ተሳዳቢው ጴንጤና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን – አደፍርስ ተሰማ

በኃይማኖት ሳቢያ ደም መፋሰስና አንገት መቀናጠል በሰው ልጅ ታሪክ ወስጥ የተንጸባረቀ ለመሆኑ እጣት ቆጠራ አያሻም።  የእኔ እምነት ካንተ ይበልጣል በመባባል አንድ አንድን ሊያሳምን መከጀሉም ያለ የሚኖር ነው። አሁን ላለንበትም የሃያ አንደኛው ከፍለ ዘመን ሃይማኖት ለኮስ እሳት አለምን እየለበለባት እንደሆነ  ምስክሩ ስንወጣ ስንገባ በራሳችን ጥላ መደንገጣችን ነው። እስልምና ሃይማኖት ተከታይ ተብየው መስጊድ ውስጥ ገብቶ በአምልኮ ላይ ያሉ ምዕመናንን በፈንጂ ያጋያል። አንድ እስልምና አማኝ ሌውን ይገድላል። ዞሮ ተመልሶ ደግሞ የሰላም እስልምናን ይሰብካል። ክርስቲያኑ ደግም በአዕላፍ ዲኖሚኔሽን ተከፍሎ እኛ ከእናንተ እንሻላለን በማለት መድረክ ላይ ይላፈፋል። አታድርስ ነው። የአሁኑ ጴንጤዎች ደግሞ ከበፊቶቹ በብዙ ይለያሉ። መዝሙራቸውና አለም ጮቤ የምትረግጥበት ዘፈን ልዪነት የለውም። መደንከር ነው። አሜን ነው ላልሰሙት ነገር። አምጡ አዋጡ እኔ ልብላ እናንተ ጾም እድሩ ነው ስብከቱ። ትልቅ ህንጻ መስራትና ያለታዬ መኪና በሃገር ውስጥ ማሽከርከር የወንጌል ሰባኪው ፍሬ ነው። ለነፍስ ማደርማ ተረስቶል። በተለመነ የምዕመናን ንዋይ መዘነጥ። በተቃራኒው ለፈጣሪ አድረው እውን መንገድ የሚከተሉም እንዳሉ አልዘነጋሁም። ስራቸው ይመስክራልና የእኔ ምስክርነት አላስፈላጊ ነው።

የዚህ ጽሁፍ መነሻና መዚጊያ ግን ስለተሳዳቢው ጴንጤ ነው። የአንድን እምነት እያንቋሽሹ በምጽድቅ የእኔ ይሻላል ማለት እራስን ማሞኘት ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለሃገሪቱ አንድነትና እድገት ብዙ አስተዋጽዖ አድርጋለች። አሁንም ወያኔን ከሚታገሉት ሃይሎች ቀዳሚውን ቦታ ትይዛለች። በዚህች ቤተክርስቲን ስር ፈደል ቆጥረን ዛሬ ለታላቅ ስፍራ የደረስን ሁሉ ውለታዋ አለብን። ሀ ሁ ብለን የጀመርነው በቅጥሮቿ ውስጥ ነውና። ጥንትም ሆነ ዛሬ የውጭና የውስጥ ጠላቶችን የተጋፈጠችና ዋጋ የከፈለች  በመክፈልም ላይ የምትገኝ ቤተክርስቲያን ናት።  በአንጻሩ በአለም ዙሪያ የተበተኑ ኢትዪጵያውያን ምዕመናናንን የነፍስ ጥማት ለማርካት ዘረኞችን በመዋጋት አንድ በሚያረገን ነገር ላይ እየተመረኮዘች መሪ ትምህርት በመስጠት ላይ ትገኛለች። በሃገር ውስጥም ወጣቱንና አዛውንቱን አይዞአቹህ በማለት በዘር የተለወሰውን ፓለቲካ እንዳይቀበል እያስጠነቀቀች ሰማያዊ መንገድን ታመላክታለች። ይህች ቤተክርስቲያን ዘለፋና ስድብ አልቅጥ ከተጣመሙ የጴንጤ ሰባኪዎች መድረክ በሚመነጭ ስሜታዊ ግፊት መወረፋዋ ተገቢ አይደለም።

ሰው አንድ የሚያረገውን መንገድ በመፈለግ በጋራ ለመስራት እንደመጣር የእኔ እጣት ካንተ ይበልጣል እያሉ መቆለጳጰስ ፈሪሳዊነት ነው። ዛሬ በወያኔ ገፋፊነት አስከፊው እስልምና ስር ስዶ ክፋት የተሞሉ መስጊዶች ምድሪቱን ባጣበቡበት ሰአት አንድ ፈጣሪን እናመልካለን የሚሉ ለወንጌል አዳሪዎች ሊጎናተሉ አይገባም።  የሁለቱም እምነቶች አንድን የሰማይ አምላክ እስካመላከቱ ድረስ በጥቃቅን ነገሮች እንካ ስላንቲያ መግጠሙ ፍሬ ቢስነት ነው። የጴንጤው ሰባኪም አንደበቱን አለዝቦ ወንጌሉን ራሱ እንደተረዳው ለምዕመኑ ማድረስ እንጂ በጊዜአዊ የመድረክ ትኩሳት የሌላውን እምነት መዘንጠል አይገባም። ባንጻሩ የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ሰባኪያን፤ባህታዊያንና መሪዎች አፈትልኮም ሆነ ታልሞ ከሰባኪው መድረክ በወጣ የተጣመመ ሃሳብ እሰጣ ገባ ከመግጠም ይልቅ ወንጌሉ “ግራህን በጥፊ ሲመታህ ቀኝህን ስጥ” እንዳለው ልዪነትን በማጠበብ ለጋራ መስራት ጠቃሚ ነው እላለሁ።

አደፍርስ ተሰማ