አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ከምርጫ ጋር ተያይዞ ሁከትና ብጥብጥ ይፈጥራሉ ያሉዋቸውን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና ደጋፊዎች አስጠነቀቁ፡፡

ጠ/ሚኒስትሩ በፓርላማ ተገኝተው ከኢህአዴግ የም/ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸውን ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን በዚህ ምላሻቸውም በስም ያልጠቀሱዋቸውን ተቃዋሚዎች አስጠንቅቀዋል። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ወደምርጫው የገቡት በግማሽ ልብ መሆኑን ፣ የብጥብጥና የሁከት አማራጭ ከተገኘ ያንን ለማካሄድ የሚያስቡ ናቸው ሲሉ ፈርጀዋቸዋል። ” የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎቹ በአንዳንድ አካባቢዎች ከወዲሁ እኛ አሸንፈናል፣ ከተሸነፍን ደግሞ ምርጫው ተጭበርብሮአል፣ ይህንን አውቃችሁ ምላሽ መስጠት አለባችሁ ብለው ሕዝብን […]