በፍራንክፈርት የእንግሊዝ ኮንስለር ፅ/ቤት የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ
ዮሃንስ ደሳለኝ (ጀርመን – ፍራንክፈርት)
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሰኔ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. June 23, 2015)፡- በጀርመን ፍራንክፈርት ትላንት ሰኞ ሰኔ 15,2007 (June 22,2015) የእንግሊዝ ኮንስለር ፅ/ቤት የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ። በዚሁ ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን በኩል ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው የተሰጡበትን 1ኛ ዓመት ለማስታወስና እንዲሁም ላለፉት አንድ ዓመት ሁኔታዎችን በለዘብተኝነት የምትመለከተው ታላቋ ብሪታንያ ለራሷ ዜጋ ምንም ዓይነት ድጋፍና ከለላ ባለመስጠቷ ለማውገዝና አስፈላጊውን እርምጃ እንድትወሰድ ለማሳሰብ የተጠራው የተቃውሞ ሠልፍ ከጅምሩ ደማቅና አላማውን ያሳካ ነበረ።