1 Comment on “”የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም” ! አሥራዳው (ከፈረንሳይ)”

  1. @@@@@@@@@—ፕሬዘዳንት ኦባማ ጠሏትም ወደዱም….@@@@@@@@@@@@@@@@———–

    ዕውነትም “የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም::”አለ በምሳሌያዊ አነጋገር-የፈረንሳዩ ጦማሪ-አሥራደው::

    ለምን ቢሉ ተፈጥሯዊ ግዴታው ነውና:-መብላት,መብላት,መብላት…እንጂ መጠጣት የሚሉትን የሚያውቅ አይመስለኝም:: ጅብ ደምን እንኳን; እስኪረጋ እየጠበቀው የሚበላው ነው የሚመስለኝ:-እናም ለሆዱ ያደረ ለሥጋው መታዘዝ የህልውና ግዴታው ነውና ማንንም ምንም አይምርም::

    እስኪ የጉጅሌውን አፈጣጠር እና ያለፈባቸውን ዓመታት በጥሞና ልብ በሉት:-
    ከመብላት,ከመብላት,ከመብላት…ጋር የተያያዙ አይደሉም?????????የዚህ መንግሥት ነኝ ባይ የሰው-ጽዕብነት ባሕርይ ደግሞ ሙታንንም አላስተረፈም:: ይሁንና በልሳኑ አስደንግጦ ስለገደለው አበበ ገላው ስናወሳ ታምራትን ልብ ልንል ይገባል:-ማን ጅብ ማን አህያ እንደሆነ ባልመድብም ጠላትን አስቀድሞ ማወቅ ተገቢ ነውና ጠላታችን አንድና አንድ ብቻ እሱም ++++ጉጅሌ+++ብቻ ነው:: ይህንን ሐቅ ዋጥ አድርገን ሌሎቹ ሁሉ እግዚአብሔር የሚልካቸው ዕቃዎች ናቸው::እነሱም መላካቸውን አያውቁትም ቢያውቁ ኖሮ “አበበ ገላው የሚባል ወቸገል ዜናዊን አስደንግጦ ይገለዋልና አታስገቡት”ያስብሉ ነበር::እናም የተባለው ይፈፀም ዘንድ ፕሬዘዳንቱም ይግቡ:-እንያቸው!!!እኛ ስለፈለግን አይደለም እግዚአብሔር አይፈፀም ያለው አይሆንም ፈቅጃለው ያለውን ግን ማንም አያግደውም::በነገራችን ላይ እኛ ኢትዮጵያዋኖች በአንድነት ይህን የሰው-ጽዕብ ጉጅሌ ቡድን ፈንቅለን ለመደምሰስ ያደረግነው አንዳችም የሰናፍጭ ትግል የለም:-ለዚህ ነው ሊነጋ ሲል የሚመሸው::ተራ ግጥሜን እንቋደስ ለመልካም ሥራ እንዳረስ::

    «ጠሏትም ወደዱም።»

    ከአሜሪካ ደጃፍ በምጥ እንደወጡ፣
    ደግሞም ወደ ኢትዮጵያ፣
    እንኳን ደህና መጡ፤
    ቆዳ ብለን ሳይሆን፣
    ጎረቤታሞች ነን፤ገብተው ቡና ይጠጡ።
    እግዜር ይናገራል አይሰማም አንዱም፤
    እርስዎ የተላኩት ለኢትዮጵያችን ነው፤
    «ጠሏትም ወደዱም።»
    ማን ዕውነት ይፈራል?ይምጣ ይለይለት፤
    ማህይማን መሃል፣ይግባና ይጎለት።
    መቼም ሰው አይፀዳም ድሮም ሆድ እስካለው፤
    የኦባማም ነገር እንዲህ ነው ‘ሚያስብለው።
    አደባባይ ወጥቶ በሰላ አንደበቱ፤
    ብዙ ቃል ሲገባ እኛን ሲለን በርቱ፤
    በተስፋ-ቃል ብቻ ስናሞቅ ሥልጣኑን፤
    ገና ልናጣራ ነው የኛ ሰው መሆኑን።
    ይለያል ይታያል ጉዱ፤
    የኦባማ ሆዱ።
    እንደ እኛ ካላየ እኛ እንኳን ብንልም፣
    ያውቀዋል መንገዱን አለው ያስቀመጠው፤
    ለአበበ ገላው በወቸገሉ ላይ፣
    ድንጋይ እንዲፈነቅል ዕድሉን ያሰጠው።
    ለጥቅማቸው ብቻ፣አይናቸው የሚያፈጥ፤
    ሕሊናን የሸጡ የሥጋን የሚያበልጥ፤
    ሞልተዋል ባለም ላይ ይሉኝታ የሌላቸው፤
    የሌሎች መገደል ደንታ የማይሰጣቸው።
    አይደለም በቁሙ ሰውን የሚበሉ፤
    ሬሳ አውጥተው የሚግጡ አሉ።
    ድሮ የሚታወቁት የውሻ-ጅብ ዘሮች ብቻማ ነበሩ፤
    በዘመናችን ግን የሰው-ጽዕብ ሆነው አሉ የተፈጠሩ።
    እናም ፕሬዘዳንት ቃልዎን ይጠብቁ፤
    ቢሄዱም ባይሄዱም፤
    ኢትዮጵያ የእግዜር ናት፣
    «ጠሏትም ወደዱም።»
    እግዜር ይናገራል አይሰማም አንዱም፤
    እርስዎ የተላኩት ለኢትዮጵያችን ነው፤
    «ጠሏትም ወደዱም።»

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*