ቴዲ አፍሮ ከአገር እንዳይወጣ ታገደ

ቴዲ አፍሮ ከጎሳዬ ጋር ተጣምረው ያቀርቡታል የተባለው ኮንሰርት በቪዛ ምክንያት ፕሮግራሙ መፋለሱ የሚታወስ ሲሆን ቴዲ ግን ዛሬ የበረራ ጉዞ ነበረው።ጉዳዩ ከሙዚቃ ስራ ጋር የተያያዘ አልነበረም።ባለቤቱ አምለሰት ሙጬ በአሁኑ ሰአት ለጤንነት ቼክሃፕ ኬንያ ናይሮቢ ትገኛለች።ቀደም ብላ የሄደችው ሚስቱን እንዴት ነሽ? ለማለትና ከጎኗ ለመሆን ፈልጎ ለጉዞ የሚያስፈልጉትን የነፍስ ወከፍ እቃዎች በሻንጣ በመሸከፍ በዛሬው አለት ከቀኑ 11 ሰአት ገደማ የአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ደረሰ። የመንገደኞች ቅድመ ምርመራ እና ማጣሪያ ሂደትን አልፎ ግን ወደ አውሮፕላኑ መግባት አልቻለም። ከምን ጋር በተያያዘና ምክንያቱ ምን እንደሆነ በማይታወቅ መልኩ መብረር እንደማይችል ተነግሮት ወደ ቤቱ ተመልሷል።