በአሜሪካ የመሸገው የሳሙኤል ዘሚካኤል ደቀ-መዝሙር
ክንፉ አሰፋ
“አሜሪካ ይዞን ከሄደ በኋላ በዋሽንግተን ዲሲ አንድ የገበያ አዳራሽ (ሞል) ውስጥ ጥሎን ጠፋ … ፖሊስ ሁለት ግዜ ይዞን ነበር … በርሃብ ተቀጣን፣ ርሃብ ጸንቶበት ሆስፒታል የገባም ልጅ አለ። … በየሬስቶራንቱ እየዞርን ለምነናል።” ይላል አንድ የ11 ዓመት ሕጻን ሳይንቲስት። ሂውስተን ቴክሳስ ያሚገኘውን ናሳ የጠፈር ምርምር ተቋም ለመጎብኘት ከአዲስ አበባ ሄደው ነው አስሩ ሕጻናት ዲሲ ላይ የሚሰቃዩት።