በመጨረሻም በግብጽ ነጻ ወጡ፣ እኛ ግን መንግሥት አለን እንዴ?
ክንፉ አሰፋ
የፌስቡክ አርበኛው ቴድሮስ አድሃኖም ቦሌ ሄደው ከሊቢያ ነጻ የወጡ ዜጎችን ሲቀበሉ አየን። እፊታቸው ላይ የማፈር ሳይሆን የጀግንነት ስሜት ይነበባል። አቀባበላቸውም 90 ደቂቃ በኢንቴቤ የሚለውን ታሪክ ይመስላል። ኡጋንዳ ላይ የታገቱ ዜጎችዋን ለማስለቀቅ እስራኤል ያደረገችው ገድል። ቴድሮስ አድሃኖምም በኩራት እና በድል አድራጊነት ስሜት ነው ስደተኞቹን የተቀበሉት።