የአዕምሮ ጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች ከተደጋጋሚ ባህላዊ ሕክምና በኋላ ወደ ሆስፒታል ይመጣሉ ተባለ Ethiopian mental health patients prefer traditional to modern medicine

በ  

     የአዕምሮ ጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች ከዘመናዊ ህክምና ይልቅ ባህላዊ ሕክምናን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተገለፀ።

የኢትዮጵያ አዕምሮ ጤና ማኅበር “የአዕምሮ ጤና በኢትዮጵያ፤ ተግዳሮቶች እና መልካም አጋጣሚዎች” በሚል ርዕስ ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ የቀረበ ጥናት እንዳመለከተው በሀገሪቱ በከፍተኛ የአዕምሮ ጤና ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች ሳይቀሩ ወደ አዕምሮ ህክምና የሚመጡት በተደጋጋሚ ወደ ባህላዊ ህክምና አምርተው ለውጥ ማግኘት ባለመቻላቸው ነው። በጥናቱ እንደተመለከተው ወደ አዕምሮ ጤና ህክምና ከሚመጡት የአዕምሮ ጤና ችግር ካለባቸው ሰዎች መካከል 60 በመቶዎቹ በአማካይ አራት ባህላዊ ህክምና ሰጪዎችን የተከታተሉ ናቸው። በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ የአዕምሮ ጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች ብቻም ሳይሆኑ በአዲስ አበባ ያሉ ጭምር ወደ ሆስፒታል ከመሄድ ይልቅ ባህላዊ ህክምናዎችን ያዘወተራሉ።

የአዕምሮ ጤና ችግርን በዘመናዊ ህክምና ይድናል ብሎ ወደ ዘመናዊ ህክምና አለመሄድ በእኛ ሀገር ብቻም ሳይሆን ባደጉት ሀገራት ጭምር ያለ ችግር መሆኑ በጥናቱ የተገለፀ ሲሆን፤ ሆኖም ግን በሀገራችን ያለው ሁኔታ በርካቶች በዘመናዊ ህክምና መዳን ሲችሉ እድሉን እንዳያገኙ እያደረጋቸው መሆኑ ተገልጿል። ብዙዎች የአዕምሮ ጤናን ከተለያዩ ባህላዊ አስተሳሰቦች ጋር እያያያዙ ከዘመናዊ ህክምና እንደሚርቁም ተገልጿል።

     በኢትዮጵያ የአዕምሮ ጤና ታሪክ ሲነሳ ለዘርፉ ብዙም ትኩረት ባለመስጠቱ በቂ የአዕምሮ ጤና ሆስፒታሎችን እንኳን መክፈት አልተቻለም። በሀገሪቱ የአዕምሮ ጤና ህክምና በመስጠት ረገድ አብዛኛውን አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው አማኑኤል ሆስፒታል ቢሆንም ሆስፒታሉ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎችን ከአቅሙ በላይ በሆነ ሁኔታ እያስተናገደ ይገኛል። ሆስፒታሉ ያለበት አካባቢ ፀጥታው እና ደህንነቱ እንዲሁም ንፅህናው ያልተጠበቀ መሆኑ ለታካሚዎች ተገቢውን እርካታ ለመስጠት አላስቻለውም ተብሏል።

Subscribe to Sodere YouTube channel. የዩቲዩብ ቻናልችን ደንበኛ ለመሆን ይመዝገቡ።

See below for some videos from Sodere YouTube channel

Ethiopian Movie Terafiqua Full ትራፊኳ ሙሉ ፊልም


Ethiopian Movie Ye Addis Abeba Habtam Full የአዲስ አበባ ሃብታም ሙሉ ፊልም


Ethiopian Movie Kemaebelu Wedeh Full ከማዕበሉ ወዲህ ሙሉ ፊልም


Ethiopia Yemaleda Kokoboch Final Program


Ethiopia Comedian MESKEREM Bekele Full Comedy Video


Ethiopia – Live poultry market in Abeba for Easter


Ethiopian Movie GEDAMAWITUA Full


Ethiopian Movie Ke Tsion Bestejerba Full ከፅዮን በስተጀርባ ሙሉ ፊልም


Receive Ethiopian News, Movies and Videos by email. Sign up for Email alerts

ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎችን፣ ድራማዎችን፣ሙዚቃዎችን፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በኢሜል አድራሻዎ እንልካለን። ኢሜሎን ያስመዘግቡ።