የሰውነት ቃጠሎን በቤት ውስጥ እንዴት ማከም እንችላለን?
የሰውነት ቃጠሎን በቤት ውስጥ እንዴት ማከም እንችላለን?
(በቴክኖሎጂስት ዳንኤል አማረ)
አነስተኛ የሰውነት ቃጠሎዎችን በቀላሉ በቤት ውስጥ በፍጥነት የመጀመሪያ እርዳታ ህክምና መስጠት ሲቻል ከበድ ያሉ ቃጠሎዎች ሲሆኑ ግን ወደ ህክምና መስጫ ተቋሞች መሄድ ተገቢ ነው።
በሙቅ ውሀ ወይም ዘይት ቃጠሎ ሲደርስብን ቤታችን ውስጥ በሚገኙ ነገሮች እንዴት የመጀመሪያ ህክምና እንደምንሰጥ በዝርዝር እንመልከት
1. ማር
ማር በፀረ-ባክቴሪያ ባህሪውና ቁስል በፍጥነት እንዲያገግም በማድረግ ወደር አይገኝለትም። ይህም የቁስሉን ህመም በመቀነስና ቁስላችን ምንም አይነት ጠባሳ እንዳይኖረው ያደርጋል።
2. ኮምጣጤ
ይህ የተለመደ የቃጠሎ ማስታገሻ ሲሆን ማድረግ ያለብዎት ኮምጣጤውን በውሀ ይበርዙት ከዚያም ንጽህ ጨርቅ ኮምጣጤው ውስጥ ከነከሩ በኃላ ቃጠሎ በደረሰበት ቦታ ላይ ይያዙት። ህመምዎ ካልቀነሰ አዲስ ኮምጣጤ በመቀየር ይደጋግሙት።
3. የሙዝ ልጫ
የሙዝን ልጫ በቃጠሎው ቦታ ላይ በሚያደርጉበት ጊዜ ከህመምዎ እፎይ ይላሉ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ የሙዝ ልጫው ቀለም ጥቁር እስከሚሆን ድረስ በቃጠሎው ቦታ እንዲይዙት ይመክራሉ።
4. የኦሊቭ ዘይት
በቃጠሎው ቦታ ላይ በተደጋጋሚ በማፍሰስ ወይም በመያዝ ይጠቀሙት ህመምዎን በማቆም እፎይታ ያጐናጽፈዎታል።
5. እሬት
ብዙ የተሞከረና የተረጋገጠ የቃጠሎ ማስታገሻ ሲሆን እሬት ቃጠሎን የማቀዝቀዝ ብቻ ሳይሆን ቆዳችን ለመድረቅ ወይም ለመዳን የሚያደርገውን ሂደት ያፋጥናል። የእሬቱን ቅርንጫፍ ከቆረጡ በኃላ መሀል ለመሀል ይሰንጥቁት ከዚያም የሚወጣውን ዝልግልግ ፈሳሽ በቃጠሎው ቦታ ላይ ይቀቡት ይህንን ሂደት ቁስሉ እስከሚደርቅ ድረስ ይደጋግሙት።
6. የላቬንደር ዘይት(lavender oil)
ህመምን የማስታገስ ጥሩ ችሎታ አለው። እሬትን ከላቬንደር ዘይት ጋር ቀላቅለው በማዘጋጀት ህመሙ እስከሚቀንስ ይጠቀሙት።
