በስዊድን ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በጋራ ኀዘናቸውን ተወጡ
“እያንዳንዳችን ወደልቦናችን መመለስ አለብን“ የክርስትና ተወካይ
“ቀዳዳውን አብረን እንድፈን“ የእስልምና ተወካይ
“በሰሃራ በረሃ አካላታቸው ለተበለተ ወገኖቻችን ዝም ማለት የለብንም“ የኤርትራ ተወካይ

Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. April 27, 2015)፡- ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከ10 ሰዓት (16፡00) ጀምሮ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም ከ2000 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በሰርገልስ አደባባይ በመሰብሰብ በሊቢያ እና በደቡብ አፍሪካ አሰቃቂ ግድያ የተፈጸመባቸውን ወገኖቻቸውን በማሰብ ኀዘናቸውን እና ተቃውሟቸውን በጋራ ገለጡ።