አባይ ፀሐዬ – ‘ልክ እናስገባችዋለን’ የተባለች ቃል ከየት እንደተወሰደች አላቃትም’ (ጽሑፍና ቪዲዮ)
ክቡር አቶ አባይ ፀሐዬ የህ.ወ.ሓ.ት/ኢህአዴግ መስራች አባል ታጋይና በአሁኑ ግዜ በሚኒስትር ማአርግ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማእከል ዋና ዳይርክተር ናቸው፡፡ ከጋዜጠኛ ዘርአይ ሀ/ማርያም በኦህዴድ ታሪክና የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳዮች ቆይታ አድርገዋል፡፡ ሙሉ ቃለ-ምልልሱ ከዚህ በታች በጽሑፍ የቀረበ ሲሆን፤ ቪዲዮውን ደግሞ ከታች መመልከት ይችላሉ፡፡ —— ዘርአይ ኃ/ማርያም:- በትጥቅ ትግሉ ዘመን ኦህዴድ የኢህአዴግ አንድ አባል ድርጅት ሆኖ መቆሙ የነበረው ፋይዳ ምን ነበር? አቶ አባይ ፀሐዬ፡- የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ አንድ የኢህአዴግ አባል ድርጅት ሆኖ መደራጀቱ በመጋቢት 1982 ዓ.ም ፋይዳው ከዛ በፊት የኦሮሞ ህዝብ በዴሞክራሲያዊ አላማ ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝብ አስተሳስሮ የሚያታግለውና የሚመራው ዴሞክራሲያዊ ድርጅት በማጣቱ የተፈጠረ ድርጅት ነው፡፡ ከዛ በፊት የነበረ የኦሮሞ ህዝብ ትግል የብሄር ጭቆናው የሌላው በደልንም ከተጀመረበት /ከተፈጠረበት ግዜ ጀምሮ ሲታገል የቆየ ህዝብ ነው፡፡ በብሄራዊ መብቱም ለአጠቃላይ የኢኮኖሚያዊና ዴሞክራሲያዊ አጠቃላይ መብትም፡፡ ግን ከዛ በፊት የነበሩ ድርጅቶች የተለያዩ በኦሮሞ ህዝብ ስም የተደራጁ ድርጅቶች ቢኖሩም አንደኛ ጠንካራ የህዝብ ድጋፍ እና ጠንካራ የህዝብ ማደራጀት ስራ አልነበረባቸውም፡፡ ወደ ህዝብ ገብተው ህዝቡን አደራጅተው ከህዝቡ ጋር ሆኖ የህዝቡን ስሜት አዳምጠው ሀይል የፈጠሩ አቅም የፈጠሩ ጠንካራ ድርጅቶች ጠንካራ የትጥቅ ትግል ሰራዊት የፈጠሩ አልነበሩም፡፡ ስለዚህ እየተደነቃቀፉ እየተኳላሹ ወደ አጎራባች ሀገሮች ወጣገባ እያሉ ነው ግዚያቸውን ያሳለፉትበአብዛኛው፡፡ ሁለተኛ መላውን የአማራ ህዝብና የኢትዮጵያ ህዝብ እንደጠላት የሚወስዱ ናቸው የነበሩ፡፡ ይህ ደግሞ የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎትና ጥያቄ አልነበረም፡፡ የህዝቡ ጥያቄ የፖለቲካ ዲሞክራሲ የማንነትና የኢኮኖሚ […]