‘ፍቱን’ መጽሔት ከሰርካለም ፋሲል ጋር (ቃለ-ምልልስ)
“የማምነው ነገር፣ የሀገሪቷ ችግር ሲፈታ፤ እስክንድርም አብሮ እንደሚፈታ ነው”›
“የስደት ህይወት ሁሉንም ነገር ከዜሮ ያስጀምርሃል“
“የእስክንድር ፅናት እና ብርታት ከፈጣሪ የተሰጠው ፀጋ አድርጌ እመለከተዋለሁ“
“በሀገራችን ጉዳይ ላይ ለመሳተፍ የግድ ፖለቲከኛ መሆን አይጠበቅብንም” ሰርካለም ፋሲል (ጋዜጠኛ)

በአንባቢያን ዘንድ ታዋቂ የነበሩት “አስኳል”፣ “ሚኒሊክ”ና “ሳተናው” ጋዜጦች አንዷ አሳታሚ ነበረች። የ97 ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረ ግርግር ለእስር ከተዳረጉት ጋዜጠኞች እና አሳታሚዎች መካከልም አንዷ ነች – ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል። በሀገራችን የግል ፕሬስን በመጀመር ፈር ቀዳጅ የሆነው የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ሰርካለም ልጃቸው ናፍቆትን የወለደችው በቃሊቲ እስር ቤት መሆኑ ይታወቃል።