አዎን ትግሬ ሁሉ ወያኔ ነው! (ምላሽ ለፕ/ር መስፍን)
በዘመናዊቱ ኢትዮጵያ አቅጣጫቸውን እየቀያየረ ከሚመጡ አርዕስቶች ውስጥ ፣ “እውነት ትግሬ ሁሉ ወያኔ ነው?” የሚለው ሁሌም እንደ አዲስ በተለያዩ ኢትዮጵያውያን ሃሳብ ሲሰነዘርበት ይስተዋላል። ሰሞኑንም በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም የተጻፈውን “የወያኔ ጥላቻ ፍሬ” የተሰኘ መጣጥፍ ስናነብ ፣ “ትግሬ ሁሉ የወያኔ ተጠቃሚ አይደለም” በሚል መንደርደሪያነት “ትግሬ ሁሉ ወያኔ አይደለም” ወደሚል መደምደሚያ ይወስዳል።
የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ግን ፣ ከዚህ በተለየ መልኩ ያምናል። አዎን ትግሬ ሁሉ ወያኔ ነው! ማንኛውም ሰው የሚኖረው እምነት በእውቀቱ እና በድንቁርናው ላይ የሚመሰረት ሲሆን ፣ ሌላው የእምነት መሰረት ግን ተስፋው ሊሆን ይችላል። እናም ፣ እንደ ፕሮፌሰር መስፍን አይነት የእድሜ ዘመኑን ስለሃቅ ሲታገል እና ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ ድምጽ ሆኖ ለኖረ ምሁር ፣ ዛሬ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ከሚታየው እኩይ የወያኔ ተግባር ጋር የትግራይን ህዝብ በጅምላ መፈረጅ ፣ አንድም በአካበቱት እውቀት ወይም ድሮ በሚያውቋት ኢትዮጵያ አይን እና ሌላም ጊዜ ፣ የትግሬውን በጅምላ ወያኔን የመደገፍ ሃቅ አሜን ብለው ለመቀበል ሲቸገሩ ብንመለከት ብዙም ላይገርም ይችላል። በተቃራኒው ግን ፣ እራሳቸው ፕ/ር መስፍን እየፈሩ ያሉት ፣ የወያኔ አገዛዝ የዘራው የጥላቻ ፍሬ በማን ላይ የከፋ ችግር ሊያመጣ እንደሚችል የመተንተናቸው እና የመተንበያቸው አይነተኛ ምስጢር ፣ የስርዓቱ አይነተኛ ተጠቃሚ ለሆኑት ትግሬዎች ከመፍራት የዘለለ አይደለም።
ፕ/ር መስፍን ጨምሮ “ትግሬ ሁሉ ወያኔ አይደለም” የሚሉ ሰዎች እንደየመከራከሪያ ነጥብ ይዘውት የሚዞሩት ፣ “ትግሬ ሁሉ ወያኔ ቢሆን ኖሮ ፣ የትግሬ ድሃ ባላየን ነበር” በሚል አጣቃሽ ሃሳብ ነው። ይህ ግን እራሱ ምሉዕ የሆነ አክንዮ አይመስለኝም። ትግሬ ሁሉ ሃብታም ያለመሆኑ ምስጢር ሁለት ይመስለኛል። አንደኛ ፣ በአንድ ወቅት ፕ/ር መስፍን በጽሁፋቸው ገልጸውት እንደነበረውና ፣ የወያኔ አመራሮች ልዩ ብቃት እንደሆነ የሚነገርላቸው ፣ እንደ ደርግ በአንድ ጊዜ ሃያ ሰላሳ ሰው ከማረድ ይልቅ ፣ ተራ በተራ መግደልን ስለሚመርጡ ፣ የሃብት ዝርፊያውንም ሆነ የሃብት ክፍፍሉን በየተራ ለትግሬዎች እያደረሱ ለመሆኑ አይነተኛው ምሳሌ ፣ የሰሞኑን የአቶ ያሬድ ጥበቡ መጣጥፍ ነው። “በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሚቀጥራቸውውስጥ 85% ትግሬዎች ናቸው” ይላል። ይሄ አሃዝ የተጋነነ ለሚመስለው ሁሉ ፣ የኢሚግሬሽን ፣ የማዘጋጃ ፣ የአየር መንገድ ፣ የብሄራዊ ንግድ ፣ የፖሊስ እና ደህንነትን ጨምሮ ከፍ ሲል የሚንስቴር መስሪያቤቶች እና ወታደራዊ ባልሰልጣናት በምን አሃዝ ላይ የተመስረተ ብሄረሰባዊ ተዋጽዖ እንዳላቸው አንድም በአካል ወይም በመጣጥፎች ሊያረጋግጥ ይችላል። ስለዚህ ፣ “ትግሬ ሁሉ ወያኔ ቢሆን ኖሮ ፣ የትግሬ ድሃ ባላየን ነበር” የሚለው ክርክር ፣ መንግስታዊና የንግድ ተቋማትን የተቆጣጠሩት 85%ቱ ትግሬዎች ናቸው ከሚለው የልቅ ፣ ለምን 15%ቱስ ከትግሬዎች ተቀነሰባቸው የሚል ክርክር ይመስለኛል። ለዚህ መልሱ ደግሞ ፣ ትንሽ መታገስ ብቻ ነው እንጅ ፣ ሁሉም ቦታዎች በትግሬ መሸፈናቸው አይቀርም።
ሌላው “ትግሬ ሁሉ ወያኔ አይደለም” ለሚለው ሥሥ መደምደሚያ እንደምሳሌ የሚጠቀሰው ፣ “ትግራይ ውስጥ እራሱ ህዝቡ ከሌላው ኢትዮጵያዊ የተለየ ነጻነት የለውም” የሚለው ነው። ይሄ በእውነትም ሃቅ ነው። ግን ለምን? ምክንያቱም ስርዓቱ በነጻነት ስለማያምን ፣ እንኳንስ ለትግራይ ህዝብ ይቅርና ለራሳቸው ለወያኔ አመራሮችም ነጻነት በድርጅታቸው ውስጥ ነጻነት የላቸውም። ምናልባት ካሉት የወያኔ ባልስልጣናት ውስጥ “እብድ እና ዘበናይ ያሻውን ይናገራል” እንዲሉ የእብድ ያህል ነጻነት ያለው ብቸኛ ግለሰብ ስብሃት ነጋ ብቻ ነው። ስለዚህም ፣ በድርጅታዊም ሆነ ግለሰባዊ የሃሳብ ነጻነት የማያምነው የወያኔ አመራር ፣ እራሱ የሌለውን ከየት አምጥቶ ለትግራይ ህዝብ ሊሰጥ ይቻለዋል?!
ቁምነገሩ ያለው ግን ፣ ወያኔ በነጻ አስተሳሰብ አለማመኑ ከሰጠው በስልጣን ላይ የመደላደል አይነተኛ ጥቅም አንጻር ሲታይ ፣ ስለምን ነጻት የወያኔም ባለስልጣናትም ሆነ የትግራይ ህዝብ አጀንዳ ሊሆን ይችላል?! ነጻነትኮ እጅግ አንጻርዊ ነው። ቅንጅትን ፍርስርሱን ካወጡት አንደኛውኮ ፣ በአመራር ውስጥ ያሉ ሰዎች “አለን” ብለው የሚያስቡት “ግለሰባዊ ነጻነት” እርስ በ እርስ አቧክቷቸው ነው የዝቡንም ተስፋ ያጨለመው። ሃሳብን በነጻ በመግለጽ ስም ፣ እንደበርካታ የተቃዋሚ አመራሮች ልዩነትን በአደባባይ እየዘሩ ተከታይ ህዝብን ተስፋ ከማስቆረጥ ፣ እንደወያኔ ስሜትን ገዝቶ ስልጣንን ለራስ እና ለሚወክሉት የትግራይ ህዝብ ጥቅም ማስከጠበቅ ሳይሻል ይቀራል?!
መጻኢ የኢኮኖሚ እና የበላይነት ተስፋውን በልጆቹ የጡንቻ ላይ ላደረገ የትግራይ ህዝብስ ፣ ይህ የምንለው አይነት ነጻነትስ ምን ያህል ያሳስበዋል?! የኢኮኖሚ ነጻነቱን እና ሙሉ በሙሉ የስልጣን ባለቤትነቱን ከተጎናጸፈ በኋላስ ቀስ በቀስ ወደሚፈልገው አይነት “አሳማ ከእንሣት ሁሉ የበለጠ ነጻነት አለው” ምኩራብ ወቅቱን ጠብቆ መድረሱ ይቀራል?!
በዚህ አጀንዳ ዙሪያ እጅግ የሚያስዝነውና እስከዛሬም በገሃድ እየታየ ያለው ፣ እራሳቸው ፕ/ር መስፍንም የደረሱበት መደምደሚያ ፣ ወያኔ ስልጣን ከተቆናጠጠ ጀምሮ ፣ እየሄደ ያለበትን አደገኛ የሆነ ለትግራይ ህዝብ ከሚሰጠው ጊዚያዊ ጥቅም ይልቅ በሚጠብቀው ታሪካዊ ተጠያቂነት ዙሪያ ፣ ከብዙሃኑ ኢትዮጵያውያን ጋር የሚቆሙ የትግራይ ልሂቃንን ቁጥር ፕ/ሩ አስር እንኳን ለመሙላት እንደተቸገሩ ሲነግሩን ወደ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ንግግር ያመራናል። የቅንጅት መሪዎች ከሁለት አመት እስር በኋላ አሜሪካን ሲዘዋወሩ ፣ ወ/ሪት ብርቱካን የትግራይ ተወላጆችን ያስቀየምናችሁ ቢኖር (“ወደመጡበት እንመልሳቸዋለን” ከሚለው የአቶ በድሩ አደም ንግግር ጋር ይያያዛል) ይቅርታ አድርጋችሁልን ፣ ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር ለፍትህ አብራችሁ ቁሙ የሚለው ጥሪ ይታወሳል። ትክክልም ነበር። ምክንያቱም ፣ ወያኔ የሚያደርሰውን የግፍ ጭፍጨፋ ማንም የሰው ልጅ በንጹህ ህሊናው ሊያወግዘው የሚገባ ሆኖ ሳለ ፣ በውጭ አገር የሚኖሩ ነጻነት ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ግን ጉዳያቸው አልነበረም። ታዲያ ትግራይ ያለው ህዝብስ ነጻነት ስለሌለው ነው ወያኔን የማይቀውም አልን ፣ ምነው በውጭ የሚኖሩትስ ነጻነት የላቸው ይሆን?! ይህ የሚያሳየው “ትግሬ ሁሉ ወያኔ” መሆኑን ካልሆነ ፣ ምን ሊባል እንደሚችል አይገባኝም።
ጽሁፌን የማጠቃልለው ግን ፣ ከላይ የገለጽሁትን ለዘብ በሚያደርግ መደምደሚያ ይሆናል። አንድን አገዛዝ በምንም ምክንያት ይሁን ፣ በተለያዩ መንገዶች መቀበል ፣ መደገፍ ፣ ማገዝ ፣ ማመን እና መጠበቅ ግለሰባዊም ሆነ ማህበረሰባዊ ምርጫ ሊሆን ይችላል። ከዚህም አንጻር ፣ እንዲሁ ተራ ፕሮፕጋንዳ ሳይሆን ፣ በገሃድ የምናየው የተግራይ ልጆች ከኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ይልቅ በህውሃት አርማ ሲኮሩ ፣ ከአድዋ ድል ይልቅ በህውሃት ምስረታ ሲመጻደቁ ፣ ቤተሰቡን በትኖ ከስራ ከሚሰናበተው ሌላ ብሄር ቁጭት ይልቅ በግፍ ለሚቀጠረው ትግሬ ሲደሰቱ፣ ከመንፈሳዊ ሲኖዶስ ይልቅ ለትግራዊ ፓትሪያሪክ ሲሟገቱ … ማስተዋሉ የየዕለት ትዝብታችን ነው። ይህ ሁሉ ግን ፣ ከግዚያዊ ጥቅም አንጻር እንጅ ፣ ትንሽ አይንን ጨፈን አድርጎ በጸጥታ ነገን ሲያዳምጡ ፣ መጭው አስፈሪ መሆኑን እነሱም እንደማያጡት ሁሉ ፣ ማንም የሰው ልጅ ይህንን መገመት አይሳነውም። ስለዚህም ፣ የትግራይ ህዝብ ፍትሃዊ ባልሆነ መነገድ ከወያኔ የሚያገኘው ጊዚያዊ ጠቀሜታ ፣ በዘላቂ ተጥያቂነትና ዘመን ተሻጋሪ የጥላቻ ውርስ እንዳያተርፍለት እራሱን ለፍትህ ማቆም መቻል አለበት። እንዴውም በአሁኑ ሰዓት ለፍትህ መታገል የሚያምርበት ፍጹም እየተጨቆነ ያለው ሌላው ብሄር ሳይሆን ፣ የስርዓቱ አይነተኛ ተጠቃሚ ትግሬው ነው። ለምን ቢባል ፣ ሌላው ኢትዮጵያዊ መሰረታዊ ፍላጎቱን ለማሟላት እንኳ ያልቻለ ሲሆን ፣ ትግሬው ግን ሆዱ ሞልቶ ያድራልና።
በአዲሱ
አዲሱ ከፋለ
The post አዎን ትግሬ ሁሉ ወያኔ ነው! (ምላሽ ለፕ/ር መስፍን) appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.