የጋምቤላ ነዋሪዎች መንግስት በታጠቁ አካላት እያስጨፈጨፈን ነው አሉ

በጋምቤላ ክልል፣ መጃንግ ዞን፣ ጎደሬ ወረዳ የሚኖሩ ዜጎች በመንግስት በተቀነባበረ ሴራ ጭፍጨፋ እየደረሰባቸው እንደሆነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተለይ ከግንቦት 2006 ዓ.ም ጀምሮ 400 ያህል ነዋሪዎች እንደተገደሉ የገለጹት ነዋሪዎች መንግስት የእርስ በእርስ ግጭት ለማስመሰል ቢሞክርም ችግሩ በመንግስት የተቀነባበረ እንደሆነ እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡፡ ‹‹የአብዛኛዎቹ ነዋሪዎች እርሻ ለገዥው ፓርቲው ካድሬዎች በመስጠት እኛ ከቦታችን እንድንፈናቀል ጥረዋል፡፡ አንወጣም ስንል ግን በግድ […]