የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እና ለቆጣቢዎች እንዴት እደሚተላለፉ ክፍል 1 ከሶደሬቲዩብ 40/60 condominiums updates
ክፍል 2 ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በዚህ ፔጅ ላይ ይለጠፋል
ጥያቄ ካላቹ ከዚህ በታች ፃፉት። የሚመለከተውን ክፍል ጠይቀን በክፍል ሶስት እናቀርባለን።
ሶደሬቲዩብ
የ 40/60 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ስራዉ እየተቀላጠፈ መሆኑን እና የመጀመሪያዉ እጣ አወጣጥ ስነስርዓትም በዚህ አመት መጨረሻ እንደሚከናወን ታዉቋል፡፡
በአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ የኮሙኒኬሽን የስራ ሂደት መሪ የሆኑት አቶ ዮሀንስ አባይነህ በሰጡን ቃለ ምልልስ ላይ እንደገለፁልን ቤቶቹ በተያዘላቸዉ የጊዜ ገደብ እና በተሻለ ጥራት እየተገነቡ ይገኛሉ፡፡ 164 ሺህ 779 ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም 14 ሺህ 273 ቤቶች በ 8 ሳይቶች ማለትም፡-
– በሰንጋተራ
– ክራዉን
– ቦሌ ቡልቡላ
– አስኮ /እንቁላል ፋብሪካ/
– ገርጂ
– መገናኛ /እህል ንግድ ተብሎ የሚጠራዉ አካባቢ /
– መሪ
– ቦሌ አያት —– እየተገነቡ ይገኛሉ፡፡
በዚህ አመት መጨረሻ የመጀመሪያዉ እጣ እንደሚወጣ የገለፁት አቶ ዮሐንስ አስከትለዉም እጣ አወጣጡ በቆጠቡት ልክ በከፍተኛዉ ብር ወደ ዝቅተኛዉ ብር በደረጃ ቅድሚያ እንደሚሰጠዉ ገልፀዋል፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ቆጣቢ እጣ ዉስጥ ለመግባት 40 ፐርሰንቱን ከፍሎ ማጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡
እጣዉ የወጣላቸዉ ሰዎችም በመኝታ ቤት በሮች እና ቀለም በስተቀር ሙሉ ስራዉ ተጠናቆ እንደሚረከቡ የታወቀ ሲሆን ብዙ የቆጠበ የቤት ባለቤትነት እድሉን እንዲያስፋ እና ህብረተሰቡ የቁጠባ ባህሉን ማዳበር እንዳለበትም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
አላማዎች
1. በመካከለኛና በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ ያሉ ህብረተሰቦችን የቤት ችግር ደረጃ በደረጃ መቅረፍ
2. የከተማዋን የተዘበራረቀ ገፅታ በመልሶ ማልማት ማስተካከል
3. በአገሪቷ ዉስጥ ያለ ስራ አጥ ዜጎችን በግንባታዉ ሂደት ዉስጥ በማሳተፍ የስራ እድል መፍጠር
4. የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዉን እየተገነቡ ነው፡፡
አቶ ዮሀንስ አባይነህ
የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎት ደጋፊ
የስራ ሂደት ሃላፊ
በአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕሪይዝ
የኮሙኒኬሽን የስራ ሂደት መሪ
ምን ላይ ደረሰ
14 ሺህ 273 ቤቶች በ 8 ሳይቶች እየተገነቡ ነው፡፡
ቦታዎቹም
– ክራዉን
– ቦሌ ቡልቡላ
– አስኮ /እንቁላል ፋብሪካ/
– ገርጂ
– መገናኛ /እህል ንግድ ተብሎ የሚጠራዉ አካባቢ /
– መሪ
– ቦሌ አያት
በተያዘላቸዉ የጊዜ ሂደት እየተገነቡ ይገኛሉ፡፡ 164 ሺኅ 779 ሰዎች በባለ 1 2 3 መኝታ ቤት ተመዝግበዋል፡፡ በዚህ አመት መጨረሻ የመጀመሪያ 40/60 ቤት እጣ ይወጣል፡፡ የዕጣ አወጣጡም በቆጠቡት ልክ በከፍተኛዉ ብር ወደ ዝቅተኛዉ ብር በደረጃ ቅድምያ እየተሰጠ ይሆናል ግን እያንዳንዱ ቆጣቢ የቤቱ አእጣ እንዲደርሰዉ በመጨረሻዉ ትንሹ 40 ፐርሰንቱን ከፍሎ ያጠናቀቀ ይሆናል፡፡ 100 ፐርሰንት ከፍሎ ያጠናቀቀዉ ደግሞ እንደቆጠበበት ጊዜ ቅድም ተከተል ይወዳደራል፡፡
እጣ ዉስጥ የሚገቡ ሁኔታዎች
1. ሳይት
2. ብሎክ /ፍሎር
3. ቤት
4. በእኩል ሰአት ተመሳሳይ ብር የቀጠቡ ሰዎች በወቅቱ ከወጣዉ ቤት ከበለጡ እጣ ዉስጥ ይገባሉ፡፡
ቤቱን ከዉስጥ ከመኝታ ቤት በሮች እና ቀለም ዉጪ ሙሉ ስራዉ አልቆ ነው የሚረከበዉ፡፡
ከዚህ በተሻለ ቤቶቹን በፍጥነት አጠናቆ ለሰዉ ለማስረከብ ጥረተ እየተደረገ ነው፡፡ ጥናትም እየተደረገ ነው፡፡
Watch Ethiopian movies legally. Upto 5 movies added daily. Here are the top 10 most viewed movies today.
Receive Ethiopian News, Movies and Videos by email. Sign up for Email alerts ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎችን፣ ድራማዎችን፣ሙዚቃዎችን፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በኢሜል አድራሻዎ እንልካለን። ኢሜሎን ያስመዘግቡ።
