ሰበር ዜና:- በአሰቦት ገዳም ደን ላይ የእሳት ቃጠሎ ተቀሰቀሰ
የወያኔ ዘመቻ በገዳማት ላይ ቀጥሏል
በዛሬው እለት ረፋድ ላይ ከገዳሙ በስተሰሜን አቅጣጫ የተቀሰቀሰው እሳት ማኅበረ መነኮሳቱ አና ከመኢሶ ከተማ ከመጡ የፌደራል ፖሊስ አባላት ጋር እሳቱን ለማጥፋት ጥረት ተደርጓል፡፡ ነገር ግን በሌላ አቅጣጫ ከገዳሙ ደን በቅርብ ርቀት እሳቱ እየተቀጣጠለ እንደሚገኝ ከገዳሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በስተሰሜን አቅጣጫ የተነሳው እሳት በማኅበረ መነኮሳቱ እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ለማጥፋት ጥረት የተደረገ ቢሆንም ጭሱ ግን አሁንም እንዳለ በስልክ ያነጋገርናቸው የገዳሙ መነኮሳት ገለጸዋል፡፡
ሙሉ መረጃውን እንደደረሰን እናቀርባለን፡፡
source: eotcmk.or
The post ሰበር ዜና:- በአሰቦት ገዳም ደን ላይ የእሳት ቃጠሎ ተቀሰቀሰ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.