መተዳደርን የመረጡ በሚያስመስል አፍራሽ ተግባር ተጠምደው ማየታችን ነው።
በእድሜ ዘመናቸው አንድም ሚዛን የሚደፋ ቁምነገር ሰርተው አያውቁም። በተለይ ደግሞ ወያኔ ወደስልጣን ከመጣ በሁዋላ ከኛ በላይ የወያኔ ተቃዋሚ ለአሳር እያሉ ሽንጣቸውን ገትረው የሚውረገረጉም ቢሆን የዚህን አረመኔ ወያኔ እድሜ የሚያረዝም እንጂ የሚያሳጥር ምንም ሰርተው አያውቁም። እንዲያውም ከእድር ለየት ባለ የፖለቲካ ቡድንነት የተሰባሰቡ መሆናችው ትዝ የሚላችውና ነገር ጣል ለማደረግ የሚባንኑት ሌላው ወገን የሰራው ነገር መኖሩን ሲሰሙ ነው። ያኔ አይናቸው ደም ይለብሳል እንደ ወያኔ ተለጣፊ ወይም ተመሳሳይ ነገር ሰርተው የተሰራውን ለማፍረስ ይጣደፋሉ። ገና አልባነነ ይሆናል እንጂ ጋዜጠኛውም ከፍርስራሾቹ አንዱን እየሆነ ነው። እንዲያውም ቆመጥ አድርገውት የራሱን ኢሳትን ይደበድቡበታል። እርሱም ዝናዬን ቀሙኝ ኩርፊያ የያዘ ይመስል አጓጉል መሄዱን መርጧል። ብቻ አጎቶቻችን ለማፍረስ ሲሆን እንደ ተኩላ ናቸው በጩኸት ይጠራራሉ ሳይነጋገሩ ይግባባሉ። ድርጅት በአይነት በአይነት ያቋቁሙና የመጥለፍ ጥማታቸውን ለጊዜውም ቢሆን ያረካሉ። የጀመሩትን ከምን እንዳደረሱት የሚጠይቅ ስለሌለ አዲስ ባቆሙት ላይ ያወራሉ። ትግል የሚለውን ቃል በግርድፉ እንዲያው ቃል በቃል ወስደው ነው መሰል አድማ እየመቱ ከሁሉም ሲታገሉና ሲያፈርሱ እድሜ ራሱ አፈራርሶ ሊጨርሳቸው ነው።
በመጨረሻ አንደርዳሪ ብልጥ ሃሳብ አገኘሁ እነሆ የብልህ ሰዎች ማህደር ከዊንስተን ቸርችል አባባል ላይ ወስዶ የለጠፈው ቃል ማረከኝ። “ውሻ በጮኸብህ ቁጥር ድንጋይ እያነሳህ የምትወረውር ከሆነ ካሰብክበት አትደርስም” የሚል ነው። አዎ ሩቅ ለመሄድ አልመው ድንጋይ ወርዋሪና ማዶ ለማዶ ቆሞ ተሳዳቢነትን የመረጡ ያሰቡበት አይደርሱም። ሰሞኑን የሚነፍሰው ንፋስ ግምኛ ነው ይሰነፍጣል። በርግጥ እነዚህ ሰዎች ነጻነትን ይፈልጋሉ ወይንስ እኛ ካላረግነው ሁሉም አፈር ይብላው የሚሉ ናቸው? እውን እነዚህ ሰዎች ለአፍራሽ ተልዕኮ የሚሰጣቸው ፍርፋሪ ኖሮ ነው ወይንስ ኑሮአቸው ይኸው ግርግር የመፍጠር ሆኖ ነው? ያስብላል። በተለይ የተማሩትና የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል እያሉ የሚጽፉት ምሁራኖች እነሱ ባሉብት መድረክ ላይ በጠንካራ ታጋዮችና መሪ ድርጅቶች ላይ ተራ ስድብ ሲደረደርና ትግሉን የሚጎዳ ግርድፍ ሀሳብ ሲዥጎዶጎድ በዝምታ ማለፋቸው ምን ይባላል? እኔን አንቱ እስካላችሁኝ ድረስ ሌላውን ድባቅ ብታስገቡትና ትግሉን ብትጎዱት እኔ ምን ገዶኝ ብለዋል ማለት ነው? ይሄ ከሆነ ስሌቱ ፍላጎታቸው መድረክ ላይ መኮፈስ እንጂ ሀገርን ማዳን አይደለም ብለን እኛም ለእንደዚህ አይነቶቹ የሚቸረውን አክብሮት እንሰጣቸዋለን።
በተግባራዊ ትግል የተጠመደው ወገን ደግሞ እነ ሰው ከንቱን ቁም ነገር አድርጎ አቧራ ማጨሱን ተወት አድርጎ ጊዜውን ተግባራዊው ትግል በሚፈልገው እንቅስቃሴ ላይ ቢያተርኩር ይሻላል። የእነኚህ አፍራሽ ወሬኞች ፋይል መዘጋት አለበት። እነርሱን ሰምቶ ከመንጫጫት ከግንቦት ሰባት አመራር ተምረን ለወሬኞች የምናባክነው ሰአት የለንም ብለን ወደተግባሩ እንመለስ። የግንቦት ሰባት አመራሮች ለርካሽና ተልካሻ ነገር መልስ ለመስጠት ደፋ ቀና ሲሉ አናያቸውም። ስራው ላይ በማተኮራቸው የእምነት ጽናትም በማሳየታቸው መሬት ላይ የሚታይ ስራ እየሰሩ ነው። ‘በርገር’ እየበሉ ግፋ በለው ብቻ እንደማይሉ ደግሞ በተግባርም እያሳዩ ነው። የሚበልጠው ለእናት ሀገር ለመዋደቅ የቆረጡ ወጣቶችንና አርበኞችን መደገፍና ትግሉን ማፋፋም ወይንስ የአሽሙር ጧፍ እያበሩ የእርግማን አዝማች ያለው የስድብ መዝሙር መዘመር?
ምርጫችንን ልናውቅ ልንበስልና ልንበቃ የሚገባን ጊዜ ላይ ነንና ከአመት አመት ራሳችንን እዚያው የነበርንበት ላይ ማግኘት ደካማ አቅማችንን ፀሀይ ማስሞቅ ይሆናል። ለዚህ ነው እነ ስም አይጠሬን ከቁም ነገር መድረክ ላይ ቆልለን በጮሁ መጠን ቃላት የምንወራወር ከሆነ መቼም ቢሆን ካሰብንበት አንደርስም ለማለት የወደድኩት። እንዲያውም ተጋብቶብን ቀንደኛ ተሳዳቢና አለክላኪ ተጓዥ ሆነን እርስበርስ የመነካከስ ባህርያትንም እየወረስን ነውና እነሱን ከመሆን ያድነን እንበልና ወደፊት እንገስግስ። ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር የሚል መፈክር ትዝ የሚለው ማነው? አዎ ያኔ ያለቀ ቢሆን ዛሬን ባልዘመትን ነበር።
ድል የማይቀር እውነት ነውና ዱር ቤቴ ላሉት ደጀን መሆን ምርጫችን ይሁን!
Molla Asgedom, the next Meles Zenawi?
Post a reply
Postby elias » Yesterday, 04:53
All signs point to Eritrean regime’s plan to march the Tigrean People Democratic Movement (TPDM) into Ethiopia in the near future. So far, there is no action on the ground except hyper propaganda. But by all indications, Shabia is ready for action because it cannot sit idly by while the country withers away as Eritrean youth run for the border and the U.N. sanction takes its toll. The country’s economy and military are depleted by the mass migration of Eritrean youth out of the country. Eritrea is in a death spiral. Molla Asgedom to the rescue… [The full text to be published shortly]ውሻ ጮኸ ተብሎ ድንጋይ አይወረወርም
July 22, 2015
ዛሬ ሁሉም ተናጋሪ ቢሆንም የነገር ድግግሞሽ አታክቶናል። ገና የተተነፈሰው እንደሰሚው ተወላግዶ ወይም ጣፍጦ የበሬ ግንባር በምታክለው ፌስ ቡክ ይለጠፋል። ወሬ ብርቅ አይደለም። እንዲያውም በርካታ ተግባር አልባ የወሬ ቤቶች ተከፍተው ወሬ ሲወቁ ነገር ሲሰልቁ ቡና ቤት መለወጥ እንደሚወድ ጠጪ ከአንዱ ፓልቶክ ወደ ሌላው እየዞሩ በጉንጭ አልፋ ፍሬከርስኪ የሚያደነቁሩን አውርቶ አደሮች በዝተውብናል። ከሁሉ የሚያሳዝነው ደግሞ ከፈር ቀዳጅ ታጋዮቹ መንደር ነበርንና አንቱ በሉን የሚሉ እድሜ ጠገቦቹ ከተማሪ ረብሻ ወዲህ አርባ አመት ያስቆጥሩም ቢሆን ዛሬም እንኳ የአስተሳሰብ ጨቅላነታቸውን አለመጨረሳቸውና አሁንም በረብሻ መተዳደርን የመረጡ በሚያስመስል አፍራሽ ተግባር ተጠምደው ማየታችን ነው።