ሆሣዕና በአርያም፤ ሆሣዕና … ሆሣዕና… ሆሣዕና…!!

ዲ/ን ክንፈ ገብርኤል
Hosaena

ሆሣዕና ቃሉ የዕብራይስጥ ሲሆን ትርጓሜውም “አሁን አድን” ማለት ነው። እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት ከፋሲካ/ከትንሳኤ በፊት ያለው እሑድ “የሆሣዕና እሑድ” በመባል ይታወቃል። በዚህ ዕለትም በቤተ ክርስቲያናችን የሚዘመረው መዝሙር፣ ማኅሌቱ፣ ቅዳሴው፣ ምንባቡና ማንኛውም አገልግሎት ሁሉ ዕለቱን በታላቅና እጅግ ደማቅ በሆነ መንፈሳዊ ሥነ – ሥርዓት የሚዘከርበት፣ የሚታሰብበት ነው። ይህ በዓል እጅግ በደማቅና ልብን በሚመስጥ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓትና ድምቀት ከሚከበርባቸው ቅዱሳን ገዳማትና መካናት መካከል የአክሱሟ ርዕሰ አድባራት ጽዮን ማርያም እና በዚህ በአዲስ አበባችን የእንጦጦ ማርያም በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ …