በሙታን ስም ድራማ በዋሽንግተን ዲሲ

በሊቢያ የተሰውትን ኢትዮጵያውያን ሰማእታትን ምክንያት በማድረግ ሰሞኑን ባደረግነው ክትትል ወያኔ London, UK ያደረገውን ድራማ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ሊደገም እየተዘጋጀ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ህዝቡን ለማምታታት ሁለት ነገሮች ተከስተዋል።

አንደኛው መምህር ዘበነ በሚያስተዳድረው የደብረ ገነት መድኃኒዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተዘጋጅቶ የቀረበው ከዚህ በታች የተገለጸው የጥሪ ማስታወቂያ ነው።
345k4l52495

ሁለተኛ ደግሞ፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት አንድነት ጉባኤ በሚል ስም በዋሸንግተን ዲሲና በአካባቢዋ የተነሰነሰው ከዚህ በታች የተቀመጠው ማስታወቂያ ነው።
85k4l52495

እነዚህ በተለያዩ ቀናት የተበተኑትን ማስታወቂያዎች ማነው ያዘጋጃቸው? ዓላማቸውስ ምንድነው? ሁለቱም የሚያንጸባርቁት በሊቢያ እና በደቡብ አፍሪካ ለተገደሉት ወገኖች የ40 ቀን መታሰቢያ የሚል ነው። ከአገር ውስጥና ከዋሸንግተን ዲሲ አካባቢ ከሚደርሰን ትችቶችና ትዝብቶች ሁሉቱም ማስታወቂያዎች ከተለያዩ አካላት የፈለቁ ይመስላሉ። ነገር ግን ሁሉቱም የሚናገሩት ያለፈውን የ40 ቀን ጸሎት እያሉ ነው። ያለፈውን የ40 ቀን ለመጠቀም ለምን አስፈለጋቸው? እውነት ለተሰውት ወገኖች የ40 ቀን መታሰቢያ እንዲደርግላቸው አሳስቧቸው ነው? የ40 ቀን መታሰቢያ ማነው የሚያድርግላቸው? እነዘበነን የተለዩ የ40 ቀን ጸሎት አድራሾች ማን አደረጋቸው? ከእንቅስቃሴያቸው በስተጀርባ ማነው የሚገፋቸው? ተልእኮውስ ምንድነው? የነሱ ጸሎት በWashington Monument (ሞኑመንቱ) ላይ ከተደረገው ልዩነቱ ምንድነው? በሞንመንቱ በተከናወነው ታሪካዊ ዝግጅት ላይ ሳይገኙ፤ ዛሬ የ40 ቀን መታሰቢያ እያሉ ሽር ጉድ እንዲሉ ማነው አደራ ያላቸው? በዋሸንገት ቅድስት ማርያም በተደረገው ጥሪ ባካባቢው ያሉ ገዳመ ተክለ ሃይማኖት፤ በዋልባ ገዳም እና በአቡነ ጴጥሮስ የተመሰረቱት ድርጅቶችና አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ወገኖች ህብረት የተደረገውን ዝግጅት የሚቃወሙና “ከኛ ፕሮጀክት ጋራ ይጋጭብናል፣ ከወያኔ ጋራ ያጋጨናል” በማለት በዝግጅቱ ያልነበሩ ናቸው? ወይስ በወቅቱ ባካባቢው ያልነበሩ አዲስ መርዶ ሰሚዎች በመሆን ልቅሶ ደራሾች ናቸው?

በሞንሞንቱ ላይ በተደረገው “የታረዱት ነፍሳት ጩኸት” በሚል መንፈሳዊ፣ ታሪካዊና ሰባዊ ወገናዊ ዝግጅት ላይ የሃይማኖት ክልል ሳይጋርድ ከተለያዩ የእምነት ድርጅቶች ድምጽ የተሰማበት ነበር። በዚያ ያልተገኘ የድርጅት ወኪል አልነበረም። እነሱ ነበሩ ወይስ አልነበሩም? ካልነበሩስ ያልነበሩበት ምክንያት ምን ነበር?

በወቅቱ በሰፊው ሲነገር እንደተሰማው “በሞሞንቱ በተደረገው ብንስታፍ ከወያኔ ጋራ ያጋጨናልና አቁሙ ካላቆማችሁ ሞንሞቱ በሚደረገው አንገኝም” ብለው የሸሹ ናቸው? ወይስ ሌሎች ናቸው?

ባደረግነው ክትትል መሠረት፤ በተለይም በመምህር ዘበነ ለማ ቤተክርስቲያን ዙሪያ ካሉት ሰዎች ሲነገር እደተሰማው በሞንሞንቱ የተደገረው ዝግጅት የወያኔን መንግስት ያስቀየመ ነው።

ሀውልት እናሰራለን የሚለው ወሬ የህዝብ ስሜት መቀስቀሻና ማደንዘዣ አድርጎ ለመጠቀም እንጂ የአቡነ ጴጥሮስን ሀውልት ያነሳ ወያኔ ሰማእታቱ ለምን ተሰደዱ የሚለውን ጥያቄ ስለሚያስከትልበት ያደርገውል ተብሎ አይገመትም። ለጊዜው ህዝቡን ለማደናበረ፤ ሀውልት የሚለውን ቃል ይጠቀምበታል። በደቡብ አፍራካውያንና በአይሲስ ለተገደሉት ወገኖቻችን አይሲስ ገደላቸው ብላችሁ አስታውሱ የሚለውን ወያኔ ባይፈቅድ ኖሮ እነ ዘበነ ጉዳዩን ለመንካት ይቸገሩ ነበር ተብሎ በሰፊው እየተነገረ ነው። ወያኔ ከማረጋገጡ በፊት ዘበነ የወገኖቻችን መታረድ ሲደርሰው የነበረው ስሜት ከወያኔ ስሜታ ጋራ በመጋጨቱ አሁን የ40 ቀን በሚለው መታሰቢያ ለማስታረቅ ያቀደው መስሎ ታይቷል። እሱም ሆነ ተባባሪዎቹ ይህን በማድረጋቸው ቢያንስ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ትርፍ ያገኛሉ።

1ኛ፦ እርም የበሉ ተብለው ባካባቢው እንዳይወቀሱ
2ኛ፦ በሞንሞንቱ የተደረገውን በመሸፈን ከመንግሥት ውለታ ለመሸመት፦
3ኛ፦ የገንዘብ ትርፍራፊ ለመለቃቀም

እንዲህ የመሰለውን ማታለያ ማነው አቁሙ የሚላቸው? ህዝቡን እንዳማያይ፣ እንደማያስብ፣ እንደማይመለከት አርገው ማሰባቸውንስ እስከመቼ ይቀጥላሉ?

ይህ ድርጊት በለንደን የተደረገውን አይነት በዋሸንግተን ለመድገም የተቀነባበረ ሴራ አይመስልም? ወያኔ ለንደን ላይ በህግ ተሸንፎ ሲወድቅ ሁለት አድርባዮች ጳጳሳት ነን ባዮች አባ ገብርኤልንና አባ ቀውስጦስን ልኮ በአካባቢው ያሉትን የኦሬንታልና የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናትን መሪዎች በማስተባበር በለንደን ከተማ ተባብሮ በቆመው ህዝብ ላይ ተጽእኖ አሳድሮ ለመከፋፈል ሞክሯል። በተመሳሳይ መልኩ በዲሲ ዙሪያ ያሉ አስመሳዮችም ለነዚህ ሰማእታት ያሰቡ በመምሰል በሞንመንቱ ላይ የተፈጸመውን ታሪካዊውን የነፍሳት ድምጽ ለማፈንና በህዝቡ የመንፈስ ተጽእኖ ለማሳደር በመሞከር ላይ እንዳሉ ያሳያል።

ከላይ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች በቀር አሁን በዚህ ሳምንት በሰማእታቱ ስም የሚደረገው እንቅስቃሴ ተዝካርም ሆነ የ40 ቀን መታሰቢያ የሚሉት ሽፋን እንጅ መሠረት እንደሌለው ያነጋገርናቸው የቤተክርስቲያን አባቶችም ሆኑ ስለ 40ቀንና መታሰቢያ የሚያውቁ አዛውንቶች ይናገራሉ።

18 Comments on “በሙታን ስም ድራማ በዋሽንግተን ዲሲ”

  1. እነ ዘበነና ሌሎችም መሰል ኢትዮጵያ ተመላላሽ ካድሬዎች ዋናው ስራችው ንግድ ነው። ዘበነ እየሩሳሌም ሰዎችን በየዓመቱ ይዞ ለመሄድ ከምዕመናን ወደ $3,000 ይሰበስባል። የሚካሄደው ንግድ ይሆን ወይንስ ሌላ የሚታወቅ ነገር የለም። ገቢውስ ለምን አገልግሎት እንደሚውል የሚያውቅ የለም። የፋይናንስ ሪፖርት ይህንን ጉዞ በተመለከተ የቀረበ አልሰማንም። የቤተ ክርስቲያኑ ቦርድ ከወያኔ ፓርላማ የባሰበት ከመሆኑም ባላይ ዘበነን ከማቆላመጥና ከመለማማጥ በስተቀር ሌላ ስራ የማይሰራ በድን አካል ነው። የሚገርመው ደግሞ የዘበነ ማዕረግ አበዛዙየቀድሞውን የኢትዮጵያ ፕሬዝድንት መንግስቱ ኃይለማርያምን ትዝ እንዲለኝ አድርጎኛል። ዶክተር መምህር መጋቢ ሐይማኖት ዘበነ ለማ የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤ/ክ ዋና አስተዳዳሪ። ኽረ ምክትል አስተዳዳሪው ቆሞስ አባ ገብረወልድም ንግዳቸውን እያጧጧፉ ነው። ባለፈው ዕሁድ ለይስሙላ እንኳ ለቤተክርስቲያኑ ከሽያጩ ገቢ ይደረጋል ሳይባል አባ ገብረወልድ ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ተዘጋጅቶላቸውና በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ማስታወቂያ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ተነግሮላቸው ያዘጋጁትን ሲዲ ሲቸበችቡ ነበር። የነዚህ ሰዎች ስራ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተመቅደሴን አረከሳችሁ፣ መሸጫ መለወጭ አደረጋችሁት ብሎ ካባረራቸው ሰዎች በምን ይለያሉ??? ግለሰብ ኪሲ የሚገባ ገንዘብን አወደ ምሕረት ላይ በተደረገ ማስታወቂያ ቤተክርስቲያኑ ውስጥ መሸጥ ፣ እርግብ ይሸጡ ከነበረው በምን ይለያል? እኝህ ሰውየ የሚገርመው ከቤተክርስቲያኑ ተሰናብተው ሌላ ቤተክርስቲያን ከሄዱ በኋላ እንደገና ተመልሰው ማገልገል ተፈቅዶላቸዋል። ምክንያቱም ዘቤ ከፈቀደ ምን የማይደረግ ነገር አለና?

  2. A church that is run by Tedla Alemayehu, the most pompous and stupid person is vulnerable for a lot of disaster.

  3. መምሕር ዘበነ ወደ ደብረ ገነት መድሐኒአለም ሲመጣ ዛሬ ያለንበት እንደርሣለን ያለ አልነበረም። አንገቱ ላይ ቀጭን አንገት ልብስ ያለ ጃኬት ለብሶ የመጣው ቀጭኑ መምሕር ዘበነ ስብከቱን ሲያሠማ የጊዜው የቤተ ክርስቲያኗ አለቃ በእሳት መሥለውት ነበር። መላከ ገነት ውቡ ዛሬ አብረውን የሉም ግን (አባ) ማትያስ ወያኔ አዲስ አበባ ሲገባ የደብረ ገነት ተቀጣሪ እንደመሆናቸው ሣያሥፈቅዱ 6 ወር ከርመው ሲመጡ ቦርዱ ደሞዝ እንደማይከላቸው ሲነግራቸው እሳቸው ደሞ እንደውም ለዚህ አካባቢ ተሹሜ መጥቻለሁ ይላሉ ቦርዱ አልቀበል ሲላቸው የደብረ ገነት መዳኅኒአለምን ጠቅላላ ገንዘብ ከአንዲት ሴት ወዳጃቸውና በጊዜው የቤተ ክርስቲያኗ ገንዘብ ያዥ ጋር በመመሣጠር ቦርዱ ሣያውቅ ወደ $400000 US ወደ ሌላ ባንክ በማዘዋወር ዘረፋ በማኪሒዳቸው ቀድሞ ከነበረው ምእመን ጋር በመሆን ፍርድ ቤት መንከራተታችንን ማን ይረሣል? አባ ማትያስ በብፁዕ አባታችን አቡነ ተክለሐይማኖት የተገዘቱ ናቸው። መምሕር ዘበነ ደግሞ አጼ በጉልበቱ ነው፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ይቀጥላል

  4. እነ ዘበነ ለማ፣ተስፋዬ መቆያና ሌሎችም ወያኔዎች ያበገናቸውና አቡነ መቃሪያስ በዋሽንግተን ሞኑመንት በተደረገው ዝግጅት ያስተላለፉት መልዕክት ነው። “ የሚለያዩን ይጠፋሉ፣ ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት መሪ የላትም፡፡ በጎሳ የሚለያዩን ይጠፋሉ። ኢትዩጵያዊያን ማንን ሸሽተው ነው በውጭ አገሪች ውስጥ የተገደሉት?” እነዚህ መልዕቶችን ከኢትዮጵያዊያን አእምሮ ለማጥፋትና በሌላ አደንዝዥ ማደናቆሪያ ለመሙላት ነው ኬና ቴምፕል ውስጥ የተዘጋጀው ማወናበጃ። በዋሽንግተን ሞኑመት ዝግጅት ላይ ሁሉም ኢትዮጵያን የሚወክሉ የኦርቶዶክስ፣ ፕሮቴስታንት፣ ሙስሊም፣ካቶሊክ ሃይማኖት ተከታዮች ተሳትፈዋል። የቀረ ቢኖር ከአገራችን እያሳደደ አሰወጥቶ ለገዳዮቻችን ያቀበለን ወያኔ ብቻ ነው።

  5. Abune Gorgoriyos,

    Which one is a kind of jealousy you are referring to? You probably referring to similar terms that Woyane uses about any opposing individual or party. Woyane supporters say that those who complain about human rights in Ethiopian are people who are out of power. You are dergue etc.

    If you are a true believer in God, do you really approve standing with Woyane at this time?

  6. የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንን ዘበነና መሰሎቹ አንድ ለአምስት ጠረነፏቸው እንዴ? ይህን ያህል ወደ ወያኔ ሊያዘምሙ የቻሉት በምን ምክንያት ነው? በነሱ ስም የሚሰራው ስራ በሙሉ አንድ ለአምስት መጠርነፋቸውን እንጁ እራሳቸውን ችለው ቤተክርስቲያን የሚያካሂዱ አይመስሉም። ስለሆነም ከነሱ አባላት መስማት እንፈልጋለን።

  7. Very disappointing and disturbing.Matthew 7:3-5 Why do you look at the speck of sawdust in your brother’s eye and pay no attention to the plank in your own eye?

  8. BALEKAB BALEDABA: I do not have to be a member or affiliating my self with any one yet as one who know where the truth are will say;

    “TO BE A CHRISTIAN MEANS TO FORGIVE THE INEXCUSABLE BECAUSE GOD HAVE FORGIVEN THE INEXCUSABLE IN YOU”.

  9. Memehir Zebene is a good preacher for sure. But he’s not the only one around. In fact there are a number of others who preach in a more Ethiopian classical style than the recent Protestant style of Zebene who shouts in church to get the attention of the congregation.
    He should decrease his voice a little bit, it’s becoming hazardous for people’s ears. If you are new to the church he can make you uncomfortable.

  10. In the name of God, please stop the madness, we lost our brothers in exile, we are in exile and we always have negative thoughts about others can we be positive and be humans and not say negative words to others and let God only God be the judge of us? We judge too much and we have no open mind in accepting others. Specially name calling is a sin by itself. The law exists to prohibit defamation at least obey the law.

    God bless us all!!!

  11. The hallmark of American Democracy is the freedom of expression guaranteed by the constitution. Thus, you have the right to express your views no matter how ridiculous and absurd. However, please don’t try to pass you opinion for the “truth”. Debre Genet Medhanealem church is one of the few churches in the DC metro area that has a governance system that has a long track record of integrity and transparency.Board elections are held on time and power is always transferred peacefully. The church finances are audited by an independent certified accountant and the board’s fiduciary responsibilities are spelled out in the church bylaws.Also, the duties and responsibilities of the clergy, including Memhir Zebene, and the elected board members are clearly specified in the bylaws. Let us separate the chaff from the wheat before trying to pass innuendos and figments of imagination as the truth.The church is open to all. Come worship and you just might learn the truth.

  12. I would like to address comments by the 2 anonymous and Germew. The trick that has been used in the last 20 years by many priests, monks etc. is to tell the followers of the church not to say any thing.

    One of the repeated quotation is Matthew 7:3-5.

    “Why do you look at the speck of sawdust in your brother’s eye and pay no attention to the plank in your own eye? 4 How can you say to your brother, ‘Let me take the speck out of your eye,’ when all the time there is a plank in your own eye? 5 You hypocrite, first take the plank out of your own eye, and then you will see clearly to remove the speck from your brother’s eye…”

    Yes, this is true that we should not be judicious in our passing judgement of others. However, let me ask those who put that type of argument, does that mean that “only those worshippers who free of any sin could question any priest or monk whatever the priest he does including divorce, stealing, lying, cheating on spouse etc.”?

    I have spoken to many in this regard in the last few years, that trick is no longer valid. In fact, as we speak, followers of ETOC are aware of Paul’s Farewell to the Ephesian Elders
    …28″Be on guard for yourselves and for all the flock, among which the Holy Spirit has made you overseers, to shepherd the church of God which He purchased with His own blood. 29″I know that after my departure savage wolves will come in among you, not sparing the flock; 30and from among your own selves men will arise, speaking perverse things, to draw away the disciples after them.…

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*