የመን ውስጥ አምስት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአየር ድብደባ ህይወታቸውን ማጣታቸውን መንግስት አስታወቀ 5 Ethiopians died in Yemen bombing

ERTA

የመን ውስጥ አምስት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአየር ድብደባ ህይወታቸውን ማጣታቸውን መንግስት አስታወቀ በአየር ድብደባው ሌሎች ሁለት ኢትዮጵያዊያንም ከባድና ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳች ጽህፈት ቤት ለኢብኮ በላከው መግለጫ አመልክቷል፡፡

በሰሜን የመን ሃራድ በሚባለው አካባቢ በሚገኘው የስደተኞች መጠለያ ላይ በተደረገው የአየር ድብደባ የኢትዮጵያዊያኑ ህይወት ማለፉ ድንጋጤና ሀዘን የፈጠረ መሆኑን መግለጫው አመልክቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ሰንዓ በሚገኘው የሚስዮኑ ፅህፈት ቤት አማካኝነት ጉዳዩን በመከታተል ላይ መሆኑንና አደጋውን በተመለከተም አዲስ አበባ የሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ የተሟላና አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ መንግስት መጠየቁንም መግለጫው አመልክቷል፡፡

በቅርቡ በየመንና በአካባቢው በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት ለአደጋ የተጋለጡ ከ3ሺህ በላይ ዜጎችን መንግስት ወደ ሀገራቸው መመለሱም ተጠቁሟል፡፡

ቀሪዎቹን ዜጎች ወደ ሀገር የመመለሱ ስራ ተጠናክሮ እንደቀጠለም መንግስት ገልጿል፡፡

መንግስት በደረሰው አሰቃቂ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች ፣ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የተሰማውን ሀዘን በመግለፅ መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

Subscribe to Sodere YouTube channel. የዩቲዩብ ቻናልችን ደንበኛ ለመሆን ይመዝገቡ።

See below for some videos from Sodere YouTube channel
Ethiopian Movie Sidet (Exodus) Full

Ethiopian Movie AYREFDEM Full

Ethiopian Movie Kanchi Befit Full

Ethiopian Movie MEZEZ Full

Ethiopian Movie Yefeker Ken full

Ethiopian Movie Yalteneka Full

Ethiopian Movie Kistet Full

Ethiopian Movie Saken Meleskut Full

Ethiopian Movie Bethelehem Full

Ethiopian Movie Setota Full

Ethiopian Movie Mena

Ethiopian comedy movie Che Belew 2

ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎች፣ ፊልሞች፣ ድራማዎች፣ ሙዚቃዎች፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በቀን አንዴ በኢሜል አድራሻችሁ እንልካለን። ይህንን ሊንክ በመጠቀም ኢሜላችሁን አስመዝግቡ። Receive Ethiopian News, Movies and Videos by email. Sign up for Email alerts