ለሕዝብ የቆመ ሽብርተኛ የሚባልበት አገር – የሚሊዮኖች ድምጽ

ወያኔ ሃብታሙ አያሌው ላይ ላቀረበው ክስ፣ ምንም አይነት መረጃ የለዉም ። ክሱ በአብዛኛው “በኢሳት ፣ በዚህ ራዲዮ፣ በዚያ ፓል ቶክ ክፍል … ቃለ መጠይቅ አደረገ ..” ወዘተረፈ የሚል ነው።
ኢሳት ላይ እጅግ በጣም በርካታ ኢትዮጵያዊያን እና የዉጭ አገር ዜጎች ቀርበዋል። ቪኪ ሃደልሰንን፣ ዶር መራራ ጉዲናን፣ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነትን፣ የሃይማኖት አባቶችን፣ አርቲስቶችን መጥቀስ ይቻላል።

አንድ ንግግር ወንጀል ነው ከተባለ፣ ፍትህ የሚያወቅ ትልቅ ሰው የሚጠይቀው “ምን ተናገሩ ?” የሚለውን እንጂ “የት ተናገሩ?” የሚለው መሆን አልነበረበትም። ሆኖም ትልቅነት የራቃቸው ገዥዎች፣ ለምን ፣ ኢሳት ላይ ቀረባችሁ በሚል እነ ሃብታሙን “ሽብርተኛ” ብለው ከሰሷቸው። እነ ሃብብታሙ የጻፉት፣ የተናገሩት በይፋ ነው። ሰላማዊ ዜጎችን እንደሆኑ ራሳቸው ወያኔዎችም ያወቃሉ። ነገር ገን ያሠሯቸው፣ “ሽብርተኛ” ስለሆኑ ሳይሆን፣ በሐሳብ እነርሱን ማሸነፍና መቋቋም ስላልቻሉ ነው። ወያኔዎች የሐሳብ ድሆች ናቸው። በሐሳብ ተሸንፈዋል።ፖለቲካቸው ከስሯል። ተቀባይነት አጥተዋል። እነ ሃብታሙ አያሌው የሕዝብ ድጋፍ እያገኙ ሲመጡ በሐሳብ ሲሸነፉ፣ ወያኔዎች ወደ ለመዱት የጫካና የኋላ ቀር አሰራርቸው ሄዱ። የኅይል እርምጃ ወሰዱ። ምንም ወንጀል የሌለባቸውን አገራቸዉን በመዉደዳቸው ሽብርተኞች አሏቸው።
እነ ሃብታሙ ግን በአካል ወህኒ ቢሆኑም፣ በአካል ቢጎዱም፣ በመንፈስ ግን የበላይነት አገኙ። ይነ ሃይልማርያም፣ የነ በረከት ስሞን፣ የነ ሳሙራ የነሱ፣ የነ መለስ ዜናዊ ፎቶዎች፣ ምናልባት በመንግስት መስርኢያ ቤቶችና ኤምባሲዎች ካልሆነ በቀር. ቁሻሻ ዉስጥ የሚጣሉት። የነ ሃብታሙ ግን፣ በክብር በግድግዳዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በህዝቡ ልብ ዉስጥ፣ ፎቷቸው እየተሰቀለ ነው። እነ ሃብታሙ እየከበሩ አሳሪዎቻችቸውን ግን እየተዋረዱ ፣ እነ ሃብታሙ እያሸነፉ፣ ወያኔዎች ግን እየተቸነፉ ኔ የመጡት።

ሃብታሙ አያሌው በባህር ዳር ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ህዝብን ሲቀሰቅስ የሚያሳይ ቪዲዮ ይመልከቱ ። ይሄን በሺሆች የታጀበ ወጣትን ነው ወያኔዎች ሽብርተኛ የሚሉት !!!!

ሃብታሙ አያሌው ሲያሰማቸው ከነበሩ መፈክሮች መካከል፡

“ታጋይ ይታሰራል፤ ትግል አይታሰርም”
“እጃችን ላይ ፈንጂ የለም፣ ከሳሾቻችን አሸባሪ ይላሉ”
“የኢትዮጵያ ህዝብ አሸባሪ አይደለም። ትቻችሎ፣ ተፋቆር የኖረ ነው”
ሲል ነበር። ሆኖ፣ ብብዙም አልቆየም ይሄንን ታላቅ ወጣት “ሽብርተኛ ብለው ከሰሱት”