ዘመነ እርጠት (Menopause) በወንዶች ይኖር ይሆን?

(በቴክኖሎጅስት ዳንኤል አማረ)

የወንዶች ዘመነ እርጠት የሚከሰተው ቴስቴስትሮን የሚባለው ሆርሞን መመረት ሲቀንስ ነው። ከሴቶች ዘመነ እርጠት ጋር ሲነፃፀር በወንዶች ላይ የሂደቶቹ መገለጫዎች ዘግይተው ይጀምራሉ ከዚያም ለውጣቸው የዘገየ ይሆናል። እድሜያቸው ከ25-75 ዓመት ያሉ ወንዶች ላይ የፍትወተ ስጋ ስራ/አገልግሎት ቀስ በቀስ መቀነስ ይታይባቸዋል በዚህ ጊዜ የሚኖረን የቴስቴስትሮን ሆርሞን መጠን በ 50% ይቀንሳል ይህ ቁጥር ከሰው ወደ ሰው ይለያያል።
የዚህ ችግር መገለጫ ምልክቶች የአቅምና አእምሮ መዳከም፣ ድብርት፣ በቀላሉ መበሳጨት፣ የባህሪ መለዋወጥ፣ የጡንቻዎች መቀነስ፣ የስብ(fat) መጨመር፣ በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ የስሜት ጣሪያ ላይ ለመድረስ መቸገር፣ የፍትወተ ስጋ ቀጥ ብሎ ለመቆም መቸገር ናቸው።

በአሁኑ ጊዜ ብዙ ወንዶች የቴስቴስትሮን ሆርሞን ህክምና ያደርጋሉ ህክምና በመውሰዳቸውም የተሻለ ለውጥ ማምጣታቸውን ተናግረዋል። የዚህ ህክምና የጐንዮሽ ጉዳት ለፕሮስቴት ካንሰርና አርተሪዮ ስኬሌሮሲስ በሽታ የመጋለጥ እድልን ይጨምራል።
ብዙ ኢክስፐርቶች እንደሚያምኑት ከሆነ ይህ ሁኔታ ከሆርሞን ውጪ ወይም በተፈጥሮ የዕድገት ሂደት ደረጃ የተፈጠረ ነው ይላሉ። የዕለት ከዕለት አኗኗር ዘይቤአችን አልኮልና አደንዛዥ እጽ መጠቀም፣ መድሀኒቶች፣ በትዳር ውስጥ የሚያጋጥሙን ችግሮች፣ የገንዘብ/ኢኮኖሚ እጥረት እና ጭንቀት ለዚህ ችግር የመጋለጥ እድላችንን ይጨምራል።
የወንዶች ዘመነ እርጠት እና ይህን ችግር ለመከላከል የሚደረጉ ሆርሞንን የመተካት ህክምና አወያይና አከራካሪ ሀሳቦች ናቸው። በተለያዮ ቦታዎች ከወንድ እድሜ መጨመር ጋር ተያይዘው የሚመጡ ለውጦችን የተለያየ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል።

መልካም ጤንነት!!!
Like my Facebook page for more news.https://www.facebook.com/Danieltechnologist