የሰባት ቀናት ጸሎተ ምሕላ ታወጀ


የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጣው መግለጫ ከነገ ሚያዝያ 14 ቀን ጀምሮ ለሰባት ቀናት ጸሎተ ምሕላ ዐወጀ፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ በአሸባሪዎች የተፈጸመውን ድርጊት አውግዞ ባወጣው ባለ ዘጠኝ ዐንቀጽ መግለጫ ለሰማዕታቱ ተገቢውን ቀኖናዊ ክብር እንደሚሰጥ ገልጧል፡፡ ለዚህም የሰማዕታቱን ቤተሰቦች የመረጃ ትብብር ጠይቋል፡፡ ‹‹የጀግና እናት አታለቅስም›› ያለው መግለጫው የሰማዕታቱ ቤተሰቦች የልጆቻቸው ሰማዕትነት በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ ስላለው በዚህ እንዲጽናኑ አደራ ብሏል፡፡ ለወደፊቱ ተመሳሳይ ችግር እንዳይከሰት ከመንግሥት ጋር አብሮ የሚሠራ ዐቢይ ኮሚቴ እንደሚያቋቁምም ገልጧል፡፡
መግለጫውን ቀጥሎ ያንብቡት
በተያያዘ ዜና ዛሬ ከሰዓት ዐሥር ሰዓት ላይ በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ወደ ሰማዕታቱ ቤተሰቦች በመሄድ ጸሎት እንደሚያደርጉና እንደሚያጽናኑ ተነግሯል፡፡  
ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲህ ሲሠራ ‹ሲኖዶስ ሲኖዶስ› ይላል፡፡