የአላሙዲ አራዊት
በአርአያ ተስፋማሪያም
ቱጃሩና ተከታዮቻቸው በዲሲ ይገኛሉ። ከሰሞኑ አሸሸ ገዳሜው ጦፏል። አንዳንዶች የዘቀጠ ተግባር ሲፈፅሙ ታይተዋል። ይህን ለጊዜው እንለፈው… ለመፃፍም ስለሚቸግር።…አራዊት (ደምስ) ቀይ ካርድ ተመዞበታል። በዲሲ ዳውንታውን አካባቢ በሚገኝ ህንፃ ላለፉት 5 አመታት የኖረው አራዊት ወጪው ይሸፈን የነበረው በቱጃሩ ነው። በወር 5 ሺህ ዶላር ተመድቦለት የቆየ ሲሆን በ5 አመት 300ሺህ ዶላር ኪሱ ገብቷል። 1ሺህ የቤት ኪራይ ከፍሎ ቀሪው 4ሺህ የኪሱ ነበር። የሚገርመው ላለፉት 5 አመታት ስራ ያለመስራቱ ነው። ጓደኞቹ ያውም ታዋቂ የብ/ቡድን ተጨዋቾች ፓርኪንግ ሲሰሩ እሱ ግን ቱጃሩን ተማምኖ ሳይሰራ ይኖር ነበር። አሁን ግን « ከዚህ በኋላ የ5ሺህ ዶላር ነገር አብቅቶዋል» ተብሎ ተነግሮታል። ከወራቶች በፊት ከሳሚ ወዳጄ ጋር ሆነን ስራ ጨርሰን በእኩለ ሌሊት በአንድ ባር አራዊትን አገኘነው። ሰው ከጀርባ የሚያንሾካሹክበትን ጉዳይ ፊት ለፊት አፍርጬ ጠየኩት። «.. ሰው ሁሉ የሪፖርተሩን አማረ አስደብድበህ ነው የመጣኸው እያለ ያማሃል። እንዳውም ከአገር በቦሌ አስመልጦ ያስወጣህ በረከት ስሞዖን ነው» አልኩት። በባሩ የነበሩ ሃበሾች በጥያቄዬ መደንገጣቸው አልቀረም። በተርበተበተ ሁኔታ « እንዴት መሰለህ አርአያ…የሚባለው ውሸት ነው። እሱ ሲደበደብ እኔ የቀነኒሳ የሰርግ ምላሽ ላይ ጀርመን ነበርኩ… ውሸት ነው..» አለ። ገፅታው ግን እውነታው መሸሸግ አልቻለም፡፡… በቅርቡ ፌስቡክ የተቀላቀልከው ወዳጄ አራዊት ምን ትላለህ?