80 ኢትዮጵያዊያን በኬንያ ተያዙ

ዳዊት ሰለሞን ኢትዮጵያዊያኑ በኬንያ ፖሊስ ቁጥጥር ስር የገቡት ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚያሻግሯቸው ተስፋ በሰጧቸው ደላሎች አማካኝነት እንዲያርፉባት በተደረገች ክፍል ውስጥ ተደራርበው እንደተኙ ነው፡፡ አየሩ በታፈነ ክፍል ውስጥ ታጭቀው የተያዙት ወጣቶች የሚበዙት ከደቡብ ኢትዮጵያ ተነስተው ሞያሌን አቋርጠው ናይሮቢ የደረሱ ነበሩ፡፡ቤተሰቦቻቸው የነበረቻቸውን መሬትና ከብቶቻቸውን ሸጠው፤የገሚሶቹ ተበድረው ጥቂት የማይሰኙት ደግሞ በአዲስ አበባ ጭምር ለዓመታት በጫማ ጠራጊነት ተሰማርተው ያጠራቀሟትን […]