አቶ ግርማ ሠይፉና መጪዉ ምርጫ -(ነጋሽ መሐመድ እና አርያም ተክሌ)

ፓርቲዉ በምርጫዉ ለመሳተፍ አጩዎቹን ሰይሞ፤የመወዳደሪያ አላማዎቹን ለይቶ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ነበር።በዚሕ መሐል ነዉ ፓርቲዉ በአቶ ግርማ ቋንቋ «ለመወዳደር አይደለም ዉድድር ለመመልከት እንኳን ያልተዘጋጁ» ላሏቸዉ ሰዎች የተሰጠዉ።

Girma Seifuበኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛዉ የተቃዋሚ ፓርቲ እንደራሴ የሆኑት አቶ ግርማ ሠይፉ በመጪዉግንቦት ሊደረግ በታቀደዉ ምርጫ እንደማይሳተፉ አስታወቁ።እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ተቃዋሚዉን የኢትዮጵያ አንድነትለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) በምክትል ፕሬዝዳንትነት ይመሩ የነበሩት አቶ ግርማ እንደሚሉት በምርጫዉየማይወዳደሩት የኢትዮጵያ መንግሥትና ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግ በፓርቲያቸዉ ላይ ባደረሱባቸዉ ተፅዕኖነዉ።በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ዉሳኔ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕን የፓርቲነት ፍቃድና ዕዉቅና ያገኙት ወገኞችበአቶ ግርማ እምነት አንድነትን የሚወክሉ አይደሉም።

መስከረም፤ 2003 ጀምሮብቸኛ ከሚል ቅፅል ጋር የምክር ቤት እንደራሴነቸዉ ሲጠቀስሲዘገብ እዚሕ ደረሱ።በሕጉመሠረት ያሉበት ምክር ቤትበመጪዉ መስከረም በሌላ እስከሚተካም የምክር ቤት እንደራሴነታቸዉ ከነቅፅላቸዉመቀጠሉ አይቀርም።አቶ ግርማ ሰይፉ።ከዚያ በሕዋላ ግንብቸኛ» የሚለዉን ቅፅል «የቀድሞዉ» በሚለዉ ለማስተካትእንደ ፖለቲካዉ ወግ በምርጫ ተወዳድረዉ እስኪሸነፉ ወይም ከፖለቲካዉ «ጡረታ» እሲከዉጡ አልጠበቁም።የ48 ዓመቱ ጎልማሳ በግንቦቱ ምርጫመወዳደሩን ይፈልጉታል ግን አይወዳደሩም።

«እኛ» የሚሉት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ን።ፓርቲዉ በምርጫዉ ለመሳተፍ አጩዎቹንሰይሞ፤የመወዳደሪያ አላማዎቹን ለይቶ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ነበር።በዚሕ መሐል ነዉ ፓርቲዉ በአቶ ግርማ ቋንቋ«ለመወዳደር አይደለም ዉድድር ለመመልከት እንኳን ያልተዘጋጁ» ላሏቸዉ ሰዎች የተሰጠዉ።

1997 ምርጫ ዉጤት የቀሰቀሰዉ ደም አፋሳሽ ዉዝግብ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ሕብረት፤ ጉልበትናእዉቅና አሳጥቶ በጣለ ማግሥት እንዳዲስ ከተደራጁት ፓርቲዎች ሰፊ ተቀባይነት፤ ብዙ አባላት ጠንካራ ፖለቲከኞችንካሰባሰቡ ጥቂት የፖለቲካ ማሕበራት አንዱአንድነት ነበር።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአንድነትፖለቲከኞች መካካል የተነሳዉን ክፍፍል አስታኮባሳለፈዉ ዉሳኔ ከተወዛጋቢዎቹ ለአንዱ አዉቅናሰጥቷል።አቶ ግርማ «ክፍፍል» የሚለዉንአይቀበሉትም።ዉሳኔዉንም «ሕገወጥ» ይሉታል።

547 በመቀመጫዎች ባሉት ምክር ቤት የተቃዋሚፓርቲ ብቸኛዉ ተወካይ በመሆን እስካሁን ያከናወኑትንተግባር ጥሩ መጥፎነት አቶ ግርማ «ተመልካች ነዉፈራጁ ይላሉ።«ያቅሜን አድርጌያለሁ» አከሉ እንደራሴዉ።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

The post አቶ ግርማ ሠይፉና መጪዉ ምርጫ -(ነጋሽ መሐመድ እና አርያም ተክሌ) appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.