የዓሊ ቢራ የጥበብ ሥራዎች የኦሮሞ ሕዝብ ሀብት ብቻ ናቸው እንዴ?!

ቋንቋዎቻችን የልዩነት፣ የጥላቻና የዘረኝነት ጽኑ ግምብ ሲሆኑብን!
ኒቆዲሞስ
የኃይማኖት ሊቃውንት በጥንት ዘመን ፍጥረት ሁሉ በአንድ ቋንቋ ይነጋገር እንደነበርና ቆይቶ ግን ይህ በአንድ ቋንቋ የመግባባት ጉዳይ ብዙም ሳይዘልቅ እንደተቋረጠ ያትታሉ። ምክንያቱን ሲያብራሩም ጥንታውያኑ ባቢሎናውያን ገናና ሥልጣኔያቸው ጫፍ በነካ ማግሥት ሰማይን የሚታከክና የፈጣሪን መኖሪያ፣ ክብሩንና ልዕልናውን የሚዳፈር ረጅምና ግዙፍ የሆነ ታላቅ ግምብ ለመገንባት ተነሱ።