የስኳር በሽታ አይነት 2 (type 2) ምንድን ነው?/What is Diabetic type 2?
(በቴክኖሎጅስት ዳንኤል አማረ)
የስኳር በሽታ ዓይነት 2 በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያለ ሰውን ያጠቃል። በስኳር በሽታ ከተያዙ 3 ሰዎች ውስጥ አንድ በሽታው እንዳለበት አያውቅም ይህ አደገኛ በሽታ ሰውነታችን ከምግብ የሚያገኝውን ካርቦሀይድሬት በትክክል እንዳይጠቀም ያደርገዋል የዚህም ውጤት በደማችን ውስጥ የስኳር መጠን ከፍ እንዲል ያደርገዋል። በደማችን ውስጥ የስኳር መጠን መብዛት የልብ ህመም፣የእይታ ማጣት፣የነርቭና አካል ጉዳትና ሌሎች አደገኛ ጉዳቶች የመጋለጥ እድልን ያሰፋል።
የስኳር በሽታ የማስጠንቀቂያ ደወል ምልክቶች
1. ውሀ ጥም
በስኳር በሽታ ዓይነት ሁለት የተያዙ ሰዎች ለብዙ ግዜ ምንም ምልክት አያሳዩም ምልክት ማሳየት ሲጀምሩ ግን የመጀመሪያው ምልክት ውሀ ጥም ነው ከዚህ ጋር ተያይዞ የአፍ መድረቅ፣የምግብ ፍላጎት መጨመር፣ሽንት በተደጋጋሚ መሽናትና ያልተለመደ የክብደት መጨመር ወይም መቀነስ ችግሮች ይታያሉ።
2. የራስ ምታት
የስኳር የደም መጠን ከተለመደው ውጪ ሲሆን የራስ ምታት፣የዕይታ መጋረድና የድካም ስሜት ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ።
3. ማመርቀዝ( infection)
የስኳር በሽታ አይነት2 ከፍተኛ የጤና ጠንቅ መሆኑ እስከሚታወቅ ድረስ ብዙም ትኩረት የሚሰጠው በሽታ አልነበረም አንደኛው ቀይ መብራት በኢንፌክሽን የመጠቃት ሲሆን በስለት ነገር ሲቆረጡ ወይም ቁስል ካለዎት በቀላሉ አይድንም በተደጋጋሚ በይስት ኢንፌክሽን ወይም በሽንት ቧንቧ ህመም መጠቃት፣የብሽሽት አካባቢ ቆዳን በማሳከክ ይታያሉ
4. የወሲብ ድክመት
በስኳር በሽታ የተያዙ ሰዎች የወሲብ ድክመት የተለመደ ነው የስኳር በሽታ በሀፍረተ ስጋ አካባቢ ያሉ የደም ቧንቧዎችንና ነበርቮች ላይ ጉዳት ያደርሳል ይህም የፍትወተ ስጋ ፍላጎትና እርካታን ማጣት ያስከትላል በተጨማሪም የሴቶች የሀፍረተ ስጋ መድረቅና በወንዶች ስንፈተ ወሲብ ያስከትላል።
በስኳር በሽታ ከተያዙ ወንዶች ከ35-70% እስከ እድሜ መጨረሻ በስንፈተ ወሲብ የመጠቃት ዕድል ሲኖራቸው ከሶስት ሴቶች አንዷ ደግም የወሲብ ድክመት ይታይባቸዋል
በስኳር በሽታ አይነት 2 የመያዝ ዕድልን የሚጨምሩ ተግባራት
– ከመጠን ያለፈ ውፍረት
– ቀይ ስጋ መመገብ
– ሲጋራ ማጨስ
– የዘር ሀረግ( asia,african,americans)
– ከቤተሰብዎ ውስጥ ወላጆች፣እህት ወይም ወንድም የተያዙ ከሆነ
– አብዛኛውን ጊዜ ሳይሰሩ በመቀመጥ ማሳለፍ::
መልካም ጤንነት!
Like my Facebook page for more news.https://www.facebook.com/Danieltechnologist
