ሰበር ዜና፡- ኢሕአዴግና አጋሮቹ 434 የፓርላማ ወንበሮችን አገኙ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአሁኑ ሰዓት እየሰጠ ባለው መግለጫ፣ እስካሁን በደረሰው ጊዜያዊ ውጤት መሠረት ኢሕአዴግና አጋሮቹ 434 የፓርላማ ወንበሮችን ማግኘታቸውን አስታወቀ፡፡ በቦርዱ ጊዜያዊ ውጤት መግለጫ መሠረት ኢሕአዴግ ከአጋሮቹ ጋር መንግሥት መመሥረት የሚያስችለው ውጤት አግኝቷል፡፡

በቦርዱ መግለጫ መሠረት ኢሕአዴግ በአዲስ አበባ ሃያ ሦስቱንም የፓርላማ ወንበሮች የተቆጣጠረ ሲሆን፣ እስካሁን በተገኘው ውጤት መሠረት ከትግራይ ክልል 38 የፓርላማ ወንበሮች 31 ማግኘቱ ተረጋግጧል፡፡