ሰበር ዜና – የሀገር አቀፍ አንድነት ጠቅላላ ጉባኤው ለአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ፀረ ሙስና እና ፀረ ኑፋቄ ንቅናቄ የጋለ ድጋፉን ሰጠ

eotc ssd 4th gen assembly

  • የንቅናቄው መነሻ የጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔ እና የፓትርያርኩ አባታዊ መመሪያ ነው
  • ከ25 በላይ አማሳኝ የአድባራት አለቆች እና ጸሐፊዎች ላይ በቂ ማስረጃዎች ተሰብስበዋል
  • የተሐድሶ አራማጅ ሰባክያንን የሚጋብዙ አለቆችና የስብከተ ወንጌል ሓላፊዎች ተለይተዋል
  • የደብረ ናዝሬት ቅ/ዮሴፍ፣ የመካነ ሰማዕት ቅ/ቂርቆስ እና ጃቲ ኪዳነ ምሕረት ተጠቅሰዋል
  • የሀ/ስብከቱ ሥ/አስኪያጅ የሰንበት ት/ቤቶቹን አመራሮች ‹‹እኔ ራሴ አሳስራችኋለኹ›› አሏቸው
  • ‹‹እንቅስቃሴው ይቀጥላል፤ የመላው የአ/አ ሰንበት ት/ቤቶች እና የአንድነቱ የጸና አቋም ነው››

eotc ssd 4th gen assembly participants00
ሦስተኛ ቀኑን የያዘው ፬ኛው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ሀገር አቀፍ አንድነት ዓመታዊ ጉባኤ÷ አማሳኝ የአስተዳደር ሓላፊዎችን እና ሠራተኞችን በማረም ሙስናን እና ብልሹ አሠራርን ከቤተ ክርስቲያን ለማስወገድ፣ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃንን በማጋለጥ ከቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት እና ከመዋቅሯ ለማጥራት በአጠቃላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ተከብሮ ውሳኔዎቹ ተግባራዊ እንዲኾኑ ለመታገል በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ለቀረበው የተግባራዊ ንቅናቄ ጥሪ የጋለ ድጋፍ ሰጠ፡፡