የምናዝነው ስንት ሰው ሲሞት ነው? – ዳንሄል ክብረት
በየመን፣ በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ስለሚሞቱት ዜጎቻችን የሚሰጡት መንግሥታዊ መግለጫዎች ሁለት ነገር የጎደላቸው ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ሰብአዊ ስሜት፡፡ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ስለሌላው ሰብአዊ ፍጡር መከራና ስቃይ ሲሰማ መጀመሪያ አንዳች የኀዘን ስሜት ይሰማዋል፡፡ ከዕውቀት ይልቅ ስሜት ለሰዎች ቅርብ ነውና፡፡ ባለሥልጣን ቢሆን፣ ፖሊስ ቢሆን፣ ዳኛ ቢሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሆን ሰው ነውና ስሜት አለው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ያዝናል፣ ይከፋዋል፣ ልቡ ይረበሻል፣ ሆዱ ይባባል፣ ኅሊናው ይደማበታል ተብሎ ይታመናል፡፡ ስለዚህም የመጀመሪያው ሥራው ማዘን ቀጥሎም ኀዘኑን በወጉ መግለጥ ነው፡፡
ሰሞኑን የማያቸው መግለጫዎቻችን ግን የኀዘን ወግ በሀገራችን የሌለ የሚያስመስሉ ናቸው፡፡ መሪዎቻችን ወደ አደባባይ ወጥተው ለሞቱት ወገኖቻችን እንደ ኢትዮጵያዊነት ኀዘናቸው የሚገልጡት፣ ጥቁር ልብስ ለብሰው የምናያቸው፣ ነጠላ የሚያዘቀዝቁት ስንት ሰው ሲሞትብን ነው? የሚያስብሉ ናቸው፡፡ ኀዘንኮ ፖለቲካ አይደለም፣ ፓርቲ አይደለም፣ ርእዮተ ዓለም አይደለም፣ ሊብራልም አብዮታዊ ዲሞክራሲም አይደለም፡፡ ኀዘን ሰብአዊነት ነው፡፡ የሚመራቸው ዜጎቹ፣ የሚያሠማራቸው በጎቹ ሲታረዱና ሲሞቱ ኀዘኑን በይፋ የማይገልጥ መሪና እረኛ መቼ ነው ኀዘኑን የሚገልጠው?
ዜጎቹ በሕገ ወጥ መንገድም ይሂዱ በሕጋዊ፣ ድንበር ጥሰውም ይሂዱ በአውሮፕላን ተሳፍረው፤ መጀመሪያ ሰዎች፣ ቀጥሎም የዚህች ሀገር ዜጎች ናቸውና ኀዘን ይገባቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ሰው አገኘዋለሁ ብሎ ከሚያስበው ክብር አንዱ በሞቱ ጊዜ የክብር ልቅሶና ኀዘን ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ከአካባቢያቸው ላለመራቅ፣ ከራቁም ለመመለስ ከሚሰጧቸው ምክንያቶች አንዱ ‹በክብር ዐርፎ በክብር መቀበርን፣ የክብር የኀዘን ሥነ ሥርዓትን ማግኘትን› ነው፡፡
ካገሬ እንዳወጣህ አገሬ መልሰኝ
በሹም የታዘዘ አፈር አታልብሰኝ፤
እንኳን የሚቀብረው የሚያዝንለት አጣ
ምን ወግ ማረግ ያያል ካገሩ የወጣ፤
የሚሉት ለዚህ ነበረ፡፡
የመንግሥት አካላት ለምን ይኼንን ለመዘንጋት እንደፈለጉ አልገባኝም፡፡ የደቡብ አፍሪካው ቃጠሎና ግድያ ሲመጣ የሀገራችን ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ብቅ ብለው ‹‹በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ባለው ነገር ከልብ እናዝናለን፣ ከደቡብ አፍሪካ መንግሥት ጋር ተነጋግረን አስፈላጊውን እናደርጋለን፤ ተመሳሳይ ችግር ለወደፊቱ እንዳይከሰትም አንሠራለን› ዓይነት ሰውነት ያለበት መግለጫ ጠብቄ ነበር፡፡ የለም፡፡ ሲሆን በሀገራችን የልቅሶ ሥነ ሥርዓት መሠረት፡፡ አሁን ደግሞ ዓለም ያወቀው አሸባሪ ‹አይ ሲስ› ኢትዮጵያውያኑን በክርስትና እምነታቸው ብቻ ሲሠዋቸው የተሰጠው መግለጫ ስሜት የሌለበት፣ ማዘን መደሰታቸውን የማይገልጥ፣ እንኳን ሰው እንስሳ የሞተብን የማያስመስል ሆነ፡፡ ከማጣራቱም ከምኑም በፊትኮ ስሜቱ ይቀድማል፡፡፡ አዝናችኋል ወይ? ስትሰሙና ስታዩ ምን ተሰማችሁ? የአሜሪካ መንግሥት እንደዚያ ዓይነት መግለጫ ሲያወጣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ያንን ነው ወይ መስማት ያለብን? ለመሆኑ መሪዎቻችን ኀዘናቸውን የሚገልጡት ምን ስንሆን ነው? ለምንድን ነው ሁሉም ነገር ፖለቲካ የሚሆነው?
ሁለተኛው የሚጎድለው ነገር ደግሞ ፍጥነት ነው፡፡ አትሌቶቻችን በኦሎምፒክ ሲያሸንፉ የባለሥልጣናቱ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት ሯጮቹ ቆርጠውት ካለፉት ሪቫን ቀጥሎ የሚመጣ ዜና ነበር፡፡ አትሌቶቹ ደክሟቸው ከመሬት ሳይነሡ የባለሥልጣናቱ መልእክት ለሚዲያ ይደርስ ነበር፡፡ በዚህ የሁላችንም ኀዘን በሆነው ጉዳይ ግን ለምን መዘግየት እንደተመረጠ ግልጽ አይደለም፡፡ ማጣረቱ፣ መረጃ መሰብሰቡ፣ ተጨማሪ የዲፕሎማሲ ሂደቶችን መሄዱ ጊዜ ይወስዳል፡፡ ማዘን ግን ጊዜ አይወስድም፡፡ ቪዲዮው ተለቅቋል፡፡ ሲሞቱ እያየን ነው፡፡ መልካቸው የኛው ነው፡፡ አይሲስ የገደላቸው ‹ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች› ብሎ ነው፡፡ የዓለም ሚዲያዎች ያንኑ እያስተጋቡ ነው፡፡ ይኄ ለኀዘን ያንሳል? አፈፍ ብሎ ተነሥቶ ‹በሆነው ነገር እናዝናለን፤ ልባችን ተነክቷል፤ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፤ ዝርዝሩን በየጊዜው እንነግራችኋለን› ለማለት ስንት ሰዓት ይወስዳል? የደቡብ አፍሪካው ችግር ደረሰ እንደተባለ ሙጋቤን ለውግዘት የቀደማቸው የለም፡፡ የኛዎቹስ የት ሄዱ?
መንፈሳዊ መሪዎችስ የት ናቸው? አንዳንዶቹ ውጭ ሀገር መሆናቸው እየተሰማ ነው፡፡ ሲሆን ይህንን ሲሰሙ አቋርጦ መምጣት፤ ካልሆነም ባሉበት ሆኖ አባታዊ ኀዘንን መግለጥና በእምነቱ የሚገባውን ማድረግ ይገባ ነበር፡፡ ሲኖዶሱስ ምን እየሠራ ነው? አልሰማም ይሆን? ዛሬ ጠዋት ቢያንስ በአዲስ አበባ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎት መደረግ አልነበረበትም? ባፈው ካይሮ ሄዳችሁ ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን ምንድን ነው ያያችሁት? በጎቹ እረኛ የላቸውም ማለት ነው? አባቶች የሚያዝኑት ምን ሲገጥማቸው ነው? እረኛው የሚያለቅሰው ስንት በጎች ሲታረዱ ነው?
ቤተ ክርስቲያኒቱ ነገሩን በዝምታ የምታልፈው ከሆነ እኛ እንደ ጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊ ቀኖና እነዚህን በክርስትናቸው ምክንያት የተሠው ክርስቲያኖች ‹ሰማዕታተ ሊቢያ› ልንላቸው ይገባል፡፡ የሰማዕትነታቸውንም በዓል ማክበር አለብን፡፡ በስንክሳሩ ማስገባት ባንችል ታሪካቸው በኅዳጉ ማስፈር አለብን፡፡ ማንም ይሁኑ ማን፣ በሚገባ የተማሩም ይሁኑ ያልተማሩ፣ ከመካከላቸው የማያምኑም እንኳን ቢኖሩ የተገደሉበት ምክንያት ክርስትና ነውና ሰማዕታት ናቸው፡፡ ያውም ‹ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት›፡፡ በስንክሳሩ እንደምናነበው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን የክርስቲያኖች መንደርና ቤተ ክርስቲያን እየተወረረ ክርስቲያኖቹ ሲሠው ገና ያልተጠመቁት፣ ነገሩ ያልገባቸው፣ ክርስትናን ለመቀበል ያልወሰኑት ሁሉ አብረው ተሠውተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን የተሠውበት ምክንያት ክርስትና በመሆኑ ሁሉንም ሰማዕታት ብላቸዋለች፡፡ የእነዚህም ክብር እንዲሁ ነው፡፡
እነርሱ በሰማይ ዋጋ አላቸው፡፡ አክሊለ ሰማዕታትንም ተቀብለዋል፡፡ እኛ ግን ሰማዕታቱን ባለማክበራችን ክብር ይጎድልብናል፡፡ ‹በረከታቸው ይደርብን› እንጂ ‹ነፍስ ይማር› አንልም፡፡
…ባንዳ ላይ ይትፉና !!!…ባንዳ ላይ ይትፉና !!!…ባንዳ ላይ ይትፉና !!!
+++ የማከብርህ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
ዳንኤል ክብረት እና የኔ እህት፤
በአንቺ ማልቀስ የጀመርሺው ዛሬ ነው፤ዕውነቴን ነው የምነግርሽ፣ብታምኚም ባታምኚም እኔ ማልቀስ የጀመርኩት ከሃያ አራት ዓመታት በፊት ነው፤ገና ጉጅሌዎች ለሥልጣን ማጭበርበር ሳይበቁበ።ዛሬ ዛሬማ፣-ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም እንዳሉት ሁሉም አገሮች ኢትዮጵያውያንን ጠልተው ብቻ አላበቁም።ከመገደልም በላይ ጉጅሌዎች በመንግሥትነት የኢትዮጵያን ሕዝብ ሥልጣን ቀምተው በዝምታቸው እኛ በቁማችን መሞታችንን እያሳዩን ነው።እንደዚህ መደረጋችንንም እንዳናምንና ዋናውን ሥጋዊውንና መንፈሳዊ የታሪክ ጠላታችንን እንዳናውቅ ራሳቸውን ደብቀው በደቡብ አፍሪቃ በወገኖቻችን ላይ በስተጀርባ ሆነው ጉጅሌዎች ያስደረጉትን ግድያ በብልህነት በጥንቃቄ መመርመር ይጠበቅብናል።
ቀልድም ውሸትም አይደለም፤እርኩሳን በዓለም ላይ እንደአሸዋ በዝተው ወረዋታል።ፈጣሪዎች እኛ ነን የሚሉ በገንዘብ የሰውን ልጅ ለመግዛት ችለው አሁን ደግሞ አገርን አይደለም፤ዓለምን ለመግዛት መጀመሪያ ዕምነትን ከምድር ላይ ለማጥፈት በጨለማ በየቀኑ የማያደርጉት የለም።ኢትዮጵያ ደግሞ አንዷ እና ቀንደኛዋ ተፈላጊ አገር ናት።አለማወቅ ጠቃሚ የሚሆነው እስከምናውቅ ድረስ ብቻ ነው፤ከዚያ በኋላ እንደሰው ማሰብ ስለምንጀምር የራሳችንን ሕልውና ውስጥ ስለምናስገባ ለሕዝቦች ነፃነት ስንል እንደ አርበኛ አንዳርጋቸው ፅጌ ራሳችንን መቶ በመቶ አሳልፈን ለመከራ እንሰጣለን።ይህም የመረረ ውሳኔ ከሰብዓዊ ምርጥ ሰዎች ጋር ያስቆጥረናል።ማህተመ-ጋንዲም ሆነ ማርቲን ሉተርኪንግ አሊያም ማንዴላ የዚህ አስተሳሰብ ውጤቶች ናቸው።መስዋዕትነቱ ግን የሕዝቦች ሆኖ ውጤቱ ግን በአንድ ግለሰብ የድል-ዝና ይቋጫል።ሐቁ ግን አሁንም ሕንዶች፣ጥቁር አሜሪካኖችም ሆኑ፣የደቡብ አፍሪቃ ሕዝቦች ነፃነት የግለሰቦችን ሥም ከማስመዝገብ እና ወደሚቀጥለው የትግል ዓይነት ከመሸጋገር ሌላ የተለየ ለውጥ አልተገኘም።ያንን የድለዝና ከኢትዮጵያ የነፃነት ዘመን አንፃር ሲመለከቱት ከቁጥር አለመግባቱን በጥልቀት ተገንዝበውታል።እንደውም የኢትዮጵያ የቆዳን ዘረኝነት በዳግማዊ አፄ ምኒልክ የአድዋ ድል መገሽለቱ ከአሥራ ስምንተኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩት የባርነት ዘመናት ወደመቃብራቸው ለታሪክ መዝገብ ለመወርወር ያበቃቸው አቢይ ሽንፈት መሆኑን በጥልቀት ተገንዘበዋል።ያንን የፈረንጅ(ሰላቶ) የበላይነት የታሪክ ሽንፈት ከክርስቶስ ልደት በፊትም የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላት በነበረው የሮማውያን በትረ-መንግሥት አዝማችነት እንደገና በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ-መግሥት ጀርመን እና እንግሊዝን አስከትሎ ወደ አገሪቱ ሰርጎ ቢገባም በአርበኞቻችን የአምስት ዓመታት ትግል እና በቀዳማዊ ኃይለ-ሥላሴ የዲፕሎማሲ ውጤት ኢትዮጵያ በነፃነቷ ያልተደፈረች መሆኗ በተባበሩት መንግሥታት ሊመዘግብላት ችሏል፤ሆኖም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጨረሻ ጀምሮ ኢትዮጵያን የሚጠብቃት እግዚአብሔር የኤሮፓውያንን ወረራ እንደባቢሎን ግንብ እንዳይግባቡበት አድርጎ አዋርዷቸዋል።ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መሠረታዊ ጠላት የሆነችው የሮማውያን መንግሥት በእንግሊዝ ሥርወካቶሊክ መንግሥትነት በመተሳሰር በድብቅ ፈንጂ ችግሮችን ቀብረው(የአባይ፣የኤርትራ፣የአርበኞች ቤተሰብን ማግለል፣የባንዳ ልጆችን ለመንግሥት ስልጣን ማብቃት፣ወዘተ)በመውጣታቸው ታሪክ መዝግቦት ዛሬ የልጅ ልጆቻቸው የተጀመረውን ኢትዮጵያን እና ኢትዮጳውያንን የማጥፋት ተግባር ቀጥለውበታል።መፍትሔው ለማይቀረው እና አብረን ለተፈጠርንበት የሥጋ ሞት ቦታ ሳንሰጥና ፆም እና ፀሎታችንን ሳናቆም ለኢትዮጵያ መዋጋት ነው።ለዚህም ቸሩ እግዚአብሐር ይርዳን፤ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር። ፨፨፨፨፨፨* * * * *ላናበቡት እንዲያነቡት ለ፯ ሰዎች ብቻ ካስተላለፉ፤የእግዚአብሔር ቸርነት፣የክርስቶስ መሪነት፣የቅድስት ማርያም አማላጅነት ከናንተ ጋር ይሁን።የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ሁሉ አላህ ክብረቱን ይሰጣችሁ ዘንድ አመሰግናችኋለሁ።
በመጀመሪያው የሕሊና ዳኝነት ጥያቄዬ የተዋሕዶ ዖርቶዶክስ ዕምነትህን በማይነካ ሒስ በፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም ሲሰነዘርበህ አነበብን፤በሁለተኛው የመጋለጥ ተኩስ ደግሞ በወጣት ኤርሚያስ ለገሰ በሳል መጠይቆች አደባባይ ተጠራህ።በጉጅሌ አገር የማጥፋት ተንኮል እንደክርስቲያናዊነትህ ብርቱም ግልፅም ሆነህ አላገኘሁህም።ምንም አላልኩም፤ምክንያቱም እኔ ማነኝ እና ከማየት ሌላ እንዳነተ ያለውን መንፈሳዊ መምህር ልዘረጥጥ እችላለሁ??? እናም በአክብሮት እየጠበቅንና እያየን ነው፤ዲያቆንም ባንዳ ላይ ምራቅ ሳይሆን ሐቁን “ሓቅ!!!”ብለህ ካንጀትህ በማውጣት ስትተፋ።መልሱንም ለማንበብ እየተዘጋጀን ነው፤ለወኔም እንዲረዳህ በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ፡ንጉሤ ግጥም የታመሰ የራሴን ሥነ-ግጥም፣ ባንዳ ላይ እንድትተፋ ሰንዝሬልሃለው።
ምላሹን ለሕዝብ ካልሰጠህ፣ከእነ መሐሙድ አህመድ እና አስቴር አወቀ ጋር በከሐዲነት በሰልፍ ለታሪክ ትቆጠራለህ+++ለእነ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ለ«ወቸገሉ ዜናዊ» የሕዝብ ንብረት በሥጦታ ካበረከቱ፤የኢሠፓ ባለሥልጣን የነበሩና ተደብቀው ሁለገብ የምክር አገልግሎት ለጉጅሌው የሚሰጡ፣በውጭ እና ባገር ቤት ሆነው ድርጅቶችን በማንቀሳቀስ ለሥልጣንና ለጥቅማቸው ሲሉ በእምነት ድርጅቶች የተሰገሰጉ፣ለጉጅሌው በድል አጥቢያ አርበኛነት እየተመረጡ እንደ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚጋለብባቸው እና ሌሎችም የባንዳዎች ቡድን አገልጋዮች የ”በቃ”ጥሪን እንድትቀበሉ አሳስባለሁ።
ተው ስማኝ አገሬ!!!
ኸረ! ስማኝ አገሬ!!!
“…ምን፡እንባ፡ነበረሽ፡ከራሔል፡ያነሰ፤
እንባ፡አይመስልም፡እንባ፡ጊዜው፡ካልደረሰ።
መራራው፡ሐዘንሽ፡እንባ፡እያፈሰሰ፥
የልጆችሽ፡ርስት፡እንዴት፡ተወረሰ።…”
የቀኝ፡ጌታ፡ዮፍታሔ፡ንጉሤ(ባ፲፱፻፴-፴፩፡ዓ.ም.፡የተዘመረ)
…ባንዳ ላይ ይትፉና !!!…ባንዳ ላይ ይትፉና !!!…ባንዳ ላይ ይትፉና !!!
የምን ጠጋ ጠጋ ? ? ?…የምን ልጥፍ ልጥፍ፤
የምን መተሻሸት…፣የምን ውትፍ ውትፍ።
እኮ ለምን ጥፍት፤አረሳስቶ ምጥት፤
የምን ብቅ ጥልቅ፤የምን ግብት ውጥት።
የምን መልመጥመጥ ነው፤የምን ደፋ ቀና? ? ?…
የሚፈሰው ደሙ መቼ ደረቀና።
ድንጋይ ያቀበሉ ስንሞት ትናንትና፤
እንዴት ተመለሱ…እየሞትን ገና…???
ሕዝቡን በአደባባይ መቼ ጠየቁና፤
እንዴት ወደ መድረክ መጡ እንደገና ? ? ?
እናም ያለፈ አልፏል ይቅር ትናንትና፤
እስኪ ዛሬ ያሳዩን ባንዳ ላይ ይትፉና።
በትዕግስቱ ጥበብ ይታወቃል ሕዝቡ፤
ይቅርታ ለማለት ብዙ ነው ሰበቡ።
እናም ያለፈ አልፏል ይቅር ትናንትና፤
እስኪ ዛሬ ያሳዩን ባንዳ ላይ ይትፉና።
በመድረክ ላይ ወጥተው መዝፈን ሳይጀምሩ፤
ይቅርታቸው ይቅደም ባንዳ እንደነበሩ።
አለበለዚያ ግን ይወጣል ሚሥጥሩ፤
በባንዳነታቸው ማን ምን እንደሰሩ።
ታሪክ ይናገራል ዛሬ ካልተናገሩ፤
ጥላቻም አይደለም ሞልቷል ምሥክሩ።
እኮ ምን ተገኝቶ አጨብጫቢዎቹ
በዚህ በዚያ ገብተው እዚህ ተከማቹ???
የምን ጠጋ ጠጋ ? ? ?…የምን ልጥፍ ልጥፍ፤
የምን መተሻሸት…፣የምን ውትፍ ውትፍ።
እኮ ለምን ጥፍት፤አረሳስቶ ምጥት፤
የምን ብቅ ጥልቅ፤የምን ግብት ውጥት።
የምን መልመጥመጥ ነው፤የምን ደፋ ቀና? ? ?…
የሚፈሰው ደሙ መቼ ደረቀና።
ይቅርታን ነፍገው ሕዝብን እንደናቁ፤
እንዴት ባደባባይ ለመታየት በቁ?????
ቀረ’ኮ ይሉኝታ ቀረ’ኮ መደበቅ፤
በጉጅሌ ጉያ ሕዝብ ላይ መሳለቅ።
መሓሙድም ሆነ እነአስቴር አወቀ፤
ሕሊናቸው ትናንት የተጨማለቀ፤
ምን ምን እንዳደረጉ ሕዝቡ እያወቀ፤
እንዴት ባንዲት ጀንበር ግፋቸው ተፋቀ???
ይሁን እሺ አልፏል ይቅር ትናንትና፤
እስኪ ዛሬ ያሳዩን ባንዳ ላይ ይትፉና።
በመድረክ ላይ ወጥተው መዝፈን ሳይጀምሩ፤
ይቅርታቸው ይቅደም ባንዳ እንደነበሩ።
ዛሬም እነሱን አይተው የሚጨማለቁ፤
የሕዝብ እንዲሆኑ እውነቱን እንዲያውቁ፤
ድንጋይ ያቀበሉ ስንሞት ትናንትና፤
እስኪ ዛሬ ያሳዩን፣
ባንዳ ላይ ይትፉና …!!!
የማይቀረው ጊዜ እየመጣ ነውና ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በጊዜ እንድትወስኑ የ”በቃ”ጥሪን እንድትቀበሉ አሳስባለሁ።
በሌላ በኩል፣
ወቸገል ዜናው የተቀሰፈ ቢሆንም፣በድኑን ኢትዮጵያውያን ለፍትህ እስኪያቀርቡት እና ሰይጣን ቶሎ ስለማይለቅ ነውና ጠበል የሚያስፈልገው በሕይወት ያሉት እንዲፈወሱ ንስሓ ሊገቡ ይገባዋል፤እናም«ወቸገሉ ዜናዊ » ወደ ምድር እንዳይቀበር እና እንዳይበሰብስ በሕዝብ ስም ማደንዘዣ እንዲወጋ እንጠይቃለን።
ወቸገል ዜናዊ፤ አይቀበር!!!
የኢትዮጵያውያንን ደም ያጠጣ እንደ-ነበር፤
መረጃ ስለአለን መለስ አይቀበር።
«ወቸገሉ» ዜናዊ ፍፁም አይቀበር፤
የኢትዮጵያ ፍትሕ መስጠት እስኪጀመር።
አይቀበር ሥሙ እሱ ብሎ መለስ፤
ገሃነም በስብሶ ከነ-አፅሙ ይመለስ።
መች-ተነግሮ ኅጢያቱ ገና-አለቀና፤
በ”ቅበሩት እርሱት” ይነገራል ዜና።
በራአይ አባዜ በጥቅማቸው ልሳን፤
ሕዝብን እንዲያ የከዱ ዛሬም ያልተረሳን፤
እንደ ውሻ ትፋት የሚልሱትን አይተን፤
ድንጋይ ዳቦ ሲሉ በጆሯችን ሰምተን፤
ከፊት ለፊት ሆኖ ሲያሻው ተደብቆ፤
ሕዝብን የገደለ ያስገደለ አንቆ፤
ደላላው ማን ነበር ትዕቢት የቆዘረው፤
እንደሞሶሎኒ ዘር-ባይኑ የቆጠረው፤
መለስ-ነው-ለገሠ በባንዳ ልጅነት፤
እንዲያ የቀሰፈው የእኛ ኢትዮጵያዊነት።
ባደባባይ ሕዝቡን ሲሰድብ የነበረው፤
በበድኑ ሳናጠምድ እንዴት እንቅበረው?
ይቀበር አትበሉኝ መቼ ቀን ሞተና፤
የውሸት ታሪኩ ደም አልጠጣም ገና።
መዘዙ ብዙ ነው ይንጋ ጊዜው ይምጣ፤
ይህ አጋዚ ሳይፈርስ እውነቱም አይወጣ።
እናም የባለራዕዮች ታሪክ እስኪነገር፤
በድኑ ለፍርድ ሳይቀርብ ፍፁም አይቀበር።
የውሸት ታሪኩ ባገር እስኪነገር፤
ወቸገል ዜናዊ፤
የለም አይቀበር!!!
እውነት የሀዘን ቀን ነው.በኢትዮጽያ ትቪ ዘፈን ይዘፈናል ይገርማል .ዘማሪ ሀብታሙ ሽብሩ የሀዘን ቀን ዛሬ ነው የጨለማ ቀን ዛሬ ነው ብሎ ለመለስ ዜናዊ ዘመረ ለዚህሁሉ መከራ ለአበቃት ክፉ መሪ.ለእውነት ዛሬ ነው የኢትዮጵያ ህዝብ ወጥቶ ደረቱን መድቃት ያለበት የጨለማ ቀን ዛሬ ነው የሀዘን ቀን ዛሬ ነው. የኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ደወሉን መደወል ሁሉም በየጠቅላይ ግዛቱ እግዚኦ ማለት አለብን አሁን ነው የረገጥነውን ባንዱራችንን አንስተን ኡ ኡ ኡ ኡ ኡ የአምላክ ያለህ ብለን መጮህ ያለብን.ያሉት ፓትርያርክ አቡን እንቢ ቢሉም ህዝቡ መውጣት እና እግዚኦ ማለት አለበት
እነዚህ ኢትዮጽያን እኾ መጠራት ያለባቸው ዳግማዊ አቡነ ጴጥሮስ ነው እስከ አሁን ማንም ለሀይማኖቱ ለእገሩ የሞተ የለም። አሁንም የኢትዮጵያ የቤተክርስቲያን የአቡነ ጳውሎስን ሐውልት የመለስን ሐውልት ተነስቶ በነዚህ ሰማእታት የኢትዮጵያውያን መተካት አለበት ለነሱ ነው የሚገባው.
This is not the first time that followers of the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church were slain for their beliefs. We all remember the beheading of the clergy and followers of a church in Jimma area. The Patriachate did not only condemn but kept silent. Instead, it condemned Mahibere Kidusan as an extremist group and joined hands with the government to decimate it. Thousands of Ethiopians who were migrating in search of a better life have been drowned in the high seas. Look at what is happening to the Ethiopian young people in South Africa. All are labelled as ‘illegal migrants’ which the claiming no responsibility for the loss of their lives. Those who have the opportunity of accessing the popes should tell them not to align with the political leadership and worldly comfort and cry for the poor.