ኢትዮጵያዉያን በየመን ከፍተኛ ስቃይ ውስጥነን ድረሱልን እያሉ ነው

በስደተኛ አቅሟ ያጠራቀመችዉን ጥሪት ለቦምብ ሚሳዬል አረር ገብራ ከአደን ዳግም ለተሰደደችዉ ኢትዮጵያዊት ጦርነቱ ከፋ፤ «የሚጠጣ ዉሐ ጠፋ፤ ወይም ተመረዘ»-ከሚለዉ ወሬ ያለፈ የጦርነቱ ሰበብ ምክንያት፤ የመርዙ ደረጃ፤ የመርዙ ምንነት፤ የመራዡ ማንነትም ግልፅ አይደለም። ኢትዮጵያዉን ስደተኞች ደቡብ አፍሪቃ ላይ እሳት ተለቀቀባቸዉ።ነደዱ–ሞቱ።ሜድትራኒያን ባሕር ዉስጥ ሰምጠዉ አለቁ።ሊቢያ ላይ ታረዱ።እስራኤል ዉስጥ ዜጋም ሆነዉ ይዋረዱ–ይገለሉ–አሁን ደግሞ ይደበደባሉ።የመን ዉስጥ በባዘነ–ጥይት–ሚሳዬል ተገደሉ። የተረፉት […]