ጨለማው ሣምንት

ክንፉ አሰፋ

Eyassu Yukunualem and Balecha Belete, ISIS massacred them in Libya. የአይሲስ ሰለባዎቹ እያሱ ይኩኑዓምላክ እና ባልቻ በለጠ

ወጣት እየሩሳሌም አስፋው እንደወትሮው ቴሌቭዥን ከፍታ እየተመለከተች ነው። ብርቱካንማ ቱታ የለበሱና፣ እጆቻቸው የፍጢኝ የታሰሩ ወጣቶች በአሸባሪዎች ታጅበው ሲጓዙ ያሳያል ቴሌቭዥኑ። ለእርድ ከተሰለፉት ወገኖች ፊት ለፊት ላይ ያለው የእየሩሳሌም ወንድም ነበር። ሌላኛው ወንድሟም ከበስተኋላ ተሰልፏል። እያሱ ይኩኑዓምላክ እና ባልቻ በለጠ፤ ሁለቱም በዚያች ቅጽበት ክቡር ነብሳቸውን በግፈኞች ተነጠቁ። ከሁሉም የከፋ የሚያደርገው ደግሞ ወዳጅ ዘመዶች የነዚህን ወገኖች አስከሬን አግኝተው ለመቅበር እድል እንኳን ባለማግኘታቸው ነው። የሁሉንም ልብ የሚሰብር ክስተት!

ሙሉውን አስነብበኝ …