የአይነ ምድር ቀለም ከበሽታ ጋር ይያያዛል?

(በቴክኖሎጅስት ዳንኤል አማረ)

ብዙ ሰዎች የሚፀዳድት አይነ ምድር ቀለም ከበሽታ ጋር የተያያዘ ነው ወይ ብለው መጠየቅ የተለመደ ነው በመሠረቱ ስጋት ውስጥ ሊከቱን የሚችሉ የአይነ ምድር ቀለም ለውጦች ቢኖሩም ጠቅለል አድርገን ስንመለከተው ግን የአይነ ምድር ቀለም ትክክለኛው ቀለም ላይሆን ይችላል።
አይነ ምድር በአብዛኛው ቢሊሩቢን በሚባል ቁስ ነገር ምክንያት ነጣ ያለ ቡናማ ወይም ቢጫ ቀለም ይኖረዋል። ይህ ቢሊሩቢን ከብረት ጋር በአንጀት ውስጥ ሲቀላቀሉ አይነ ምድራችን የሚያምር ቡናማ ቀለም እንዲኖረው ያደርጋል። አይነ ምድራችን ልክ እንደቀስተ ደመና የተለያዩ አይነት ቀለሞች አሉት እነዚህን ቀለሞች እስኪ በዝርዝር እንመልከታቸው።

ጥቁር ቀለም
አይነ ምድራችን ጥቁር ሆነ ማለት ከላይኛው የጨጓራና አንጀት ክፍል፣ ጉሮሮ፣ ሆድ ወይም የትንሹ አንጀት የመጀመሪያ ክፍል አካባቢ የሚነሳ/የሚመጣ ደም አለ ማለት ነው። ከነዚህም በተጨማሪ ሊድ፣ ከብረት የተሰሩ የወሊድ መቆጣጠሪያዎችና ብሉ ቤሪ ጥቁር ሊያደርጉት ይችላሉ።

አረንጔዴ ቀለም
አረንጔዴ ቅጠላማ አትክልቶች ክሎሮፊል አላቸው ይህ ክሎሮፊል አይነ ምድርራችን አረንጔዴ ቀለም እንዲይዝ ያደርጋል በተጨማሪም የሀሞት ፈሳሽ ምንም ይዘቱን ሳይቀይር በአንጀታችን ውስጥ ሲያልፍ አረንጔዴ ቀለም ያለው ተቅማጥ ያስቀምጠናል። ጡት በሚጠቡ በተለይም ገና የተወለድ ህፃናት አረንጔዴ ቀለም ያለው አይነ ምድር የተለመደ ነው።

ቀይ ቀለም
ደማቅ ቀይ ቀለም ያለው አይነ ምድር የሚፀዳድ ከሆነ በታችኛው የጨጔራና የአንጀት መስመር ደም መፍሰስ ሲሆን ለአይነ ምድር ቀይ መሆን የተለመደው ምክንያት ክንታሮት ነው። በተጨማሪም ስኳር ድንችና ቲማቲም ቀይ እንዲሆን ያደርጋሉ።

ግራጫ ቀለም
የጉበት፣ ጣፊያ እና የሀሞት ከረጢት በሽታዎች ሲኖሩብን አመድማ የደበዘዘ ግራጫ ቀለም አይነ ምድር ይኖረናል።

ቢጫ ቀለም
ቢጫ አይነ ምድር እንዲኖረን ከሚያደርጉ ነገሮች አንድ ጃርዲያ የተባለ የፓራሳይት በሽታ ነው። ጂያርዲያ ተቅማጥን ያስከትላል። ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ጂልበርት ሲንድረም የተባለ የቢሊሩቢን መጠንን የሚጨምር የዘረመል በሽታ ነው።

መልካም ጤንነት።

Like my Facebook page for more news.https://www.facebook.com/Danieltechnologist