በአይሲስ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ 6 ኢትዮጵያውያን ማንነት ተለየ 6 Ethiopians who were killed by ISIS identified

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2007(ኤፍ.ቢ.ሲ) ባሳለፍነው እሁድ በሊቢያ ውስጥ በአሸባሪው አይ ኤስ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ኢተዮጵያውያን ማንነት በመለየት ላይ ይገኛል።

በዚህም መሰረት በርካታ የሟች ቤተሰቦች የልጆቻቸውን ሞት ተረድተው ሀዝን በመቀመጥ ላይ ይገኛሉ።

ቀደም ብሎ ኢያሱ ይኩኖአምላክ እና ባልቻ በለጠ የተባሉ የጨርቆስ አካባቢ ተወላጆች የአይ ኤስ ሰለባ መሆናቸው ተለይተው ቤተሰቦቻቸው ሀዘን ላይ መሆናቸው ይታወሳል።

አሁን ደግሞ ወጣት ብሩክ እና ሌሎች ሁለት ወጣቶች የጨርቆስ አካባቢ ነዋሪዎች እንደነበሩም የተለያዩ ምንጮች ጠቅሰዋል።

ሌላኛው በአይ ኤስ የተገደለው ወጣት  በቀለ አርሴማ ይባላል ተወልዶ ያደገው በጉራጌ ዞን በቸሃ ወረዳ ካራቻ የሚባል ቦታ ሲሆን፥  በአሁን ሰዓት ቤተሰቦቹ ተረድተው የአካባቢው ነዋሪዋች ልቅሶ እየደረሱ  ይገኛሉ።

የትግራይ ክልል ተወላጅ የሆኑት እና የመቀሌ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወጣት ዳዊት ሀድጉ እና ወጣት አለም ተስፋዬም የአይ ኤስ አረመኔያዊ ገድያ ሰለባ ሆነዋል።

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ እሁድ ገበያ የሚባል አካባቢ ነዋሪ የሆነው ወጣት መንግስቱ ጋሼም ሌላኛው የአይ ኤስ ሰለባ መሆኑ ተለይቷል።

Subscribe to SodereMovies YouTube channel. የዩቲዩብ ቻናልችን ደንበኛ ለመሆን ይመዝገቡ።

See below for some videos from Sodere YouTube channel
Ethiopian Movie Ye Addis Abeba Habtam Full የአዲስ አበባ ሃብታም ሙሉ ፊልም
Ethiopian Movie Kemaebelu Wedeh Full ከማዕበሉ ወዲህ ሙሉ ፊልም
Ethiopia Yemaleda Kokoboch Final Program
Ethiopia Comedian MESKEREM Bekele Full Comedy Video
Ethiopia – Live poultry market in Abeba for Easter
Ethiopian Movie GEDAMAWITUA Full
Ethiopian Movie Ke Tsion Bestejerba Full ከፅዮን በስተጀርባ ሙሉ ፊልም
Receive Ethiopian News, Movies and Videos by email. Sign up for Email alerts

ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎችን፣ ድራማዎችን፣ሙዚቃዎችን፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በኢሜል አድራሻዎ እንልካለን። ኢሜሎን ያስመዘግቡ።