በደቡብ አፍሪካ የተፈጸመውን የሻርፕቪሌን ዕልቂት ማስታወሻ
ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሀገሬ)
ደቡብ አፍሪካ እ.ኤ.አ. በ1960፣
እ.ኤ.አ መጋቢት 21/1960 ልክ ከዛሬ 55 ዓመታት በፊት ወደ 5 ሺ የሚገመቱ ሰልፈኞች (እንደ አፓርታይድ ፖሊስ የተጋነነ መረጃ ከሆነ ደግሞ 20 ሺ ሰዎች) በደቡብ አፍሪካ በሻርፕቪሌ ከተማ በትራንስቫል ግዛት (በአሁኑ ጊዜ ከደቡብ አፍሪካ 9 ግዛቶች መካከል አንዷ በሆነችው እና ጋውቴንግ እየተባለች በምትጠራው ግዛት) ፖሊስ ጣብያ ፊት ለፊት ተሰባሰቡ።