በስዊድን የአንድነት የድጋፍ ማህበር በሓገራችን አትዮጵያ ዕለት ተዕለት እየተንሰራፋ የመጣውን አምባገናናዊ ስርዓት ያወግዛል
በስዊድን የአንድነት የድጋፍ ማህበር በሓገራችን አትዮጵያ ዕለት ተዕለት እየተንሰራፋ የመጣውን አምባገናናዊ ስርዓት ያወግዛል፡፡ ሁላችንም እነደሰማነው የወያኔ ኢህአደግ አምባገነን መንግሥት ህዝብ ያቋቋማቸውን የአንድነትትና የሚኢአድን ድርጅቶች ፋሸሸታዊ ጡንቻውን በመጠቀም ከዚህ ቀደም በቅንጅት ላይ እንዳደረገው ሁሉ የምረጫ ቦረድ ተብዬው ቡድን አማካኝነት ፓረቲዎቹን ለተለጣፊ ስብስቦች አሳልፎ ሰጥቷል ፡፡ ይህንን ሕገወጥ እና አምባገነናዊ ማናለብኝነት የኢትዮጵያሕዝብ በአንድነት ቆሞ ሊያወግዘውና ሊታገለው ይገባል፡፡ በመሆኑም የአንድነት የድጋፍ ማህበር በስዊድን በሓራችን የዲሞክራሲ ሥርዓት እሰኪሰፍን የህግ የበላይነት እስኪረጋገጥ የሰብዓዊ መብቶች እስኪከበሩ ድረስ ትግሉን እደሚቀጥል ያረጋግጣል ፡፡ ይህ ጥሪ፡- በዓለም ላይ ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያኖች ሁሉ፤ ኢትጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ እንዲሰፍንና የኢትዮጵያን ሕዝብ እኩልነቱና ሰብዓዊ መብቱ ተጠብቆ እንዲኖር ለምትታገሉ የፖልቲካ ድርጅቶች፤ የሰብዓዊ መብት ታጋዮች እና ግለሰቦች በሙሉ ይህንን አምባገነናዊ ሥርዓት በህበረት እንድንታገልና ሴራውን እንድናከሽፍ ጥሪያችንን እናስተላልፋልን፡፡ ጥር 23 ቀን 2007 ዓም (ፌብርዋሪ 1 ቀን 2015) በስዊድን ያነድነት የድጋፍ ማህበር ሰቶከሆለም፡፡
The post በስዊድን የአንድነት የድጋፍ ማህበር በሓገራችን አትዮጵያ ዕለት ተዕለት እየተንሰራፋ የመጣውን አምባገናናዊ ስርዓት ያወግዛል appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.