የኦፌኮ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ሳይመርጡ ቀሩ
ራሳቸው በሚወዳደሩበት ምርጫ ያልመረጡ የመጀመሪያው የፓርቲ መሪ ሆኑ
Ethiopia Zare (እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. May 24, 2015)፡- በኢህአዴግ ተቃዋሚነት የብዙዎች ድጋፍ እንዳላቸው የሚታመነው የኦፌኮ (የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ) ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ዛሬ በተካሄደው ምርጫ ድምጻቸውን መስጠት (መምረጥ) አለመቻላቸው ታወቀ። ዶ/ር መረራ ፓርቲያቸውን ወክለው በተወለዱበት የጉደር ከተማ ተወዳዳሪ ቢሆኑም፤ ለራሳቸውም ይሁን ለሌላ ሰው ድምጻቸውን የሚሰጡበትን የምርጫ ካርድ በሰዓቱ ባለማውጣታቸው ዛሬ መምረጥ ሳይችሉ ቀርተዋል።