ከአዲስ አበባ ወደ ደምቢዶሎ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ ተገልብጦ የ12 ሰዎችን ህይዎት ቀጠፈ 12 people died after bus overturned
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዛሬ ማለዳ ከአዲስ አበባ ደንቢዶሎ 68 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ተገልብጦ 12 ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ ቀሪዎቹ 56 ተሳፋሪዎች ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለጸ።
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች አምቦ እና አዲስ አበባ በሚገኙ ሆስፒታሎች ለህክምና እንደተላኩም ፖሊስ አስታወቋል።
አውቶቡሱ 194 ኪሎ ሜትር እንደተጓዘ ረፋድ 4 ሰአት ላይ ምዕራብ ሸዋ ጨሊያ ወረዳ ራቾ ገጠር ቀበሌ ልዩ ስሙ መሳለሚያ አካባቢ ሲደርስ ነበር አደጋው የደረሰው።
የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ከበደ ደቢርሳ ተናግረዋል።
በኬነሳ አመንቴ
Watch Ethiopian movies legally. Upto 5 movies added daily. Here are the top 10 most viewed movies today.
Receive Ethiopian News, Movies and Videos by email. Sign up for Email
alerts
ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎችን፣ ድራማዎችን፣ሙዚቃዎችን፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በኢሜል አድራሻዎ እንልካለን። ኢሜሎን ያስመዘግቡ።