ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል: የቅ/ሲኖዶስ አባላት ራሳቸውን በመስጠትና ወቅቱን በዋጀ አካሔድ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያድኑ ጥሪ አቀረቡ
ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ፣ የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር እና ልማት ድርጅት የበላይ ሓላፊ
ስለ አስተዳደራዊ ችግሮችና የወደፊት ስጋቶች ተናግረዋል
ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ፣ የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር እና ልማት ድርጅት የበላይ ሓላፊ
- እኛ ዘንድ ቀኖና እና ሥርዐት ሲጣስ ‘No’ ማለት የለም፡፡ ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን ማስፈጸም ከኹሉም የሥራ ሓላፊዎች የሚጠበቅ ኾኖ ሳለ በዝምታ ማየት ነው፡፡ ምእመናን ናቸው ሃይማኖታችን እያሉ መቆርቆር እያሳዩ ያሉት፡፡
- መልካም አስተዳደር ባለመኖሩ በየጊዜው በሚፈጠረው ውዝግብ የተነሣ÷ የቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖናዊ ሥርዐት ይጣሳል፤ ገጽታዋ ይዳከማል፤ ኢኮኖሚያዊ አቅሟ ይቀንሳል፤ የሕዝብ ድጋፍ እና የውጭ ዕውቅና ይጠፋል፤ የውስጥና የውጭ ጠላቶቿ ይበረታሉ፤ አንድነቷ ተናግቶ በየመንደሩ ልዩ ልዩ እምነቶች ይፈጠራሉ፤ በመጨረሻም መበታተን እና መከፋፈል ይከተላል፡፡
- ልቅ ዝርፊያና ሙስና፣ መንፈሳዊነትና ሰብአዊነት ከሌለው መሥመር የለቀቀ ዘረኝነት፣ ዘመናዊ አስተዳደራዊ ሥርዐት እንዳይኖር ከሚቃወም የአመለካከትና የተግባር ድክመታችን መላቀቅ ይገባናል፡፡ ወቅቱን የዋጁ፣ በተግባር የሚተረጎሙ ሕገጋት እና ደንቦች ያስፈልጉናል፤ በረጅምና በአጭር ጊዜ ዕቅዶች መመራት ይኖርብናል፤ ዕውቀትን መሠረት ያደረገ፣ በተሰጠው ሓላፊነት የሚጠየቅ፣ በማያቋርጥ ሥልጠና አቅሙን የሚገነባ የሰው ኃይል ምደባና ሥምሪት ያስፈልገናል፡፡
ብፁዕነታቸው፣ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የጥናትና ምርምር ማእከል ግብዣ ‹‹ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግሮች እና መፍትሔዎች›› በሚል ርእስ ትላንት ማምሻውን በኮሌጁ አዳራሽ ያቀረቡትን ሐሳብ ሙሉ ይዘት ይከታተሉ፡፡
Source:: haratewahido
The post ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል: የቅ/ሲኖዶስ አባላት ራሳቸውን በመስጠትና ወቅቱን በዋጀ አካሔድ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያድኑ ጥሪ አቀረቡ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.