ሆስኒ ሙባረክ አዲስ አበባ አይሄዱም
ግብፅና ኢትዮጵያ በዓባይ ጉዳይ ቀደም ሲል፣ በቅኝ ግዛት የተደረሰባቸውና ኢትዮጵያን ያገለሉ ሁለት ስምምነቶች (ማለትም እ.ኤ.አ. የ1929 እና የ1959) የናይልን ውኃ ግብፅንና ሱዳን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስለነበሩ ይህ ሁኔታ እንዲስተካከል ከአፄ ዮሐንስ 4ኛ ዘመን ጀምሮ ጥረት ቢደረግም የግብፅ ወራሪዎች በኢትዮጵያን ላይ ጦርነት ቢሰብቁም በአፄ ዮሐንስ 4ኛ አማካይነት ለሦስት ያህል ጊዜ ሽንፈትን ተከናንበው ተመልሰዋል።
ይሁንና የኢትዮጵያን ሰላም የማይፈልጉት እነዚሁ ግብፆች የግብፅ ፕሬዚዳንት በነበሩት አንዋር ሳዳትና የአሁኑ ፕሬዚዳንታቸው ሆስኒ ሙባረክ ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ጀምሮ፤ የዛሬዋን ኤርትራን በማስገንጠልና በሶማሊያ የነበረው የዘይድ ባሬ መንግሥትን በመበታተን ሶማሊያን መንግሥት አልባ ያደረገውን የደርግ መንግሥትን እንዲወድቅ ፤ከፍተኛ እርዳታ በአሁኑ ወቅት ፊትና ጀርባ ለሆነው ለወያኔ መንግስት በመርዳት፤ ዛሬ ውጥንቅጧ የወጣችውን ሀገር የአሁኑ ትውልድ እንዲረከብ አድርገውታል ።
ግብፅ በአካባቢው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ዓማፂዎችን በመርዳት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለመሆን የቻለችው ለኢትዮጵያ አዝና ሳይሆን የራሷን አድቫንቴጅ ለመጠበቅ ጭምር ነው፡፡
በቅርቡ በአምስት የተፋሰሱ አባል አገሮች የተፈረመውን አዲስ ስምምነትም ግብፅና ሱዳን ለመፈረም ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡የግብፅ ፕሬዚዳንት በተለይም ግብፅ የናይልን ምንጭ ለመቆጣጠር ባላት ታሪካዊ ሕልም፣ ኢትዮጵያን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለማተራመስ ስትሞክር ቆይታለች፡፡ ይሁንና ግብፆች እራሳቸው ሲተራመሱ ያታያሉ።
ግብፆች በየዓመቱ አምስት ቢሊዮን ዶላር ለጦር መሣሪያ መግዣ ከአሜሪካ መንግስት በእርዳታ ያገኛሉ፡፡ በየዓመቱ አዳዲስ መሣሪያ በመግዛት መልሰው ያጠፉታል፡፡ይህም ከኢትዮጵያ ጋር አንድ ቀር ለማይቀረው ጦርነት በተጠንቀቅ መቆማቸውን የሚያሳይ ነው።
በቅርቡ ግብፅ ኢትዮጵያን ለመውረር ታስባለች የሚለውን የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስን የአፍ ወለምታን ጨምሮ የኢትዮጵያና የግብፅ ባለሥልጣናት ከዚህ ቀደም እርስ በርስ የቃላት ጦርነት ሲያደርጉ ኖረዋል፡፡የዓለም መገናኛ ብዙሐን ጉድ እስኪል ድረስ።
አሁን ደግሞ ከአፍሪካ ኅብረት ጉባሄ ላይ ቀርተው የማያውቁትና ወያኔን በመርዳት ስልጣን እንዲቆናጠጥ ያደረጉት የግብፁ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ በያዝነው ወር በአዲስ አበባ በሚካሄደው የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ላይ እንደማይካፈሉና በሳቸው ምትክ ጠቅላይ ሚኒስትራቸው አህምድ ናሲፍ ግብፅን ወክለው እንደሚሳተፉ የግብፅ ድረ ገፅ የሆነው አህረም ኦንላይን ይፋ አድርጓል።
እንደ ድር ገፁ ገለፃ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ በጉባሄው ላይ የማይገኙት በዓባይ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር በተፈጠረው አለመግባባት የተነስ መሆኑን ገልጿል። ሌላው ለግብፅ አሳሳቢ ጉዳይ የሆነው በደነቡ መሠረት ከ60 በመቶ ድምፅ በላይ ካገኘ መንግሥት መመሥረት ይችላል የተባለው የደቡብ ሱዳን መንግሥት ጉዳይ ሲሆን በዚሁ መሠረት 60 በመቶ ደመፅ ለማግኘት በመቻሉ ከግብፅ ጋር ወግኖ የነበረው የሱዳን መንግሥት አቋም ለሁለት የሚከፍል በመሆኑ በተለይም ግብፅን የሚረዳውን ሀሳብ የሚያፈረስ አዲስ ክስተት ሊፈጠር ይችላል በማለት አገሪቱን እንዳስጨነቃት የፖለቲካ ተንታኞች እየገለጹ ነው፡፡
ምክንያቱም የሰሜኑ የሱዳን መንግሥት በዓባይ ጉዳይ ላይ የወሰደው አወዛጋቢ አቋም ነገ ቅዳሜ ይፋ በሚሆነው የደቡብ ሱዳን መንግሥት ውድቅ ይደረጋል የሚል ስጋት አሳድሯል፡፡ ይህ ደግሞ የወያኔ መንግስት ለዓባይ ውኃ ፍትሐዊ ክፍፍል ሌላ ወዳጅ አገር በመፍጠር በኩል ተጠቃሚ እንዲሆን ከማድረጉም ባሻገር፡፡በወንዙ ላይ ያሉት የቆዩ ስምምነቶችን ዕጣ ፈንታም አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል፡፡የሚል ስሜት ከማሳደሩም ባሻገር በቅርቡ የአባይ ተፋሰስ ሀገሮች ውድድር በማዘጋጅት ድጋፍ ለማሰባሰብ ለሞከረችው ግብፅ እራስ ምታት ከመሆኑም ባሻገር ወደ ጦርነት ልታመራ ትችላለች የሚል አስተያየት ከወዲሁ እንዲሰነዘር አድርጎታል።